Connect with us

በአዲስ አበባ ልዩ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ እንደሚጀመር ምክትል ከንቲባው አስታወቁ

በአዲስ አበባ ልዩ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ እንደሚጀመር ምክትል ከንቲባው አስታወቁ
Photo: Facebook

ዜና

በአዲስ አበባ ልዩ የመሬት ኦዲትና ምዝገባ እንደሚጀመር ምክትል ከንቲባው አስታወቁ

መኖሪያ ቤት ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉ ነዋሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የሚገነቡበት ቦታ ያገኛሉ ብለዋል

በ2013 ዓ.ም. ዓብይ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ዋናው በከተማዋ የመሬት ይዞታ ላይ ልዩ ኦዲት ማካሄድና የመሬት ምዝገባ ማከናወን እንደሚሆን፣ የአዲስ ከበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ይፋ አደረጉ።

ምክትል ከንቲባው ይህንን ይፋ ያደረጉት ከሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተካሄደው የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ሰባተኛ ዓመት ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ ትልቅ ሀብት መሬት እንደሆነ የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፣ በሚከናወነው የመሬት ኦዲት ከዚህ ቀደም ያላግባብ የተወሰዱና ለረዥም ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ይዞታዎች እንዲመለሱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በሚደረገው የመሬት ኦዲትና ምዝገባ ተለይተው ለከተማ አስተዳደሩ እንዲመለሱ የሚደረጉት ይዞታዎች፣ ለሌላ ልማት እንደሚውሉ አስታወቀዋል። በኦዲት እንዲመለሱ የሚደረጉት ይዞታዎች፣ በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስረድተዋል።

‹‹የጋራ መኖሪያ ቤት ለማግኘት ተመዝግበው ለበርካታ ዓመታት እየተጠባበቁ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ በማኅበር ተደራጅተው የራሳቸውን የጋራ መኖሪያ ሕንፃ እንዲገነቡ ይደረጋል፤›› ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን የመኖርያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ 125 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፣ እየተገነቡ ከሚገኙት ቤቶች መካከል 96 ሺሕ የሚሆኑት በ28/80 የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ሥር የተያዙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ሁለት ሺሕ ቤቶች ደግሞ በ40/60 የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ሥር የተያዙ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የገጠማቸውን ትልቅ ተግዳሮትም ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዋናነት ከዚህ ቀደም ለተገነቡ ቤቶች የተወሰደ ከፍተኛ የባንክ ብድር አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች የቤት ልማት ፕሮጀክቱን ያጋጠመው ተግዳሮት መሆኑ ተጠቅሷል። የከተማ አስተዳደሩ ኮዬ ፈጬ ተብሎ በሚጠራው የግንባታ ሳይት ላይ በተነሳበት የወሰን ጥያቄ ምክንያት፣ ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ዘጠኝ ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ ከሁለት ዓመታት ገደማ በፊት ዕጣ ቢያወጣም፣ ቤቶቹን እስካሁን ለነዋሪዎች ማስተላለፍ እንዳልቻለ ይታወቃል።

ምክትል ከንቲባው የቤቶች ልማት ፕሮጀክቱ ከባንክ ዕዳ ጋር ተያይዞ የገጠመውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸው፣ ከወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄም ዳግም ችግር በማይፈጥርበት መንገድ ዕልባት እንደሚያገኝ አስታውቀዋል።

በ2013 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ዓብይ ተግባር ይሆናል ባሉት የመሬት ኦዲት ምዝገባ ላይም፣ ለመሬት ወረራ ምክንያት የሆነውን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ለመሬት ወረራ ተጋላጭ ከሆኑት ይዞታዎች መካከል የከተማ አርሶ አደሮች ይዞታ እንደሆነ የተናገሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ፣ በዚህ አካባቢ ሥርዓት ለማበጀትም ለከተማዋ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለ2013 በጀት ዓመት ያቀረበውን 61 ቢሊዮን ብር በጀት ምክር ቤቱ ተቀብሎ አፅድቋል፡፡ ምክትል ከንቲባ ታከለ ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ላከናወኗቸው ስኬታማ ተግባራት የዕውቅና ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል ከንቲባው በተለይ የሚከናወኑ ሥራዎች የከተማዋ ነዋሪዎችን ያማከለ እንዲሆን በማድረግ፣ ውጤታማ ሥራ በማከናወናቸው ሽልማቱን እንደተበረከተላቸው ተገልጿል።

በተለይም አስታዋሽ አጥተው ለዘመናት የተዘነጉ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ማዕከል ያደረጉ ሥራዎችን በመሥራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ፣ በተጨማሪም የከተማዋን ታሪካዊና የቱሪዝም መስህብነት የሚያጎሉ፣ እንዲሁም የነዋሪዎችን ችግር የሚፈቱና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማስጀመራቸው በታሰበላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማስቻላቸው ለዕውቅና ሽልማቱ በምክንያትነት ተጠቁሟል።

በከተማዋ ለሚገኙ ተማሪዎች ምግብ፣ የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም እንዲቀርብ አመራር መስጠታቸው ሥራውንም ተቋማዊ እንዲሆን ማድረጋቸው ተጠቅሷል።

በኢኮኖሚው ዘርፍም የከተማ ግብርና በስፋት በከተማዋ ባህል እንዲሆን ሐሳብ በማመንጨትና አመራር በመስጠት፣ እንዲሁም የዕደ ጥበብ ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው እንዲጨምር እየሠሩ ያሉት ሥራ ስኬታማ መሆናቸው ተወስቷል።(ሪፖርተር ~ ዮሐንስ አንበርብር)

Click to comment

More in ዜና

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • #ድሬደዋ #ድሬደዋ

  ዜና

  #ድሬደዋ

  By

  #ድሬደዋ በድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማያከብሩ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  ዜና

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  By

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር...

 • ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  ዜና

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  By

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top