Connect with us

ፈረስ የኢቢሲያዎች ታሪክ፣ የጦርነት አጋር፣ የክብር ምልክት፣ የሀቲት ማቆሚያ

ፈረስ የኢቢሲያዎች ታሪክ፣ የጦርነት አጋር፣ የክብር ምልክት፣ የሀቲት ማቆሚያ

ባህልና ታሪክ

ፈረስ የኢቢሲያዎች ታሪክ፣ የጦርነት አጋር፣ የክብር ምልክት፣ የሀቲት ማቆሚያ

ፈረስ የኢቢሲያዎች ታሪክ፣ የጦርነት አጋር፣ የክብር ምልክት፣ የሀቲት ማቆሚያ፡፡
******
(ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ)

አንዳንድ ታሪኮች ምክንያት ፈልገን ደጋግመን ብናነሳቸው ሸጋ ነው፡፡ አንዳንድ እውነቶች ስላልተነገሩ አንዳንድ ሀሰቶች በሰፈሩ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለታቸው አይቀርምና፡፡ አቢሲኒያ ለፈረስ ሩቅ የምትመስለው ከታሪክ የራቀ ብዙ ሰው ይኖራል፤ ምክንያት ፈልገን አቢሲኒያን ከፈረስ ያዛመደ ታሪክ በወፍ በረር እንቃኛለን፡፡

እርግጥ ነው የአቢሲኒያ ነገሥታት ከፈረስ ያላቸው ቁርኝት መንፈሳዊም መነሻ አለው፡፡ ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ የድል አድራጊነቱ ምልክት መኾኑ ከዚያ በኋላ የጊዮርጊስን ታቦት ጭምር ይዞ ወደ ጦርነት የመጓዝ እና በእሱ እርዳታ ድል ይኾናል ብሎ የማመን መንፈስ ናኝቷል፡፡

አብልጦ ነገሥታቱን ከፈረስ ያዋደደ የሚባለው ግን ሰማዕቱ መርቆሪዎስ ነው፡፡ እሱ ፈረሰኛና በጦርነት ድል አድራጊ የኾነ ብርቱ የጦር አዛዥ ነበር፡፡ ይኽንን ሰማዕት የሚገልጸው ቅዱስ ሥዕል በአክሱም አካባቢ ኢየሱስ ገዳም ግድግዳ ላይ ከነፈረሱ በክብር ተቀምጧል፡፡ መርቆሪዎስ ፈረሰኛው በብዙ ቀደምት የአቢሲኒያ ወታደሮች ልዩ ስፍራ አለው፡፡ ለዚህ ነው በአቢሲኒያውያን ቀደምትና አንዷ ከተማ በሠይፈ አርዕድ መናገሻ በፋርጣ በየዓመቱ የመርቆሪዎስ በዓል በጥር ሲነግስ በፈረስ ጉግስ የሚደምቀው፡፡ የእስቴና የአጅባር ሜዳ የፈረስ ጉግስ ንግሥ በዓላት ረዥም ዘመን ያስቆጠረው የአቢሲያውያንና የፈረስ ቁርኝት አንድ ማሳያ ነው፡፡

ፈረስን ከአቢሲኒያውያን ጋር ስናነሳው በምድሩ ጠንካራ ሀቲት ላይ የተገነባ መሳሪያ መኾኑን ለመመልከት የአስረኛው ክፍለ ዘመኗን ዮዲት ጉዲት በተመለከተ የተሳሉ ቀደምት ሥዕሎች ዮዲት በፈረስ ኾና ስታዋጋ ያሳየናል፡፡

እርግጥ ዛጉኤዎቹም ቢኾኑ ከፈረስ የተቆራኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በ15ኛው ክፍለ ዘመን ብራና ላይ የተሳለ አንድ የቅዱስ ላሊበላ ምስል የተሸለመ ፈረስ ሲጋልብ ያሳየናል፡፡ በተመሳሳይ በናኩቶ ለአብ ቤተክርስቲያን የሚገኘው ንጉሥ ነአኩቶ ለአብን የሚያሳየው ሥዕልም እንዲሁ በፈረስ ታጅቦ ሲጓዝ ይገልጻል፡፡

ዛጉኤን ከፈረስ ስለመተሳሰሩ ገለጽን እንጂ አክሱማዊው ካሌብን ከሚገልጹት ቀደምት የብራና ሥዕሎች አንዱ በተሸለመ ፈረስ ተቀምጦ በነብር ታጅቦ የሚያሳየው ሥዕል ነው፡፡

ፍራንሲስ አልቫሬዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅት ያተመለከተውን በጻፈበት መጽሐፍ ኖቬምበር በገባ በአስራ አምስተኛው ቀን ሆነ ያለውን ሲገልጽ “ንጉሠ ነገሥቱ ለልዩ መልዕክተኛው ለማሳየት በሙሉ ሽልማት ያጌጠ ፈረስ ልኮ ይኽንን የመሰለ የጦር መሳሪያ በፖርቹጋል መገኘቱን ጠየቀ፡፡ የፈረሱ ጌጥ መጣብር ነበር፡፡” ይለናል፡፡ አልቫሬዝ ንጉሠ ነገሥቱ በሚጓዝበት ጊዜ የሚከተውልን ህዝብና የፈረሰኛና የእግረኛ ብዛት የጻፈልን እማኝ ነው፡፡

ቀደምት አቢሲኒያውያን ከተማ እንኳን ሲመሰርቱ ከፈረስ ጋር አቆራኝተው ነው፡፡ ለምሳሌ የዐፄ ሱስኒዮስ ዜና መዋዕል ጸሐፊ “ሰፊና ቀና ሜዳ ያላት ለፈረስ መግሪያ ግልቢያና ለእንስሳት ግጦሽ ትመቻለችና ይህቺ ሀገር ትሻለኛለች ብሎ በዚያ ከተመ፡፡” ሲል ይነግረናል፡፡

አቢሲኒያውያን ለፈረስ መካነ መቃብር በማቆም ብቻ ሳይኾን ያቆሙት መካነ መቃብር ቅርስ ሆኖ በዓለም ዘንድ የተመዘገበላቸው ናቸው፡፡ በወርቃማው የጎንደር ዘመን ለዐፄ ፋሲል ፈረስ ለዞብል የተሰራው መቃብር ዛሬ የዓለም ቅርስ አካል ነው፡፡

በእርግጥ በዚያው በጎንደር ዘመን የተሰራና በተመሳሳይ በአፍሪቃ በልዩነት የሚገለጸው የዓለም ቅርስ አካል አንዱ አሻራ የአፄ በካፋ የፈረስ ማቆሚያ ፓርኪንግ ነው፡፡ በዘመነ መሳፍንት የመጣው ናትናኤል ፒርስ የዘመነ መሳፍንቱ ታላቅ መስፍን ራስ ወልደ ስላሴ በዛሬዋ ትግራይ አራማት ላይ ስለተቀላቀላቸው አንድ ሺህ ፈረሰኛ ሠራዊት ጽፎልናል፡፡

አርኖ ሚሼል ዲባዲ ከሸዋ ሳህለ ስላሴ የላኩለትን በቅሎ ብቻ አይደለም የሚነግረን በጎንደር ስለነበረው ደማቅ የደብረ ታቦር የፈረስ ጉግስ ጨዋታ የተመለከተውን አሳይቶናል፡፡ የደጃች ጎሹን ፈረሰኞች ተርኮልናል፡፡ የአቢሲኒያዎቹን የጦር አሰላለፍ ሲነግረን ደግሞ ግንባር ቀደም ተሰላፊዎቹ ፈረሰኞቹ እንደሆኑ ደንቡን አኑሮልናል፡፡

የሄነሪ ሳልት፣ የጀምስ ብሩስ፣ የሀሪስ እያልን ከዘረዘርን አቢሲኒያውያንንና ፈረስን ተርከን አናበቃም፡፡ ከዚያ ይልቅ የሚሻለው በአቢሲኒያ ምድር የሚነገረውን አንድ አፈ ታሪክ አካፍዬችሁ ላብቃ፡፡ ፈረስን ከአህያ በማዳቀል በቅሎን የፈጠራት አዊ ነው ይባላል፡፡ ዛሬ ሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማህበር ሰማኒያ አመቱን ያስቆጠረ አመታዊ የፈረስ ትርዒት የሚያካሂድ ብቸኛው አፍሪቃዊ የፈረስ አፍቃሪ ነው፡፡ ጥር ሲመጣ ቀጠሯችሁ አዊ ይሁን፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top