Connect with us

በኢትዮጵያ በኮሮና ወረርሽኝ ከ26ሺ በላይ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ

በኢትዮጵያ እስከ መጪው ህዳር ወር በኮሮና ወረርሽኝ ከ26ሺ በላይ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ
Photo: Social media

ዜና

በኢትዮጵያ በኮሮና ወረርሽኝ ከ26ሺ በላይ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ

በኢትዮጵያ እስከ መጪው ህዳር ወር በኮሮና ወረርሽኝ ከ26ሺ በላይ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ

~ ከ8 ነጥብ 5 ሚልየን በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙ ተገምቷል፣

በአገራችን የኮቪድ – 19 ወረርሺኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው በመጪው ህዳር ወር ላይ እንደሚሆን የተጠቆመ ሲሆን ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙና ከ26ሺ በላይ የሚሆኑ በቫይረሱ ህይወታቸውን እንደሚያጡ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው፤ የኮቪድ 19 ጥናቱ ያመለክታል፡፡

ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርስበት ጊዜ ሰኔ ወር መጀመሪያ ገደማ መሆኑ ቀርቶ ወደ መጪው ህዳር ወር 2012 ዓ.ም መገፋቱ ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ መሠረትም ህዳር ወር 2013 መጀመሪያ አካባቢ 8 ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ አንድ ሺ አስራ አንድ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሲሆን፤ በዚሁ ወር አጋማሽ ላይ የሟቾች ቁጥር 26ሺ አምስት መቶ አርባ አራት እንደሚደርስ ጠቁሟል፡፡

የቫይረሱ ስርጭትና የሞት መጠን በምስራቅ አፍሪካ አገራት በፍጥነት እየጨመረ፣ ያመላከተው መረጃው፤ በኢትዮጵያ በሳምንቱ የበሽታው የስርጭት መጠን በ78 በመቶ የሞት ምጣኔው ደግሞ በ61 በመቶ ጨምሯል ብሏል፡፡ ከበሽታው የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሄዱንም ከጥናቱ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

የበሽታው የስርጭት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደርሳል ተብሎ በሚጠበቅበት የህዳር ወር ላይ 392ሺ767 የሆስፒታል አልጋዎችና 21ሺ038 የጽኑ ህመምተኛ አልጋዎች እንደሚያስፈልጉ የተነበየው የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጥናት፤ በሽታው እስከ ፈረንጆቹ አዲስ አመት ድረስ እንደሚቆይና እስከዚያው ጊዜ ድረስም በአጠቃላይ ከ50ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አመልክቷል፡፡

(ምንጭ:- አዲስ አድማስ ጋዜጣ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top