Connect with us

ግብፅ በሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት

ግብፅ በሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት ኢትዮጵያ በትኩረት እንደምትከታተል አስታወቀች
Photo: Social Media

ዜና

ግብፅ በሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት

ግብፅ የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆነችውና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕጋዊ ዕውቅና ባላገኘችው ሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለመመሥረት እያደረገች ያለውን ጥረት፣ ኢትዮጵያ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን አስታወቀች።

የግብፅ ባለሥልጣናት ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በስፋት ሲያደርጉ እንደነበር፣ ከሳምንት በፊት ከፍተኛ የግብፅ መንግሥት ልዑካን በሶማሌላንድ ከፕሬዚዳንት ሙሳ አብዲ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል።

በዚህ ውይይት ወቅትም የግብፅ መንግሥት በሶማሌላንድ ሰሜን ምዕራብ ቀጣና የጦር ሠፈር ለማቋቋም ያለውን ፍላጎት በመግለጽ፣ ለፕሬዚዳንት ሙሳ አብዲ ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።

ይህንን የግብፅ አዲስ እንቅስቃሴ በተመለከተ የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር)፣ የግብፅ ፍላጎት ምን እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑን አስታውቀዋል።

‹‹ግብፅ በሶማሌላንድ የጀመረችው እንቅስቃሴ ምንም ይሁን ምን፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ላይ አሉታዊ ጉዳት እንደማያስከትል ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ ውጪ ከሆነ ሕጋዊነት አይኖረውም፡፡ ከሆነ ግን ሰብዓዊነትንም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰላምና የደኅንነት መርህን ይቃረናል፤›› ሲሉ ቃል አቀባዩ ለኬንያ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ግብፅ በሶማሌላንድ ምን ለማድረግ እንደፈለገች ኢትዮጵያ በአንክሮ የምትከታተለው እንደሆነ፣ የተጨበጠ መረጃ ላይ በመመሥረትም ኢትዮጵያ አቋሟን እንደምታሳውቅ ገልጸዋል።

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ዲፕሎማት፣ ግብፅ ወደ ሶማሌላንድ ፖለቲካዊ መስፋፋት ለማድረግ የጀመረችው ጥረት አንድምታው ፈርጀ ብዙ እንደሆነ ገልጸዋል።

አንደኛው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ፖለቲካን መረበሽ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በተለይም በሶማሊያ ያላትን የቆየ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ መገዳደር እንደሆነ አስረድተዋል።

ይህ የግብፅ ፖለቲካዊ አካሄድ በሊቢያ የፖለቲካ ጉዳይ የበላይነት እንዳትይዝ ከቱርክና ከሩሲያ የገጠማትን ተግዳሮት፣ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንዲስፋፋ የሚያደርግ አቅም እንዳለውና ውጤቱም ከወዲሁ መታየት መጀመሩን ጠቁመዋል።

በዚህ ሥልት በኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊ ጫና ለማድረስ ግብፅ መፈለጓ ግልጽ ነው ብለው፣ በሊቢያ ፖለቲካ ጉዳይ ፍላጎት ያላቸውን እንደ ሩሲያ፣ ቱርክና ከዚህ በተቃራኒ የቆሙትን አሜሪካና የአውሮፓ ኃያላን ወደ ሶማሌላንድ ሜዳ ለመውሰድ የሸረበችው ሴራ መሆኑን ያብራሩት ዲፕሎማቱ፣ ይህ ጥረቷ ከተሳካም እየተሸነፈችበት ያለውን የህዳሴ ግድብ ወይም የዓባይ ወንዝ የውኃ ፖለቲካ ከሊቢያ ሁኔታ ጋር ተጣምሮ፣ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ስበት ማዕከል የማድረግ አሻጥር በውስጡ እንደሚታይም ገልጸዋል።

ግብፅ ይህንን ሴራ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው የኢጋድ አባል አገሮች፣ አሜሪካና ሌሎች ኃያላን አገሮች በጂቡቲ የሶማሊያና የሶማሌላንድን ፖለቲካዊ አለመግባባት ለመፍታት በተወያዩ ማግሥት መሆኑ ደግሞ፣ ግብፅ ይህ የሰላም ጥረት እንዳይሰምር፣ አካባቢው እንዳይረጋጋና ለፍላጎቷ ምቹ እንዲሆን በሥጋት ላይ እንደሆነች በግልጽ ማሳየቱን አስረድተዋል።

ግብፅ ከሶማሌላንድ በተጨማሪ በፑንትላንድም ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎቿ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መጨመራቸውን የገለጹት ዲፕሎማቱ፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን በፑንትላንድ እየገነባች ወዳጅነቷን ለማጠናከር እየጣረች እንደሆነ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ሞቃዲሾ ለሚገኘው የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት የጦር መሣሪያና የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ሞክራ እንዳልተሳካላት የተናገሩት እኚሁ ዲፕሎማት፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ፎርማጆ የዓረብ ሊግ አባል አገሮች የህዳሴ ግድቡን በመቃወም አቋም ሲይዙ እሳቸው ግን ከዚህ ተቃራኒ መቆማቸው፣ ግብፅ አሁን በአፍሪካ ቀንድ ለምታደርገው እንቅስቃሴ ሌላው ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በሶማሌላንድ የጦር ሠፈር ለማቋቋም ጥረት አድርጋ እንደነበር፣ እንዲሁም የበርበራ ወደብን አልምቶ ለማስተዳደር የ30 ዓመት ኮንትራት ተፈራርማ እይደነበር ይታወሳል።

የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንቅስቃሴውን በመቃወም፣ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር በጥምረት የበርበራ ወደብን ለማልማት ከገባቸው ውል ውስጥ ተከልሶ፣ እንዲሁም የሶማሌላንድ መንግሥት ድርሻ ተቀንሶ ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ 19 በመቶ ድርሻ እንዲሰጣት ተደርጓል።

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በሶማሌላንድ ልትመሠርት የነበረውን የጦር ሠፈር በዚህ ምክንያት የተወች ሲሆን፣ ተለዋጭ ወደብ በኤርትራ ማግኘቷ ሐሳቧን እንድትቀይር ሳያደርጋት እንዳልቀረ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ የልማት ፕሮጀክት ላይ የያዘችው 19 በመቶ ድርሻ አሁንም እንዳለ ሲሆን፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ 51 በመቶ ድርሻም ሆነ የሶማሌላንድ መንግሥት ቀሪ ድርሻ አሁንም እንዳለ ቢሆንም፣ አሁንም ፕሮጀክቱ ፈቀቅ እንዳላለ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የግብፅ ባለሥልጣናት ሶማሌላንድ መመላለሳቸውን በቀጠሉባቸው ያለፉት ሳምንታት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ልዩ መልዕክተኛቸው የሆኑትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ወደ ቱርክ ሲልኩ፣ ባለፈው ሳምንት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴን ወደ ሶማሌላንድ እንደ ላኩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። (ሪፖርተር ~ ዮሐንስ አንበርብር)

Click to comment

More in ዜና

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • #ድሬደዋ #ድሬደዋ

  ዜና

  #ድሬደዋ

  By

  #ድሬደዋ በድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማያከብሩ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  ዜና

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  By

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር...

 • ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  ዜና

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  By

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top