Connect with us

ጠ/ ሚር ዐቢይ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ችግኝ ተከሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ችግኝ ተከሉ
Photo: Facebook

ዜና

ጠ/ ሚር ዐቢይ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ችግኝ ተከሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ጋር በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን በሰመራ ከተማ አኑረዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆንም በአፋር ሰመራ ከተማ በሚገኝ አዲስ ፓርክ ችግኝ ተክለዋል።

በክልሉ ዘንድሮ 1.8 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ ቀጣይ ጉብኝት እና የውይይት መድረክ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።


አሁን የችግኝ የመትከያው ወቅት አጋማሽ ላይ መደረሱ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተከል ከታቀደው 5 ቢሊየን ችግኝ መካከል እስካሁን 2.9 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል።

#EBC

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top