Connect with us

በኦሮሚያ ክልል ለተጎዱ ወገኖች የ40 ሚልየን ብር ድጋፍ ተደረገ

በኦሮሚያ ክልል ለተጎዱ ወገኖች የ40 ሚልየን ብር ድጋፍ ተደረገ
Orthodox Christians pray outside the closed Medhane Alem Cathedral as the government recommends to avoid large gatherings to curb the spread of the Covid-19 in Addis Ababa, Ethiopia, on April 5. Photographer: Michael Tewelde/AFP via Getty Images

ማህበራዊ

በኦሮሚያ ክልል ለተጎዱ ወገኖች የ40 ሚልየን ብር ድጋፍ ተደረገ

በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በጽንፈኞች ጉዳት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች የመጀመሪያ ዙር 40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ባደረገበት በዛሬው ዕለት በቀጣይም ሦስት ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በቀያቸው የማቋቋም ተግባር ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ።

ጉዳቱን ለማጣራትና የተጎዱንት የመልሶ ለማቋቋም በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ሄኖክና ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ በተገኙበት በጠቅላይ ቤተክህነት በሰጠው መግለጫ ለተጎጅዎች ተብሎ የተሰባሰበውን ገንዘብ ማከፋፈሉን አስታወቀ።

ቤተክርስቲያን የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራን የተጎዱትን የሚያጽናና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ከ260 በላይ አባላት የተሳተፉበት ልዑክ በመላክና የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም የጉዳቱን መጠንና ክርስቲያኖች ያሉበትን ሁኔታ ማጣራቷን ያስገነዘበው መግለጫው የተጎዱትን ለይቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየስማቸው የሒሳብ ደብተር እንዲከፍቱ አድርጎ ገንዘቡ በቀጥታ እንዲደርሳቸው ማድረጉን ገልጧል።

በተጎጅዎች ስም ከተሰበሰበው ገንዘብ አንድም ሳንቲም ቢሆን ለሌላ ዓላም አለመዋሉን ያስታወቀው የዐቢይ ኮሚቴው መግለጫ በቴክኒክ ኮሚቴው አማካኝነት በእያንዳንዱ ቤተሰብ ሰማዕትነት የተቀበሉና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ክርስቲያኖች ተለይተው የቤተሰብ ብዛት እና የወደመባቸውን ንብረት ግምት ውስጥ ያስገባ ትንተና ተደርጎ ገንዘቡ መከፋፈሉን አስታውቋ።

በሀገረ ስብከታቸው በሚኖሩ ክርስቲያኖች ላይ አሰቃቂ ግፍ የተፈጸመባቸው ብፁዕ አቡነ ሄኖክ “የክርስቲያን ልጆቻችን መንፈሳዊ ጥብዓት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰማዕትነት ተጋድሎ ነው። የተጎዱ ልጆቻችን መልሰን ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ያቀረብነውን አባታዊ ጥሪ ተቀብላችሁ ፈጣን መልስ የሰጣችሁ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ከሰማዕታቱ በረከት ተሳታፊ ሆናችኋል” ብለዋል።

የጂግጂጋ፣የምሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ በበኩላቸው “ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኃላፊነቱ የሁላችን መሆኑን ተረድተን በአንድነት እንቁም። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ በሻሸመኔ ያላግባብ የታሠሩ ልጆቻችን እንዲፈቱን መንግሥትን እንጠይቃለን” ብለዋል።(ማኀበረ ቅዱሳን)

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top