Connect with us

ጃዋር ከአባይ ሚዲያ ጋር ስላደረገው ቃለ-መጠይቅ በወፍ በረር!

ጃዋር ከአባይ ሚዲያ ጋር ስላደረገው ቃለ-መጠይቅ በወፍ በረር!

ፓለቲካ

ጃዋር ከአባይ ሚዲያ ጋር ስላደረገው ቃለ-መጠይቅ በወፍ በረር!

ጃዋር ከአባይ ሚዲያ ጋር ስላደረገው ቃለ-መጠይቅ በወፍ በረር!

1ኛ) ስለሞቱ ሰዎች አልጸጸትም

የ86 ሰዎች ሞት “ምነው ባልሆነ ኖሮ” ብዬ አልጸጸትም አለ። ይህ ከጃዋር የሚጠበቅ ፖለቲካዊ አቋም ቢሆንም ግን እንደ ማህበረሰብ እጅግ አስደንጋጭና አሳሳቢ ነው። እንኳን በአንድ ሰው የመደነባበርና የመደንገጥ ጩሀት ሳቢያ ደጋፊዎቹ ያለምንም መረጃ ብድግ ብለው 86 ሰው እምሽክ አድርገው ይቅርና እንደ ሀገር ጦርነት ውስጥ ገብተን ስለገደልናቸው ወታደሮች እንኳ ዞር ብለን ስናስበው ያመናል፣ ይጸጽተናል፣ ባልሆነ ኖሮ፣ “I am sorry this happened, በመሆኑ አዝናለሁ፣ አልፎ ሳስበው ይጸጽተኛል” ማለት እጅግ ሰባዊነት ነው።

ኤርትራና ኢትዮጵያ ዛሬ አልፎ ሲያዩት እጅግ ስህተት እንደነበረ ተረድተው እንደ ተጸጸቱ ገልጸዋል። የጃዋርን “በ86 ሰዎች ሞት” ምንም አይጸጽተኝም ንግግር በሚዲያ ማሰራጨት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ይህን የሚሰሙ ተከታዮቹ፣ ወጣት ዜጎች፣ ተመሳሳይ ፖለቲከኞች ለሚገድሏቸው፣ ለሚያስገድሏቸው፣ እንዲሁ በፖለቲካ ግርግር ህይወታቸው ለሚጠፋ ንጹሀን ዜጎች “አይጸጽተኝም” የሚለው ንግግር ሰብአዊነትን የሚያዋርድ፣ ትክክል ያልሆነ ምሳሌነት ነው።

በሰዎች ሞት አልጸጸትም ንግግር ከመረጃነቱ ይልቅ የሞራል ጥያቄ በመሆኑ ወይ ቀድሞም መጠየቅ አልነበረበትም ተጠይቆ ምላሹ “ጤናማ ማህበረሰባዊ አቅራቦት” እንደሌለው ሲታወቅ ተቆርጦ መጣል ነበረበት! ከሁሉ በላይ ደግሞ ጉዳዩ ከዛሬ ነገ ወደ ህግ አግባብ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ እንደመሆኑ የሞራል ጥያቄውን ወደ ጎን ትቶ ምርመራዊ ጥያቄኦች ላይ ማተኮር ይገባ ነበር።

2ኛ) ትከሻ አልተለካካሁም

ጃዋር ባንተና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ባለ የትከሻ መለካካት እስከ መቼ ኦሮሚያ ውስጥ ውጥረት ይፈጠራል? ለሚለው ጥያቄ “ትግል እያካሄድኩ እንጂ ትከሻ እየተለካካሁ አይደለም” ሲል መልሷል። አልተሞገተም። እንዲሁ ታልፏል።

ጃዋር ከአብይ ጋር ትከሻ ሲለካካ ሁለት አመት አለፈው። ገና የኦህዴድ ሊቀመንበርነቱን ሲረከብ ነበር ጃዋር ትከሻውን ከአብይ በላይ አድርጎ ማሳየት የጀመረው። ከትከሻ መለካትም በላይ በተደጋጋሚ በግለሰቡ ማንነት ላይ አፍ እላፊ ሲናገር እንደነበረ ይታወቃል። ይህ ሁሉ ቢቀር እንኳ “ሁለት መንግስት አለ” ሲል የተናገረውን መሰረታዊ ጥያቄ ማንሳት በቂ ነበር።

በምንም አይነት ሳይንስ በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት መንግስት ሊኖር አይችልም። ጃዋር ግን የቄሮ ክንፉን በመመካት ያሻውን ማድረግ የሚችልና እንድያውም በተለይ በኦሮሚያ ክልል “መንግስት ነኝ” በሚል አካሄድ አብይ የጃዋርን ያህል ተጽኖ ፈጣሪ እንዳልሆነ ለማሳየት ሞክሯል። ይህ አባባሉ ምን ያህል ተቀባይነት ኖሮት በክልሉ ችግር ሲፈጥር እንደነበረም የታየ ነው።

3) የሚዲያ ክፍተት

ከጃዋር/ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ጋር ቃለ-መጠይቅ የሚያደርጉ ሰዎች አንድ ጠንካራ ጥያቄ ከወረወሩ በኋላ መለስ የሚሉት ነገር፣ ወዲያው ተከታይ ጥያቄ (Followup questions) ለመጠየቅ አለመቻል ለብዙዎቹ የማርያም መንገድ እየሆነ፣ ጉዳዮቹ ተድበስበው ሲታለፉ ማየት የተለመደ ሆኗል። ይህ መታረም አለበት። መሰረታዊ ጥያቄዎችን ብቻ ሳይሆን ሀሳቦችን ሰብስቦ መሄድና ሰውዬውን ኢንተርፕሬት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ያለዝያ የማርያም መንገድ በመስጠት ቀላል ፖለቲካዊ አመኔታ እንዲያገኙ መረማመጃ መሆን ይመጣል።

(የትነበርክ ታደለ)

Continue Reading
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top