Connect with us

የጨረቃ የተባለው በጸሐይ የሚደረግ ምርጫ

የጨረቃ የተባለው በጸሐይ የሚደረግ ምርጫ
Photo: Social Media

ፓለቲካ

የጨረቃ የተባለው በጸሐይ የሚደረግ ምርጫ

የጨረቃ የተባለው በጸሐይ የሚደረግ ምርጫ፡፡ አራት ኪሎ ስም ሲያወጣ፤ ትግራይ ምርጫውን ይመርጣል፡፡
******
(ከስናፍቅሽ አዲስ)
ጨረቃ ፖለቲካ ሆነች፡፡ ጨረቃ ቤት ወደ ጨረቃ ምርጫ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጸሐይ የሚደረገውን የትግራይ ክልላዊ ምርጫ የጨረቃ ሲሉ ስም ሰጥተውታል፡፡ የዳቦ ስሙ ያላሳሰባት ህወሃት ወንድ የሆነ ያስቆመኛል ያለችውን ምርጫ በጸሐይ አድርጋዋለች፡፡

በህወሃትም ሆነ በብልጽግና በኩል ያለው የአንድ ጋን ጥንስስ መሆን አባዜ የትግራይ ምርጫ የህዝብ ፍቃድ ይኑርበት አይኑርበት የማየት እድል አልሰጠንም፡፡ ብልጽግና ማየትም ሆነ መታዘብ ነውር ነው ብሎ ኤርፖርት ሰው ያወርዳል፤ ህወሃትም ብትሆን ምርጫውን ያልተቀበለ አይምጣብኝ ብላለች፡፡ የህዝቡን ስሜት በዚህ የዝሆኖች የማዶ ለማዶ ጠብ መረዳት ከባድ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኢቲቪ ቆይታ ቁጭ ብዬ ተመለከትኩት፤ ነይ ተኚ ምን የሚረባ ነገር አለው የሚለውን የእህቴን ንትርክ ችዬ የጠቅላዩን ንግግር ቤተሰቡ ተሰብስቦ ከሚመለከትበት ዘመን ለብቻዬ አምሽቼ በማይበት ምዕራፍ አየሁት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኔ ነው እንደውም በአፍሪካ ብቸኛው ድጋፍ ያለኝ መሪ ነኝ ብለዋል ያድርግላቸው፡፡ እውነት ከሆነ እንደኔ ደስተኛ የለም፤ ምክንያቱም ብቻዬን ከመደገፍ ዳንኩ፡፡ የአለማያ ሐይቅ ሙላትና የአሜሪካ ችግኝ ልትከል ብትል እሳቸው ላይ አለመድረስ እንዳልሰማሁ የቆጠርኳት ንግግራቸው ናት፡፡

የትግራይ ምርጫ እውን ሆኗል ትግራይም መርጣለች የምርጫው ህጋዊ ነው አይደለም ውዝግብ አሁን መልኩን ወደ ምርጫው ስም ቀይሯል፡፡ የጨረቃ ነው ባለ ይዞታ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ይዞታው የምሪት ነው የውርስ ላይ መድረሳችን አይቀርም፡፡

የትግራይ ምርጫ በሰላም ተጠናቆ ህዝቡ ህወሃት እንደነገረችን ምርጫውን ፈልጎት ወኪሉን ለመምረጥ ከበቃ ወንጀልነቱ አይታየኝም፡፡ የሚበልጠው ሰላም ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ከጥይት ጭምብል ልኬ ኮሮናን ብታደግ እመርጣለሁ እንዳሉት ለሰላም እጅ መስጠታቸው ጥቅሙ ለሀገር ነው፡፡ በምርጫ ስበብ የሚከሰት ቀውስ ከምርጫ መደረጉ አለመደረጉ ጉዳይ በከፋ ሀገር ይጎዳል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top