Connect with us

የመረጠው ከንቲባ መርቶት በማያውቀው አዲስ አበባ

የመረጠው ከንቲባ መርቶት በማያውቀው አዲስ አበባ
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

የመረጠው ከንቲባ መርቶት በማያውቀው አዲስ አበባ

የመረጠው ከንቲባ መርቶት በማያውቀው አዲስ አበባ፤ ምርጫው የሚመራው ከንቲባ ከአድልዎ ነጻ እንዲሆን ነው፡፡
ክብርት አዳነች አበቤ አደራዎትን እንቅፋት ከሆኑ ደላላ አርቲስቶች ከተማዎትን ይጠብቁ፤
ከስናፍቅሽ አዲስ

የመረጥነው ከንቲባ መርቶን አያውቅም የሚመራን ከንቲባ ግን ባለመስራት፣ በአድልዎ አሰራርና በሙስና ያሰቃየን ነዋሪዎች ነን፡፡ ኢንጅነሩ ታከለ ብዙ የሚታሙበት ነገር ቢኖርም አዲስ አበባን የኔ በማለትና ከአዲስ አበባ ደሃ ጋር ለመቆም በመሞከር ቀዳሚው የኢህአዴግ ዘመን ከንቲባ ይመስሉኛል፡፡

አዲስ አበባ በኢ ፍትሐዊ አሰራር የተጎሳቆለች ከተማ ናት፡፡ ከንቲባዋ በተሾመ ማግስት ከሰፈሩ ሰው ያግዛል፤ ወደ ሰፈሩ ደግሞ ሀብቷን ያጋግዛል፡፡ ከፍ ያለ ሀሳብና አዲስ አበባ የተዋወቁት በከንቲባ አርከበ እቁባይ ጊዜ ነበር፤ እሳቸው ከአቶ መለስ አልተግባቡም፡፡ ኢንጅነር ታከለ ከዶክተር አብይ አለመግባባት ያንሳቸው አልያ ሌላ ምክንያት ቀን የሚያወጣው ሆኖ ሳለ አዲስ አበባን የኔ በማለት ግን ስመ መልካም ናቸው፡፡

አዳነች አበቤ አሁን ከንቲባችን ሆነዋል፡፡ የአዳነችን ከንቲባነት አለመቀበል ሞኝነት ነው፡፡ መጀመሪያ አዲስ አበባ በመረጠችው ከንቲባ ተምርታ አታውቅም፤ አዲስ አበባ ሳትመርጣቸው ከመሯት ከንቲባዎች አንዷን ምናልባትም የመጨረሻዋን አልቀበልም ከማለት የምንፈልገው አይነት ከንቲባ እንዲሆኑ ማድረግ የሚበልጥ ጉዳይ ነው፡፡

አዳነች አበቤ በቆራጥ ውሳኔ አይታሙም፡፡ በዚህ ላይ ከአድልዎ የጸዳ አሰራር እንዲከተሉ ነቅቶ መጠበቅ፣ ችግር ካለም እንዲታረም መጮህ ወሳኙ ነገር ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ሴትየዋ ብርቱ በመሆን አይታሙም፤

ባይሆን አዲሷን ከንቲባ ሰው በተሾመ ቁጥር ብሔሩን እየቀየረ የአጀበና የአጨበጨበ ደላላ አርቲስት ዳግም በታከለ ኡማ መንገድ እንዲሸኛቸው እድል መስጠት የለባቸውም፡፡ ሆሆይታና ዳንኪራ የደሃ ከተሜን ኑሮ አይለውጥም፡፡ ልብስና አለባበስ ለራቁቱ ደሃ ከተሜ ሞገስ አይሆንም፡፡ ገንዘብ እየረጩ በአዝማሪ መወደስም ቢሆን የለማ ከተማ መሪ አያደርግም ስለዚህ ከንቲባችን እንዲህ ካለው ግርግር መራቅ አለባቸው፡፡ የግብር ከፋዮን ብር ግብር እያበሉ ቢያስጨፍሩ የክፉ ቀን ማንም ከጎናቸው እንደማይቆም ከቀድሞው ከንቲባ ማየት ነው፡፡

አዲስ አበባን መምራት ከባድ ቢሆንም በዘረኝነት ያልታመሰ ነዋሪ ያለባት ስልጡን ከተማ በመሆኗ ደግሞ ችግሩን ያቀለዋል፡፡ መልካም ስምና መልካም ስራ ደግሞ ቀን ቆጥሮ ይክሳል፤ ልጆች ቀና ብለው የሚሄዱበት ትውልድ የሚኮራበት ዘለዓለማዊ ስንቅ ነው፡፡ እምነት ላለው ደግሞ በሰማይም ዋጋ አለው፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top