Connect with us

ኢትዮጵያዊነትን ማከም የምንችልበት ጊዜ አሁን ነው

ኢትዮጵያዊነትን ማከም የምንችልበት ጊዜ አሁን ነው
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ኢትዮጵያዊነትን ማከም የምንችልበት ጊዜ አሁን ነው

 

በአገሪቷ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች አሁን ካልታከሙ ኢትዮጵያዊነት የማይድንበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ተገለጸ።

ይህን የገለጹት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ቆይታቸው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት፣ ሠላምና አንድነትን የዳሰሱ ወቅታዊ ጭብጦች ላይ ያተኮረ ሲሆን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘመናት የተገነባ በቀላሉ የማይጠፋ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።

ሌሎች በገንዘብ ኢትዮጵያን አፍርሱ ብለው ጥፋት እንደሰሩ ሁሉ እኛም በእውቀታችን ከሰራን ትውልዱን መመለስና ኢትዮጵያን ማዳን እንችላለን ብለዋል።

የጥንት ኢትዮጵያዊያን የሰሯቸው የአንድነት ታሪኮች ሲዳሰሱ በተለይ በአድዋ ጦርነት ታሪክ የሰሩት በጀግንነት ተግባብተውና በሃገር ፍቅር ስሜት ተሳስረው መሆኑ ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያዊነት ማለት ቅይጥነት፣ አብሮነት፣ ለሌላው መኖርና አዛኝነት፣ አትንኩኝ ባይነትና ጀግንነት ነውብለዋል።

የአሁኑ የመከፋፈልና የልዩነት ታሪክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተሰራ የሴራ ፖለቲካ የመጣ መሆኑንም አብራርተዋል።

በአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የጥቁርን አሸናፊነት በተግባር ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ በሌላ በኩል ከአባይ ወንዝ የባለቤትነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እድገቷን የማይፈልጉ የውጭ ጠላቶች እንዲኖራትም አድርጓታል ሲሉም ገልጸዋል።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዲዳከም በውጭ ጠላትና በሃገር ውስጥ ባንዳዎች ሃይማኖትና ዘርን ትኩረት በማድረግ የመስራት አዝማሚያ ጥንትም የነበረ ነው ይላሉ።

ይሁን እንጂ ይህ ኢትዮጵያዊነትን የማዳከምና ልዩነትን የማስፋት ስራ መንግስታዊ መዋቅር ይዞ ላለፉት ዓመታት ሲሰራ መቆየቱ አሁን ላጋጠመው ችግር ዋነኛ ምክንያት መሆኑም አውስተዋል።

ኢትዮጵያን የሚከፋፍል የጥላቻና የዘር ፖለቲካ የሚያመርቱት የውጭ አካላት ቢሆኑም በሃገር ውስጥ ደግሞ የጉዳዩ አስፈፃሚዎች መኖራቸው ችግሩን የባሰ እንዳደረገው ጠቁመዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በበኩላቸው አሁን በአገሪቷ ያሉት ችግሮች የመነጩት ላለፉት ዓመታት ትውልዱ ስለ አገሩ ታሪክና ማንነት በአግባቡ ስላልተማረ ነው ይላሉ።

መፍትሄው በትውልዱ ላይ መፍረድና በመንግስት ላይ መጠቆም ሳይሆን ሁላችንም ኃላፊነት ወስደን በየሙያችን መስራት ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የጥንት አባቶች ለዘመናት በደማቸው፣ በላባቸው፣ በድካማቸውና በእውቀታቸው የገነቧት በመሆኗ ችግሮች በቀላሉ ገፍተው የሚጥሏት አለመሆኗንም ዲያቆን ዳንኤል አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች አሁን ካልታከሙ ኢትዮጵያዊነት የማይድንበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችልና ሁሉም ለዚህ አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።(ኢዜአ)

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top