Connect with us

ተመስገን ጥሩነህ እና ሽመልስ አብዲሳ በጋራ መግለጫ ሰጡ

ተመስገን ጥሩነህ እና ሽመልስ አብዲሳ በጋራ መግለጫ ሰጡ

ፓለቲካ

ተመስገን ጥሩነህ እና ሽመልስ አብዲሳ በጋራ መግለጫ ሰጡ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ተመስገን የተፈጠረው ክስተት መቼም ቢሆን መከሰት የሌለበት እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የማይደግፈው የነውጥ መንገድ ነው ያሉ ሲሆን የኦሮሞ እና የአማራ ወጣቶች ለውጡን እውን ለማድረግ በአንድነት እንደቆሙ ሁሉ ዛሬም በመተባበርና መደጋገፍ የብልጽግና ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲን ለማጥፋትም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት ለመጉዳት የሚሰሩ የነውጥ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በሚደረገው ጥረት ውስጥ በህግ ቁጥጥር ውስጥ ያሉ ሁሉ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሳይሆን ህግ በሚፈቅደው መንገድ ብቻ ምርመራው እየተጣራ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የትኛውም ብሔረሰብ ላይ የሚደርስ ኢ- ሰብአዊ ጥቃት የደረሰበት ክልል ውስጥ እስከተፈጸመ ድረስ የክልሉ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል ያሉት ፕሬዚዳንቱ እንደ መንግስት ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም የክልል መንግሥታት ከተጠቂዎች ጎን በመቆም ህግና ሥርዓትን ማስከበር እና ፍትህን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ብልጽግና የህዝቦችን ትስስር በማስፋት በአንድነት ለልማትና እድገታችን የሚሰራ ፓርቲ አንደመሆኑም በየትኛውም ክልል ውስጥ የሚኖር ብሔር የተነጠለ ማንነት ሳይሰማው የሚኖርበት እና ኑሮውን በተረጋጋ ሁኔታ የሚቀጥልበትን እድል ላይ ትኩረት አድርገን መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ለደረሰው ጉዳት 3 ሺ ኩንታል የምግብ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡

የኦሮሚያው ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳም በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች መካካል እሳት እየጫሩ የ ለውጡን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚደረገው ጥረት አይሳካም፤ ትብብርና ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል የአርቲስት ሀጫሉን ኅልፈተ ህይወት ተከትሎ ለደረሰው አስከፊ ሀዘን ከኦሮሞ ህዝብ ጎን ስለነበረ እና ለተደረገው ድጋፍ ሁሉ በኦሮሞ ህዝብ ስም አድናቆታቸውንና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top