Connect with us

ዛሬ የየብሱ ላይ ግዙፍ እንስሳ የዓለም ዝሆን ቀን ነው

ዛሬ የየብሱ ላይ ግዙፍ እንስሳ የዓለም ዝሆን ቀን ነው
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

ዛሬ የየብሱ ላይ ግዙፍ እንስሳ የዓለም ዝሆን ቀን ነው

ስለ ሀገሬ ዝሆኖች ህልውና ሕይወታችሁ ለሰጣችሁ የኢትዮጵያ ሬንጀሮች የእናንተ ታሪክ በተፈጥሮ ቀለም ለዘለዓለም ተጽፏል፡፡
ሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ዛሬ የዝሆን ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ስለ ባቢሌ ዝሆኖች አብልጩ አስባለሁ፡፡ እነሱ በአፍሪቃ ቀዳሚው የሚባለው የዝሆን መጠለያ ግዛት ነዋሪዎች ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ በአፍሪቃ መኖር የተነፈጉ፣ መከራ የሚያሳድዳቸው፣ የሰው ልጅ የሚጨክንባቸው ፍጥረት ሆነዋል፡፡

ደግሞ ስለ ባቢሌ ዝሆን ጠባቂ ሬንጀሮች አስባለሁ፡፡ ለተፈጥሮ ፍቅር ዋጋ ስለሚከፍሉ፤ ለዝኆን መኖር ስለሚሞቱ፡፡ የዓለም ሀገራት ዝሆን ይጠበቅ ዘንድ ተስማምተዋል፡፡ በቃል ኪዳን ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ የታደሉት የጥበቃ ስራቸው ስኬታማ ሆኖ የዝሆን ሞት ብርቅ ኾኖባቸዋል፡፡ እኛ ግን ከዝኆን አልፎ የዝኆን ጠባቂው ሞት በቃ ማለት ያልቻልን ዜጎች ሆነናል፡፡

ዝሆንን የምንጠብቀው ለራሳችን ስንል ነበር፡፡ ዝሆንን የታደገ ምድር ራሱን ያኖራልና፤ ዓለም ዛሬ የዝሆን ቀን ብሎ ያከብራል፡፡ ለዝሆን ጥበቃ ቁርጠኛ የሆኑ ሀገራትና ዜጎቻቸው የድል ጽዋቸውን ያነሳሉ፡፡ ዳግም ቃል ይገባሉ፡፡ ይህንን ግዙፍ ፍጥረት ወደሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር፤

እኛ በዚህ ዓመት በአንድ ስፍራ ስምንት ዝሆኖች ተገድለውብናል፡፡ ስለ ሞቱ ዝሆኖች ሀዘናቸውን በቅጡ ያልተወጡት የማጎ ስካውቶች ለምን ተናቃብኝ ባለ ገዳይ ቂም ተይዞባቸዋል፡፡ እየሞቱ ዝሆን እንዳይሞት ዛሬም በስራ ገበታቸው፤ ዛሬም በዱር ህይወታቸው ውስጥ ናቸው፡፡

ባቢሌ የሰሞኑን ግርግርና አመጽ ተከትሎ አንድ ዝኆን ነፍሱን ተነጥቋል፡፡ ገድያው ቀላል እንዳልሆነ የሚያሳየው ግን ጥርሱ አለመኖሩ ነው፡፡

ያም ሆኖ አሁንም እድል አለ፤ ከጨበራ ጩርጩራ እስከ ኦሞ ከማጎ እስከ ቃፍታ ያለውን ዝሆን ለትውልድ ለማሻገር ግርማ ሞገስ ያለውን ግዙፍ ልዩ የባቢሌ ዝሆን ከጥፋት ለመታደግ እድል አለ፡፡ ይህንን ቀን ስናከብር የዱር ህይወት ጀግኖችን፣ ለዝኆን ጥበቃ የሞቱ ሬንጀሮችን፣ በሞታቸው ቤተሰባቸው የተበተነባቸውን እነሱን ሁሉ አብረን እናክብራለን፤ እነሱን ሁሉ እንዘክራለን፤ ክብር ይገባቸዋልና፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top