Connect with us

መስከረም መቼ ነው?

መስከረም መቼ ነው?
Adey abeba, a flower that grows in Ethiopia only from September to November | © maailmajapaikat / WikiCommons

ጥበብና ባህል

መስከረም መቼ ነው?

መስከረም መቼ ነው?
(አስራት በጋሻው)

ጌታዬ ሆይ መቼም ቢሆን ጥሪህ በደረሰኝ ቀን እመጣለሁ። አልቀርም።

ከፈጠርከው ነገር ሁሉ በጊዜ ውስጥ እንድኖር ስላደረከኝ አመሰግንሀለው። ልመናዬንም ቅሬታዬንም ሰምተህ እንደምትፈጽምልኝ እተማመናለሁ።

ከዘመኔ መሀል የተከሰተውን የአመታትህ መለያ የሆነውን 2012 አ.ምን ጠላሁት ። ይህ አመት አንጀት ሆኖብኛል። ጎታታ እና ለፈረንጆችም የሰጠሀቸው 2020ም ቢሆን ያው ነው። ጥላቻዬ እየባሰብኝ የመጣው ደግሞ ሊያልቅ ሲል ነው።

ጌታዬ በእድሜ አቆጣጠርህ ላይ ይህን ዘመን ለኔም ሆነ ለሀገሬ ሰዎች ቀንስልን ።ከገጀራም ሆነ ከኮሮና ተርፈን ቤት ስንገባ አንድ አስደሳች ዜና ሰማን።ምክር ቤቱም መንግስትም የስልጣን ዘመናቸውን አራዝመዋል። አንኳን አበጁ ። እንሱስ በቴሌቪዥን ተከራክረው ነው።እኔ የት ሄጄ ልከራከር? አመቱን ምን አደረገህ? ላልከኝ በዚህ አመት ምን ያልሆነው አለ?አንተ ማታውቀው አለ?

አንተ ደግሞ የኛኑ እድሜ ተመልክተህ እንዲሁ እንድታራዝምልን ብንጠይቅህ ምን ችግር ይኖረዋል?

የኢትዮ ቴሌኮም ሰዎች ያልተጠቀማችሁበትን እናካካስላችኃለን ብለዋል። ያቺ ወጣት ልጅ አንጀቷ ራርቶ እንዲህ ካደረገች አንተማ ምኑ ይሳንሀል?

የኔንም የቤተሰቤንም አቤቱታ ተቀበል ። የሀገሬ ሰው ያንተን ስም ሳይጠራ አይውልም ። ዱቄትና ዘይትም ተቀብሎ አንተኑ አመስግኖ ይተኛል። ለድሀው አቃፊው አንተ ነህና።

ጌታ ሆይ መስከረምን ላክልኝ 2012ንም አንሳልኝ ።ከመዝገብህ ሰርዘው ። ተጨማሪ እኖር ዘንድ አንድ አመት ፍቀድልኝ ።
የኔንም የሀገሬንም ጸሎት ስማ ።ብቻ ዝም ብለህ በአጭር ቃል በሬን አንኳኩ ይከፈትላችኋል ባልከው ቃል መሰረት ጥያቄዎቼን ተቀብለህ በሆነ መንገድ  ”ምስኪኑ የኢትዬጵያ ህዝብ ሆይ ከህይወት ዘመንህ 2012ን ተሰርዟል ” በለን

ከሰቆቃ ሁሉ ሰውረን
ጌታ ሆይ መስከረም ግን መቼ ነው?

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top