Connect with us

በጎ ሰዎች ተሸለሙ

በጎ ሰዎች ተሸለሙ
Photo: Social Media

ዜና

በጎ ሰዎች ተሸለሙ

#በጎ_ሰዎች ተሸለሙ

የበጎ ሰው ልዩ ሽልማት በኢንተርንኮንቲኔንታል ሆቴል ኘረዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በክብር እንግድነት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። የሽልማት ስነስርዓቱን ባላገሩ ቲቪ በቀጥታ ስርጭት ሸፍኗል። ተሸላሚዎቹ:-

1) አቶ ካሊድ ናስር፡– ባለፉት አምስት ወራት በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የገዛ መኖሪያ ግቢያቸውን ሳይቀር በመስጠት፣ መጠለያ የሌላቸውን በመደገፍ የበጎ አድራጎት ሥራ የሠሩ፣

2) አቶ ኪሮስ አስፋው፡-ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያለማቋረጥ መቶ ጊዜ የሕዳሴ ግድብ ቦንድ የገዙ፣

3) ቢኒያም ከበደ፡-የንባብ ለሕይወት መሥራች አዘጋጆች አንዱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቭዥን መስራች፣

4) መሐመድ አልአሩሲ:- የህዳሴው ግድብ ተሟጋች ፡ በተለይም በአረብኛ ቋንቋ ከግብፆች ጋር በሚዲያ እየተናነቀ የሚገኝ ወጣት ናቸው።

5) ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ:- አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ መምህሩ እንዲሁም በውሃ ዲፕሎማሲው ዘርፍ ከህዳሴ ግድቡ ግንባታ ጀምሮ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙት ፣ ብሎም መፅሃፍ የፃፉት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ የ8 ኛው በጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

6) ኢትዮ ቴሌኮም:- በዓመቱ ውስጥ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በሰራቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የ2012 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ድርጅቱን በመወከል የተገኙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

7) የሕክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች:- የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን ከተሰረተ ጀምሮ ራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የዜጎች ደኅንነት ለመጠበቅ ከፊት የተሰለፉ የጤና ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የ2012 የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመድረኩ የጤና ባለሞያዎችንና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመወከል ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

8) የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ ሠራተኞች በሙሉ (ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ሠራተኞቹን ወክለው ሽልማቱን ተቀብለዋል)

#የድሬቲዩብ ኤዲቶሪያል ቦርድ ተሸላሚዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top