Connect with us

8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በልዩ ሁኔታ ጷጉሜ 1 ይካሄዳል

8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በልዩ ሁኔታ ጷጉሜ 1 ይካሄዳል
Photo: Social Media

ዜና

8ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በልዩ ሁኔታ ጷጉሜ 1 ይካሄዳል

በየዓመቱ ማብቂያ ላይ የሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት የ2012 ስምንተኛ መርሃግብር ጿጉሜ 1 ቀን 2012 በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ይካሄዳል።

የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት ትላንት ሐምሌ 12/2012 በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ የዘንድሮው የሽልማት መርሃ ግብር በልዩ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስታውቋል።

የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ቀለመወርቅ ሚደቅሳ እንደተናገሩትም፤ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ መጋቢት 15 እጩዎችን የመቀበልና አበርክቷቸውን የማጥናት ሥራ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም ከ200 በላይ እጩዎችን ተቀብሏል። ሆኖም በተከሰተው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት የጥናት ሥራው በእቅዱ መሠረት ሊከናወን እንዳልተቻለ አውስተዋል።

ስለዚህም ለወትሮው ልዩ ተሸላሚ በሚመረጥበትና በሚሸለምበት የቦርድ አባላት የጥቆማና ምርጫ ሂደት መሠረት፤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሥራ እንዲሳካ ላደረጉ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ሥራ ላይ ግንባር ቀደም ከሆኑት መካከል ተሸላሚዎች ተመርጠዋል ተብሏል።

በዚህ መሠረት ስምንት ተሸላሚዎች እንደሚኖሩና በሽልማቱ እለት ይፉ እንደሚደረግ ቀለመወርቅ አስታውቀዋል። የድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበር ዳንኤል ክብረት በበኩላቸው፤ ምንም እንኳን አገር በብዙ አስጨናቂ ክስተቶች መካከል ብትሆንም በጎዎችን ማመስገንና ማጉላትም አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል። ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ ተገቢው ጥንቃቄ እንደሚደረግና ተመልካችም በቀጥታ ስርጭት እንደሚመለከተው ተናግረዋል።

[አዲስ ማለዳ]

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top