Connect with us

“ነፍጠኛ” የሚለው ቃል በሕግ ይታገድ!

"ነፍጠኛ" የሚለው ቃል በሕግ ይታገድ!
ነፍጠኛ Concept & graphic design by #Gudukassagraphix #abygirma

ትንታኔ

“ነፍጠኛ” የሚለው ቃል በሕግ ይታገድ!

“ነፍጠኛ” የሚለው ቃል በሕግ ይታገድ!
(ያሬድ ጥበቡ~ የኢህዴን ነባር ታጋይ)

የጥንት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የክፍል ባልደረባዬ የነበረው ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለነፍጠኝነት ሲያወራ ሰማሁት። እናም አሰብኩ። ልክ ደርግ ጋላ የሚለውን ቃል መጠቀም በህግ እንዳገደው ሁሉ፣ የኦሮሚያ ክልሉም ብልፅግና ፓርቲና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ነፍጠኛ የሚለውን ቃል መጠቀም ህገወጥ ማድረግ አለባቸው። ምክንያቱም ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚገደሉት ነፍጠኛ እየተባሉ በመሆኑ ቃሉን መጠቀም ነውርና በህግ የሚያስጠይቅ ካልተደረገ፣ በዚህች ሃገር ላይ ገና የብዙ ንፁሀን ደም ይፈሳል።

ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የሃገሪቱ ጥግ የመኖር መብት ስላላቸው፣ ነፍጠኛ እየተባሉ መገደሉ እንዲቆም ከተፈለገ መንግስት ይህን ቃል መጠቀም ወንጀል ነው ብሎ ማወጅ አለበት። ያን ሳያደርግ ቀርቶ እነሺመልስ እብዲሳ በድብቅም ሆነ በህዝብ አደባባይ ሲጠቀሙበት ካየን፣ መንግስትን የግድያዎቹ ተባባሪ አድርገን መመልከት ግዴታችን ይሆናል። ከመመልከትም በላይ ለህልውናችን እንድንተጋ እንገደዳለን። ይሄው ነው!

===

ፎቶ:- በሲያትል የሰሞኑ ሰልፍ ላይ የታየ መፈክር!

አዎ!. በአያቶቼ፣ በአባቶቼ ነፍጠኛ ነኝ! እናም ምን ይጠበስ?

(ጫሊ በላይነህ)

እነሆ ህወሓት ከመራራ ትግልና መሰዋዕትነት በኋላ ከማዕከላዊ መንግስቱ ተሸንፋ ብትባረርም ብልሹ አስተምህሮዋ አገር ማመሱን፣ ማተራመሱን ግን ቀጥሏል። የህወሓት የአመታት የክፋት አዝመራ ፍሬው ጎምርቷል።

ህወሓቶች ከጫካ ጀምሮ ለአማራ እና ለክርስቲያኑ በተለይም ለኦርቶዶክስ እምነት ያላቸው ጥላቻ በቃላት የሚገለፅ አልነበረም። እናም አማራ እና ኦርቶዶክስን የሚያጣላሉት በጅምላ “ነፍጠኛ” እያሉ ነበር።

ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱዎች ቱትሲዎችን ሊጨፈጭፉ ሲሉ የሰጡት ስም “በረሮ (cockroch)” የሚል ነበር። የኢትዮጵያ ሁቱዎች ደግሞ ሊጨፈጭፉ ሲነሱ “ነፍጠኛ” የሚል የመግባቢያ ኮድ ፈጠሩ። “ነፍጠኛ” ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ ነፍጥ ወይንም መሳሪያ ያነገበ ማለት ቢሆንም እነዚህ ነፍሰ ገዳዮች ግን “ነፍጠኛ” ብለው በጠላትነት የሚፈርጁት እነማንን እንደሆነ ግልጽ ነው።

መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት “የነፍጠኛውን አከርካሪ ዳግም እንዳያንሰራራ አድርገን ሰብረነዋል” ሲል ኤታማዥር ሹም የነበረው ሳሞራ የኑስ “ነፍጠኛን እንደ ሲጋራ አጭሰን ጥለነዋል” ብሎ ነበር።

ጡረተኛው አቦይ ስብሀትም ” አማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ስለማለቱ ብዙዎች የምናስታውሰው ነው።
የእነመለስ ራዕይ አስቀጣዮች እነሆ ዛሬም ከአሳዳጊዎቻቸው ህወሓቶች የተማሩትን ይዘው “ነፍጠኛ” ያሉትን ወገን በአደባባይ ሲያጥላሉ፣ ሲረግሙ፣ ሲዝቱ ከመዋል አልፈው ካራ እስከማስመዘዝ ደርሰዋል።

የእነሱ ግርፍ የሆኑ ወጣቶች ይህን የኮድ ፍረጃ የተረጎሙት “ነፍጠኛ” ማለት አማራ ነው። “ነፍጠኛ” ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነው በማለት ስለመሆኑ በየጊዜው እነዚህን ወገኖች ላይ እየተፈፀሙ ያሉት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ህያው ምስክሮች ናቸው።

ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ የህወሓት ቫይረስ ተሸካሚዎች አፋቸውን ሞልተው “ጥቃቱ ጄኖሳይድ ነው አትበሉ። አንድ ሀይማኖትና አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ነው አትበሉ” በማለት በግልፅ ከገዳይ ጋር ያላቸውን ውግንና ያንፀባርቃሉ።

የህወሓት የተሳሳተ እና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ትርክት ተሸካሚ የሆኑ የኦዴፓ የአሁኑ ብልፅግና አንዳንድ አመራሮች ከተሳሳተ ትርክታቸው ባልፀዱበት ሁኔታ መሰል ችግሮች በዘላቂነት እልባት ያገኛሉ ማለት ዘበት ነው።

እናም ገዥው ፓርቲ ብልፅግና የህወሓት ውርስ የሆኑት የማጥቂያ ፍረጃዎችና ሌላውን ወገን በጠላትነት መመልከቻ መነፅሮቹን አውልቆ አርቆ ሊቀብር ይገባል። ከፋፋይ ትርክቶችን ከካድሬዎቹ፣ ከአባላቱ ጭንቅላት ውስጥ በአስተማማኝ መልኩ ማፅዳት ወይንም ማደስ ይጠበቅበታል። “ነፍጠኛ”፣ “ትምክህተኛ”፣ “ጠባብ”…የሚሉ የህወሓት የጥላቻ ፍረጃዎችና የተሳሳቱ ትርክቶች ተሸካሚ የሆኑ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችም ብትሆኑ አሁንም በአመለካከት ህወሓትን እያገለገላችሁ መሆኑ ሊያሳፍራችሁ ይገባል።

በለውጥ ስም ስልጣን ላይ ተቀምጦ የህወሓት ኘሮፖጋንዳ ማሸን መሆን አይቻልም። እናም ከቻላችሁ ንቁና ራሳችሁን አስተካክሉ!..ካልቻላችሁ በሐሰት ትርክት ህዝብን አታባሉ! በሰላም ወደምትሄዱበት ሂዱ!!
***

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top