Connect with us

መብትን ከመጠየቅ ውጪ ጥላቻን ያልደገሰው የዎላይታ የመብት የጥያቄ

መብትን ከመጠየቅ ውጪ ጥላቻን ያልደገሰው የዎላይታ የመብት የጥያቄና የሰለጠነ ትግል ድል

ባህልና ታሪክ

መብትን ከመጠየቅ ውጪ ጥላቻን ያልደገሰው የዎላይታ የመብት የጥያቄ

መብትን ከመጠየቅ ውጪ ጥላቻን ያልደገሰው የዎላይታ የመብት የጥያቄና የሰለጠነ ትግል ድል፡፡
ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ቤተክርስቲያን አልተቃጠለም፤ ክርስቲያን አልተገደለም፡፡ መስጂድ ፈርሶ ሙስሊም አልታደረም፡፡ መጤ ተብሎ የተገደለ፣ የተዘረፈ የለም፡፡ ዎላይታ በሰለጠነ አግባብ ጥያቄ ጠየቀ፡፡ ጥያቄው ትግል ነበር ትግሉ መብትን ብቻ ደጋግሞ መጠየቅ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሳይዘልፍ፣ ለውጡን ንቆ ሳይሆን የለውጡ ባለቤት ነኝ ብሎ፡፡ ገድሎ ሳይሆን ሞቶ ዎላይታ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

በዚህ ጨለማ ዘመን እንቅፋት ሲመታው መንጋው አጠገቡ ያለውን መጤ ብሎ በሚገልበት ኋላ ቀር ጊዜ ዎላይታ ዓላማውን ባልሳተ ትግል ጥያቄውን ጠይቋል፡፡

በደቡብ ክልል የሚነሱ የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች መልሳቸው አፈ ሙዝ የሆነው ዛሬ አይደለም፡፡ ሲዳማ በሃያ አምስት አመቱ ክልል ሆኗል፡፡

ክልል መሆን የተለየ ጉዳይ አድርጌ ባላየውም በደቡብ የነበረው የኢህአዴግ ስርዓት ግን ልዩ ወረዳ ለጠየቀ እስር የብሔርና የማንነት ጥያቄ ላቀረበ ጥይት በመስጠት የስቃይ ቀጠና ሆኖ ኖሯል፡፡

የደቡብ ጥያቄዎች ሀገር ለሚያፈርሱ አጀንዳ ነጣቂዎች ምቹ ናቸው፤ ምክንያቱም በሰለጠነ መልኩ በፍጥነት አይፈቱም፡፡ የዎላይታን ጥያቄ በሰለጠነ መልኩ መፍታት አሁንም ነገ ዛሬ ባይባል ለሁሉም ይጠቅማል፡፡

ዎላይታዎች ከባዱን ጊዜ በትእግስት አልፈውታል፤ መንግስትና ዎላይታን ደም አፋሶ የሰው ደም መላስ የፈለገ ክፉ ሀሳቡ ከሽፏል፡፡ ማንም ሳይሞት ነገሩ እልባት ቢያገኝ መልካም ነበር፡፡ አልሆነም የሰው ህይወት ጠይቋል፡፡ ያም ሆኖ ሰላም ለማስከበር የገባው ሠራዊት በሰላም ተሸኝቷል፡፡ ያ ምድር ከዚህ በኋላ ሰላም ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡

ትናንት ታስረው የነበሩ የዞኑ አመራሮች ሲፈቱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ቀጣዮ ምላሽ ምን ይሆናል የሚለው በሂደት አብረን እናየዋለን፡፡ የህዝብ ጥያቄ በሀገርና በህግ አግባብ ፈጥኖ የሚፈታበት አሰራር እንዲህ ያለውን ችግር፣ የሰላም መደፍረስ፣ የህዝብ ሞትና የጊዜና የገንዘብ ውድመት ይታደጋል፡፡

የዎላይታዎቹ አዲስ ክልል ለቀጣዩ ዘመን መለወጫቸው ይደርሳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እንዲህ ባለ ጨዋነትና ሰላማዊ ትግል የማይመለስ ጥያቄ የለም፡፡ ወገንን በመንጋ ካልገደሉ ዲሞክራሲ የሌለበት በሚመስል ሀገር ያለ ወገን ጥቃት ጥያቄን አቅርቦ መልስ ማግኘት ስልጣኔን ለወገን ማስተማር ነው፡፡ በዚህ የዎላይታ ህዝብ አሁንም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top