Connect with us

የምርጫ ቦርድን የ2013 በጀት ቀንሶ ያቀረበው ገንዘብ ሚኒስቴር አስተካክሎ እንዲያቀርብ ታዘዘ

የምርጫ ቦርድን የ2013 በጀት ቀንሶ ያቀረበው ገንዘብ ሚኒስቴር አስተካክሎ እንዲያቀርብ ታዘዘ
Photo: Social media

ዜና

የምርጫ ቦርድን የ2013 በጀት ቀንሶ ያቀረበው ገንዘብ ሚኒስቴር አስተካክሎ እንዲያቀርብ ታዘዘ

የዲሞክራታይዜሽን ተቋማትን በጀት ተመልክቶ እንዲፀድ የመላክ ስልጣን ያለው የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ለምርጫ ቦርድ መደበኛ በጀት ቦርዱ ጠይቆ ከነበረው ከ 119 ሚሊየን ብር በላይ ቀንሶ 85.1 ሚሊየን ብር እንዲፀድቅ ለገንዘብ ሚኒስቴር ልኮ የነበር ቢሆንም፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር ከሃላፊነቱ ውጭ የቦርዱን የመደበኛ በጀት መጠን እጅግ ቀንሶ ለፓርላማ ማቅረቡ በቋሚ ኮሚቴው አባላት አስተችቶታል፡፡

በሌላ በኩል በአመቱ ለሚደረገው አገራዊ ምርጫ ቦርዱ እንዲፀድቅለት 4.26 ቢሊየን ብር ለቋሚ ኮሚቴው አቅርቦ የነበረ ቢሆንም፤ ከረቂቅ ግምገማው እና በቋሚ ኮሚቴው እና ቦርዱ ሃላፊዎች በተደረገ ውይይት በጀቱ ወደ 4.14 ቢሊየን ብር ዝቅ እንዲል ተደርጎ በ2013 በጀት ረቂቅ ውስጥ እንዲካተት ለገንዘብ ሚኒስቴር ቢላክም፡፡

ሚኒስቴር ተቋሙ ለምርጫ ማስፈፀሚያ ለቦርዱ ባለፈው አመት ተመድቦለት ሆኖም በኮሮና ምክንያት ምርጫው መደረግ ባለመቻሉ ያልተጠቀመበትን በጀት ማለትም 2.4 ቢሊየን ብር ሊጠቀም እንደሚችል አቅርቦ ነበር፡፡

ይህም የምክር ቤቱን ስልጣን የተጋፋ እና የወቅቱን የዋጋ ልዩነት እና ንረት ከግምት ያላስገባ ነው ብለውታል ስለጉዳዩ ካፒታል ያናገራቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት፡፡

በመሆኑም ገንዘብ ሚኒስቴር የቀረበለትን በጀት መሰረት በማድረግ አስተካክሎ እንዲያቀርብ ታዟል፡፡
ከሌሎች ባለ በጀት መስሪያቤቶች በተለየ ምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ግንባታ ተቋማት የሚባሉትን እንደ ፍርድ ቤት፣ የሰባዊ መብት ኮሚሽን፣ ዋና ኦዲተር፣ እንባ ጠባቂ፣ እና ምርጫ ቦርድ በጀቶችን አይቶ በበጀት እንዲካተት ሃላፊነት አለበት፡፡

(ካፒታል ጋዜጣ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top