Connect with us

አምባሳደር የሀገሩ ገበና ሸፋኝ እንጂ የእናት ሀገሩን ቀሚስ ገልቦ እርቃን ላዋርድ ባይ አይደለም

አምባሳደር የሀገሩ ገበና ሸፋኝ እንጂ የእናት ሀገሩን ቀሚስ ገልቦ እርቃን ላዋርድ ባይ አይደለም
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

አምባሳደር የሀገሩ ገበና ሸፋኝ እንጂ የእናት ሀገሩን ቀሚስ ገልቦ እርቃን ላዋርድ ባይ አይደለም

አምባሳደር የሀገሩ ገበና ሸፋኝ እንጂ የእናት ሀገሩን ቀሚስ ገልቦ እርቃን ላዋርድ ባይ አይደለም፡፡
አምባሳደር ግን የዐፄ ምኒልክ ውል ለግብጽ የወገን ነው የሚል ምስክርነት ለመስጠት በመሞከር ከግብጽ ጋር ለመቆም በአደባባይ ጽፈዋል፡፡
******
ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ኢትዮጵያ ከመቼውም ግዜ በላይ ጠንካራ ዲፕሎማት የምትፈልግበት ወቅት ላይ ደርሳለች፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አምባሳደሮች በሰው ሀገር ተጧሪ ከመሆን ያለፈ ሀገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ስራ ሲሰሩ አይታይም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚሄዱበት መንፈስ መሄድ የቻሉ አምባሳደሮች ጥቂት ናቸው፡፡ እንደ አምባሳደር መለስ አለም ያሉት ምን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ የኬኒያን ዕለታዊ ጋዜጦች ማንበብ ወይም የናይሮቢን የሀገር ልጅ መጠየቅ በቂ ነው፡፡

በሀገር ሀብት ሀገርን ወክለው ሄደው እምነታቸው አልያም ጎጣቸው ጠልፎ የሚጥላቸው ብዙ ናቸው፡፡ ማተብ ካሰረ ኢምባሲው ቤተስኪያን እንዲሆንለት ከሰለመ ደግሞ መስጂድ ሊያደርገው የሚፈልግ ብዙ ነው፡፡ ከጰነጠጠም እንጸልይበት ይላል፡፡

በሌላ በኩል አምባሳደር ተብሎ ሙሉ የሀገር ክብር ተሸክሞ ይሄድና እዚያ ግን ከቀበሌው ያላላፈ በዘር በሽታ የተለከፈ ሰው ሆኖ ያርፋል፡፡ ሰሞኑን አንዱ አምባሳደር በዳግማዊ ምኒልክ ጉዳይ የሰጡት አስተያየት የሀገር ክብር እና የአምባሳደርነት ትርጉምን እንዴት እንዳዮት አሳይቶናል፡፡

በዚህ ጽሑፍ ለምን ዐፄ ምኒልክ በሀገራቸው አምባሳደር ተነቀፉ ብዬ አልሟገትም፡፡ ዐፄ ምኒልክ ድፍን የጥቁር ሀገር አምባሳደር ሁሉ ወኪላቸው ነው፡፡ በደቡብ አፍሪቃ፣ በኬኒያ፣ በማሊ፣ በጋና፣ በጃማይካ፣ በብራዚል፣ ብቻ በብዙ የዓለም ሀገር አምባሳደር ክብራቸው ከፍ ብሎ የሚመሰከርላቸው ንጉሥ በጥላቻ የሰከረ ምንም ቢል የስካር ደረጃውን ቢያሳይ እንጂ ከንጉሡ ክብር አንዳች አያጎድልም፡፡

ግን አምባሳደርነት ምንድነው? የወረዳ ወኪልነት? የብሔር ፊት አውራሪነት? የጎጥ አሳላፊነት? ብዙ ሀገር ከእኛ በከፋ የታሪክ ልዩነት፣ ከእኛ በሰፋ የውስጥ ሽኩቻ ይታመሳል፡፡ አንድም አምባሳደር የዓለም ህዝብ የተቀበለውን የራሱን ታሪክ ያጎደፈ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡

አንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስለ ግብጽና የአጼ ምኒልክ የአባይ ስምምነት ሲገልጹ ግብጾች ብልጥ ለመሆን ሞከሩ እንጂ አልተሳካላቸውም ነበር ያሉት፡፡ አሁን አንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግን የዐፄ ምኒልክ ውል ለግብጽ የወገን ነው የሚል ምስክርነት ለመስጠት በመሞከር ከግብጽ ጋር ለመቆም በአደባባይ ጽፈዋል፡፡ አምባሳደሩ የፖለቲካ ጥላቻ አልያም የታሪክ እውቀት እጥረት ወይም ሌላ የራሳቸው ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ግን የሀገር ብሔራዊ ጥቅም በሚያሳጣ መልኩ የራስን ስሜት ለመግለጽ ብቻ ራስ ጎል ላይ ኳስ አይመታም፡፡

መንግስት ሃላፊነት አለበት፡፡ ብሔራዊ ክብር የሚገባቸው ሰዎችን እንዲህ ባለው የአምባሳደርነት ሙያ ሊመድብ ይገባል፡፡ አምባሳደርነት ሀገር ሆኖ መገኘት ነው፡፡ ሰፈር መሆን የፈለገውን በሰፈሩ ብዙ ስፍራ ስላለ አምጥቶ እዚህ የተጨማለ ፖለቲካ ውስጥ መመደብ ይቻላል፡፡ ቢያንስ ለሀገር ክብር መሪውን የሚመጥን አምባሳደር መሾም አንድ ነገር ነውና መንግስት ደጋግሞ ያስብበት፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top