Connect with us

የጋሞ ዞን አስጠነቀቀ

የጋሞ ዞን አስጠነቀቀ

ፓለቲካ

የጋሞ ዞን አስጠነቀቀ

የጋሞ ሕዝብ በስነ-ልቦና ከሚቀራረባቸው ህዝቦች ጋር አደረጃጀት መፍጠር ካልቻለ ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ የራሱን ክልል የመመስረት ጥያቄውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጋሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሚገኙ ዞኖች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀው ያንን መሰረት አድርጎ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን አስታውሰዋል፡፡

የክልል ይገባኛል ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ካቀረቡ ዞኖች አንዱ የጋሞ ዞን ነው ያሉት አስተዳዳሪው ጥያቄው ከቀረበ በኋላ ባሉ ሂደቶች ዙሪያ ግልጽነት ለመፍጠር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተግኝቷል ብለዋል፡፡

በሀገር ደረጃ የመጣውን ለውጥ የጋሞ ህዝብ ተቀብሎ ሀገር ወደ ተሻለ ጎዳና እንድትደርስ እስከታችኛው መዋቅር ለውጡን ለማስቀጠል የራሱን ሚና ሲወጣ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

የጋሞ ዞን ለውጡን ተከትሎ የሚመጡ አለመረጋጋቶች ዞኑ ውስጥ እንዳይከሰቱ ከአባቶች፣ ከወጣቶች እንዲሁም ከመንግስት መዋቅሮች ጋር በጋራ በመሆን ተቆጣጥሮ ተሻግሯል፡፡ ከዚህ በኋላም አካባቢው ሰላም እንዲሆን፣ እንደ ሀገር የተጀመሩ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ፣ትልሞችና እቅዶችም ግባቸውን እንዲመቱ የራሱን ድርሻ ለመወጣት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ከለውጡ ጋር ተያይዘው የመጡ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች የጋሞ ህዝብ ዛሬ የጠየቀው አይደለም ያሉት አስተዳዳሪው ከ2 አስርት ዓመታት በፊት ጀምሮ ጋሞ የራሱን ክልል ለማደራጀት መንግስትን ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ ጠቅላይ ግዛት፣ ክፍለ ሀገር ከዚያም ዞን ሆኖ በአብሮነት ከተለያዩ ህዝቦች ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡

በ2011 ዓ.ም ዳግም በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ለክልል ምክር ቤት ያቀረበ ቢሆንም በአንድ አመት ጊዜ ምላሽ አልተሰጠውም ፡፡ በመሆኑም ቅሬታውን ለፌዴሬሽን ምክርቤት ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ የኢፊድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ለሁሉም ዞን የክልል ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ህዝቡን በማወያየት በአንድ የክልል አደረጃጀት ውስጥ መካተት የሚችሉ አከባቢዎችን የመለየት ሁኔታ ቢመቻች በማለት ምከረ ሀሳብ ማቅረቡን አስታውሰዋል፡፡

የጋሞ ህዝብ ምንም እንኳን ጥያቄው የራሱን ክልል የመመስረት ቢሆንም ለሀገር በማሰብ እና በአብሮነት በማመን ከህዝቡ ለመምከር ሀሳቡን መቀበሉንም ተናግረዋል፡፡
እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ በውይይቱም ከነማን ጋር ለመኖር እንደሚፈልግና በስነ-ልቦና አንድ ከሆኑ ህዝቦች ጋር በጋራ ተደራጅቶ ለመኖር እንደሚፈልግ ማሳወቁን ገልጽዋል፡፡ የጋሞ ህዝብ አብሮ በአንድ በመደራጀት ለሀገር ተምሳሌት የሆነ መዋቅር ፈጥረው የነበሩ ህዝቦች ስላሉ ከነሱ ጋር አብሮ መሆን እንደሚፈልግ ማሳወቁንም ገልፀዋል፡፡

ከዚያ ውጪ በተቃራኒው አብሮ መሆን የማይችል አደረጃጀት ለመፍጠር የሚደረግ ግፊት ካለ የጋሞ ህዝብ ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ የራሱን ክልል የመመስረት ጥያቄውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ህዝቡ ድምዳሜ ላይ መድረሱን አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል፡፡

ይህንን አማራጭ ተከትሎ የፌደራል መንግስት ምላሽን መላው የጋሞ ህዝቡ በጉጉት እየተጠባባቀ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
ከአጎራባች ህዝቦች ጋር ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱም ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተዳዳሪው አሳውቀዋል፡፡

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማሻከር እና ህዝብን በተሳሳተ መረጃ ለማደናገር የሚሰሩ ሚዲያዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ያሳሰቡት ምክትል አስተዳዳሪው የፌደራል መንግስትም የተሳሳተ መረጃ ይዘው በሚወጡ ሚዲያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

ከአጎራባች ዞኖች ከሚገኙ ወንድም ህዝቦች ጋር ተቻችለንና ተከባብረን በተለያየ አደረጃጃት ለመኖር እንፈልጋለን ብሎ የጋሞ ህዝብ ሲወስን ከጥላቻ አመለካከት በመነሳት ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበሩ አደረጃጀቶች የህዝቡን ፍላጎት መሠረት ያላደረጉና በፖለቲከኞች ፍላጎት ብቻ ተሞክሮ ያልተሳካ ታሪክ ስላለ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡ የአጎራባች ህዝቦች በክልል የመደራጀት ፍላጎትንም የምንደገፍ መሆኑን እንገልፃለን ብለዋል

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top