Connect with us

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዴታቸውን ያልተወጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ተበዳሪዎችን አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዴታቸውን ያልተወጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ተበዳሪዎችን አስጠነቀቀ
Photo: Social Media

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዴታቸውን ያልተወጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ተበዳሪዎችን አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግዴታቸውን ያልተወጡ የጋራ መኖሪያ ቤት ተበዳሪዎችን አስጠነቀቀ
,,,,,
የኮሮና ቫይረስ በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሚያዚያ 2012 ላይ እስከ ሰኔ/2012 ለሦስት ወራት የሚቆይ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን ይህ የእፎይታ ጊዜ የተጠናቀቀ በመሆኑ የቤት ብድር ያለባቸው ደንበኞች ክፍያቸውን ከሐምሌ 2012 ጀምሮ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው በባንኩ የሞርጌጅና የግል ብድር ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ሽመልስ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ለ20/80 እና ለ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤት በ13ዙር እንዲሁም ለ40/60 ተበዳሪዎች በሁለት ዙር የቤት ብድር የሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ለ105ሺህ ደንበኞች የቤት ብድር መስጠቱን ያስታወሱት አቶ መንግስቱ በሦስት ወራት የእፎይታ ጊዜው ባንኩ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ክፍያ ማዘግየቱን ጠቁመዋል፡፡

በእፎይታ ጊዜው የተጠቀሙ ደንበኞች ያልከፈሉት ክፍያ ከቀሪ ክፍያቸውና ከሚቀረው ጊዜ ጋር ታስቦ ከሐምሌ 2012 ጀምሮ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ዕዳቸውን የማይከፍሉ ደንበኞች እዳቸው እንደሚጠራቀምባቸውና አላስፈላጊ የወለድ ጫና እንደሚፈጥርባቸው በመግለፅ በገቡት ውል መሰረት እዳቸውን እንዲከፍሉ ነው አቶ መንግስቱ ያሳሰቡት፡፡

በርካታ ደንበኞች በውላቸው መሰረት እዳቸውን እየከፈሉ መሆኑን በመጠቆም ሁሉም ደንበኞች ቀሪ እዳቸውንና በየወሩ የሚከፍሉትን መጠን ውል ከገቡባቸው ቅርንጫፎች በማጣራት በማንኛውም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ወርሃዊ ክፍያቸውን መክፈል እንደሚችሉ አቶ መንግስቱ ገልፀዋል፡፡(ኢት ንግድ ባንክ)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top