Connect with us

የሰሜንና ደቡብ ኦሞ ሕዝቦች መሻት የአንድ ታላቅ ኦሞ ህዝብ ክልል ባለቤትነት?

የሰሜንና ደቡብ ኦሞ ሕዝቦች መሻት የአንድ ታላቅ ኦሞ ህዝብ ክልል ባለቤትነት?
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የሰሜንና ደቡብ ኦሞ ሕዝቦች መሻት የአንድ ታላቅ ኦሞ ህዝብ ክልል ባለቤትነት?

የሰሜንና ደቡብ ኦሞ ሕዝቦች መሻት የአንድ ታላቅ ኦሞ ህዝብ ክልል ባለቤትነት? ወይስ የተበጣጠቀ ትንንሽ ክልሎች ማየት?

ኦሞቲኮችን ግዙፍ ክልል ከመሆን የሚያግዳቸው ችግር ምንድን ነው?

የደቡብ ክልል አዲሱ የክልልነት አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ዕይታዎችን እያስቀመጥን ነው፡፡ ክልሉ በተጨማሪ ክልሎች ሲዋቀር ታሳቢ ከሚደረገው ቀጠና አንዱ የኦሞቲክ አካባቢ ሲሆን በዚህ ቀጠና በዋናነት ዎላይታ አስቀድሞ የክልልነት ጥያቄን አቅርቧል፡፡ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ዳውሮም እንዲሁ የክልል ይገባኛል ጥያቄውን በምክር ቤታቸው በሙሉ ድምጽ ያጸደቁ ናቸው፡፡

አስቀድሞ የተሞከረው ወጋጎዳ በወቅቱ የፈጠረው ፖለቲካዊ ኪሳራ ቀውስና ዛሬም ድረስ አብሮ በመሆን ላይ ስጋት የፈጠረ መንፈስ ቀጠናውን በቀላሉ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዳይወሰንበት አድርጓል፡፡ የቀደመው ሥርዓት ካድሬዎች የህዝብ ንቀትና ጥላቻም ቢሆን አንድ የሚባሉ ወንድማማች ህዝቦች ፖለቲካዊ ሽኩቻ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል፡፡

1.5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ ይዞ በርካታ ወረዳዎች እያሉት የጎፋ ህዝብ ሃያ ሰባት አመታትን በዞን መዋቅር ለመደራጀት መፈለጉ እንደወንጀል ተቆጥሮ በልማት ወደ ኋላ እንዲቀር ተፈርዶበታል፡፡ አስቀድሞ የተሰጣቸው የልዩ ወረዳነት መዋቅር በአንድ ጀምበር ዛሬ የት እንደገቡ በማይታወቁ አረመኔ ካድሬዎች እንዲፈርስና ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ተብለው ያለ ጥናት እንዲዋቀሩ የተረጉት አካባቢዎችም ውሎ አድሮ ያገነገነው ቁርሾ በአሳዛኝ ሁኔታ በትኗቸዋል፡፡

የሰገን አካባቢ ህዝቦች መፈራረስ እንደ ቀላል እውን የሆነ ጉዳይ አይደለም፡፡ ኮንሶን የሚያክል ታታሪ ህዝብ ለአራት አመት ስራውን እንዳይሰራ የፈረደበት ክስተትን አስተናግዷል፡፡ መዋቅር ፈርሶ ያለ መንግስት ሦስት አመት እንዲኖር አድርጓል፡፡

የደቡብ ኦሞዎቹ ፈርጦች የደቡብ ፖለቲካ ገሸሽ አድርጓቸው ኖሯል፡፡ ምስላቸው ለፖስተር ስማቸው ለቱሪዝም ከመፈለግ በስተቀረ በክልሉ ፖለቲካ ውስጥ ሚና አልነበራቸውም፡፡ በልማት የተፈጸመባቸውን በደል በአልተበረዘው ባህላቸው ይቀር ብለው ሁሉን ረስተዋል፡፡

ሰሜንና ደቡባዊ የኦሞ አካባቢዎች ፖለቲካው ሊያጫርሳቸው፣ ሊያለያያቸውና ሊያጠፋፋቸው ቢሞክርም ባህል ታድጓቸዋል፡፡ ሰው መሆን በክብር አስተሳስሯቸዋል፡፡

በቀጠናው ካድሬ እንጂ የብሔር በዳይ የለውም፡፡ ጋሞ ሲሰቃይ ኖሯል፤ ጎፋ ያልተነፈገው ነገር የለም፤ ዎላይታ ብዙ መከራዎች ገጥመውታል፣ ዳውሮ ልማት ተነፍጓል፣ ደቡብ ኦሞዎቹ ያገኙት ምንም ነገር የለም፤ ኮንሶዎች ሁሉን ነገር እንዲያጡ ተፈርዶባቸዋል፤ ጋርዶላዎች የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ ተርፏል፣ ባስኬቶ ማንም የማያነሳው ባዕድ ተደርጎ ታይቷል፣ ኮንታዎች ሁሉ እያላቸው ደቡብ ፖለቲካ ዳር የገፋቸው ናቸው፣ አማሮዎች ሞት እንደ ስጦታ ተለግሰዋል፡፡

ኮሬዎች በሀገራቸው ሁሉን ተነፍገዋል፣ ኦይዳ ዘይሴ እያልን ከቆጠርን የቀጠናው ፖለቲካ መራር ነው፡፡
አሁን ሁለት ፍላጎት አለ፡፡ የቀድሞውን ስሜት መልሶ በመሳሰብ ኦሞዊ አንድነት አያሻኝም የሚልና የለም ኦሞዊ ህብረታችን አዋጪ ነው ብሎ ያሰላ፡፡ እርግጥ ደቡባዊና ሰሜናዊ የኦሞ አካባቢዎች ኦማዎ ክልል ለመመስረት ከበቁና የጋራ አንድነታቸውን እውን ካደረጉ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል ቀጥሎ የትልቁ የኢትዮጵያ ክልል ባለቤትነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ይህ ግን አሁንም ነገም የሚገጠም ፈተና እንዳለ ሳንዘነጋ ነው፡፡ ለምሳሌ የክልሉ መዲና የት ይሆናል የሚለውን? የቀጠናውን ጤናማነት ለማስጠበቅ ሶዶንም፣ ሳውላንም፣ ጎፋንም ጅንካንም መዲና አድርጎ መጠቀም ይቻላል፡፡
ቢሮዎችን በአንድ ስፍራ የመሰብሰቡና ሀብትን አንድ ከተማ የማፍሰሱ ጠባይ ካለፈው ስህተት አንጻር ካልታረመ አብሮ ክልል ሆኖ ከርሞ ነገ ልሂድ ቢልስ የሚለው ስጋት መቅረፊያ አይኖረውም፡፡ እናም ኦሞቲኮች ኩሽ አቅፈው ክልል ከመሆን የሚያግዳቸውን ምክንያት ቁጭ ብሎ መቁጠሩና ቀርፎ መጣመሩ ምትክ የለውም፡፡

ብዙ ትንንሽ ክልል መሆን ባያዋጣም ሳይፈልጉ መዋህድም ሌላ የልማት አበሳ፣ የሰላም ጠር፣ ህዝቦች አንድነት መቀስ እንደሆነ ሊታሰብ ይገባል፡፡ እንቆቅልሽ ነው፤ ኦሞቲክና መጪው ጊዜ ….

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top