Connect with us

የደቡብ ክልል አዲስ አደረጃጀት አዳዲስ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል

የደቡብ ክልል አዲስ አደረጃጀት አዳዲስ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል

ፓለቲካ

የደቡብ ክልል አዲስ አደረጃጀት አዳዲስ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል

የደቡብ ክልል አዲስ አደረጃጀት አዳዲስ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል፡፡
ጋሞ የጎረቤቶቻቸውን ቀልብ ለአብሮነት ስበዋል፡፡
አርባ ምንጭ በአዲስ የተስፋ ጎዳና ላይ ትሆን?
******
(ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ)

ሃምሳ ስድስት ክልል የመሆን ጥያቄ የታየበት የደቡብ ክልል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም በሆደ ሰፊነት ተቀብለው ምከሩበት ባሉት መሰረት ሲመከር ሰንብቷል፡፡ አጥኚ ቡድን ተቋቁሟል፡፡ ያ እያንዳንዱ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄው ውሎ አድሮ በህብረት ወደ መጋመድ እሳቤ መምጣቱ እየታየ ነው፡፡

ደቡብን ከአንድ እስከ አምስት ክልሎች ዳግም ለማደራጀት የቀረበው ምክረ ሀሳብ የሲዳማን ክልል የመሆን የአርነት ሀሳብ አልነካውም፡፡ ሲዳማ ከሪፈረንደሙም በፊት ክልል መሆንን ይሻ ነበር፡፡ ሪፈረንደሙም ይሔንን አረጋግጦለታል፡፡ ከሪፈረንደሙ በኋላ አጥኚ የተባለው ቡድንም ቢሆን ይሄንን አክብሯል፡፡

ደቡብን አምስት ይደርሳሉ በሚባሉ ክልሎች ዳግም የማዋቀሩ ሀሳብ አሁን ደግሞ አዳዲስ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል፡፡ ክልል እሆናለሁ የሚለውን ጥያቄ ያህል ክልል እንሁን በሚለው የጋራ መሰባሰብ ውስጥ ከእከሌ ጋር ሳይሆን ከእከሌ ጋር ነው ክልል መሆን ያለብኝ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው፡፡

አንዳንዶች ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ የሄዱበት አግባብ አስታራቂ የሚመስል ይዘት አለው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ጎፋዎች የቀድሞውን የኦሞቲክ ክልል እውን መሆንና ጠንካራ የክልል ባለቤትነትን አይቃወሙትም፡፡ በጉዳዮ ላይ ተወካዮች ባደረጉት ስምምነትም የመጀመሪያ ምርጫቸው ይሄ ሆኗል፡፡ ግን ሳውላ የክልሉ መዲና ሆና የሚለውን አስምረውበታል፡፡

የጎፋዎች ሁለተኛ ምርጫ የተባለው ከመጀመሪያው ምርጫ ዎላይታ ራሱን ችሎ የሚደራጅበት ሁኔታ ካለው ከቀሪው የኦሞቲክ ክፍል ጋር ክልል ሆኖ መደራጀት ሲሆን ያም ቢሆን አሁንም ማዕከል የምትሆነው ሳውላ ናትና ሳውላ መዲና ከሆነች የሚለው ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ዳውሮዎች የምዕራብ ኢትዮጵያን አካልነት የመረጡ ይመስላል፡፡ የዳውሮ አባቶችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካወያዩና ከዳውሮ ዞን ተወካዮች ጋር ከመከሩ በኋላ ፍላጎቱ ምን ድረስ ነው የሚለው ቢታወቅም አሁን ባለው ድባብ ግን ዳውሮዎች ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደቡብ ክፍል ልባቸው አመዝኗል፡፡ ኮንታ ክልል አቋርጠው ይመጣሉ ወይስ እነሱም ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ልባቸውን ይሰዳሉ? ይሔ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ሁኔታም የሚወስነው ይመስላል፤

ቡርጂና አማሮ መዲናችን አርባ ምንጭ ናት ያሉ ይመስላሉ፡፡ በምክር ቤቶቻቸው ሳይቀር ይሄንን ፍላጎት አንጸባርቀዋል፡፡ ጋሞዎች የጎረቤቶቻቸውን ልብ ማርከዋል፡፡ ብዙዎቹ ኦሞቲኮች ከጋሞ ጋር መደራጀትን ወደውታል፡፡ ይህ ለዘመናት መከራና ስቃይ ሲያስተናግድ የነበረው የጋሞ ህዝብ የጨለማ ምዕራፍ ማብቂያ ይመስላል፡፡

አርባ ምንጭ የጋርዱላዎች መዲና ናት፤ አርባ ምንጭ የጎፋዎች ናት፡፡ አርባ ምንጭ የኮንሶዎች፣ የቡርጂዎች የአማሮዎች፣ የጋርዱላዎች፣ የደቡብ ኦሞዎች ናት፡፡ አርባ ምንጭ አዲስ ተስፋ ላይ ትሆን? ውቧ ከተማ ውብ የክልል መዲና የምትባልበት ቀን ቀርቦ ይሆን?
ይቀጥላል…..

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top