Connect with us

በአሜሪካ የወያኔ እና የሸኔ  የተቃዉሞ ሰልፍ!

በአሜሪካ የወያኔ እና የሸኔ  የተቃዉሞ ሰልፍ!
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

በአሜሪካ የወያኔ እና የሸኔ  የተቃዉሞ ሰልፍ!

በአሜሪካ የወያኔ እና የሸኔ  የተቃዉሞ ሰልፍ!
(ታዬ ደንደአ)

ከትላንት በስትያ ነበር! ወያኔ እና ሸኔ ባንድራቸዉን አያይዘዉ በአሜሪካ ስያትል ሰልፍ ሲያደርጉ አየን። ነገሩ ህልም ቢመስልም ያዉ ማየት ማመን ነዉ! ወያኔና ሸኔ የኢትዮጵያን መንግስት ለመቃወም በጋራ ተሰልፏል! መፈክራቸዉ “አምባገነኑ የኢትዮጵያ መንግስት ፍትህን እና ህዝብን እያጠፋ ነዉ” ይላል!

ከሰማይ በታችና ከምድር በላይ! ወያኔ እና ኦነግ ሸኔ በጋራ ለፍትህ ሲሰለፉ! ኢ-ፍተሓዊነት እራሱ ቆም ለፍትህ ሲከራከር! መቸም ዘመን የማያሳይ አይኖርም! ወያኔ በኦነግ ሸኔ ስም የፈፀመዉን ወንጀል የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያዉቃል። ኦሮሞ በጅምላ ተገድሏል! ብዙ ሺዎች ያለጥፋት ታስሮ ቤተሰብ ተበትኗል! ሴቶች ተደፍረዉ ወንዶች ተኮላሽቷል! ባለሀብቶች ተዘረፈዉ ተማሪ እና አስተማሪ ተባሯል! የሸኔ አመራርን ጨምሮ በርካቶች ተሰዷል! ታዲያ ገዳይና ሟች፥ አሳሪና ታሳሪ፥ ከሳሽና ተከሳሽ፥ አባራሪና ተባራሪ ሂሳብ ሳያወራርዱ የፈጠሩት ኢ-ፍተሓዊ ጥምረት እንዴት ስለፍትህ ይናገራል? ኦነግ ሸኔ ካሰረዉ እና ካሰደደዉ ወያኔ ጋር ቆሞ ከስደት የመለሰዉን እና ከእስር የፈታዉን አመራር ከመክሰስ በላይስ ፍትህን ማዛባት ከየት ሊመጣ ይችላል? ስለየትኛዉ ፍትህ ይወራል?

አንዳንዴ እኮ የሚባል ነገር ይጠፋል! አሁን ወያኔ “ዴሞክራት” ሆኖ በሰልፍ አባገነንነትን ሲቃወም ምን ይባላል? ምርጫ በወያኔ ለወያኔ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል! ወያኔን ያልደገፈ “አሸባሪ” ተብሎ ወህኒ ይወርዳል ። ከተሳካለት ደግሞ ሀገሩን ጥሎ ይሰደዳል! ለነፃነት የተናገሩ በአደባባይ ሲረሸኑ ከርሟል! ኦነግ ሸኔም ቢሆን በዚህ ረገድ ከንሰሃ አባቱ ወያኔ አይለይም! ዓላማዉን ያልደገፉትን የህዝብ ልጆች ገድሎ አቃጥሏል።

በራሱ አባላት ላይ ሳይቀር አስከፊ ግፍ ፈፅሟል! በሶሎሎ በሺ የሚቆጠሩትን ታጋዮች ገድሎ አዉሬ አስበልቷል! በኤርትራ በረሀም ከኢትዮጵያ ሰራዊት ለቆ የተቀላቀሉትን ገድሎ ቀብሯል! በወለጋ እና በጉጂ የህዝብ ልጆችን ሰቅሎ፣ ገርፎ፣ ገድሎ አቃጥሏል! ይህ ፀረ-ሰዉ ድርጅት በምን ሞራል ስለአምባገነን ይናገራል? መሰንበት ደግ ነዉ ይባላል። ብዙ ነገሮችን በህደት ያሳያል።

ወያኔ እና ሸኔ ለ”ህዝብ” ብለዉ በጋራ “አምባገነንነትን” ሲቃወሙ ከማየት በላይ ግን በዓለም ላይ ምን ተአምር ሊከሰት ይችላል? ዘመኑ 21ኛ ክፍለ ዘመን መሆኑ በጀ! መረጃ በፍጥነት ይዘዋወራል። የአስመሳዮች ትክክለኛ ማንነት በቀላሉ ይጋለጣል! ውሸት እና ውሸታም መንገድ ላይ ይራገፋል። አሸናፊዉ የጠራ እዉነትን ይዞ በመርህ የሚመራ ብቻ ይሆናል!

#ግድቡየኔነዉ
#አረንጓዴአሻራ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top