Connect with us

ጀዋር መሐመድ ከ86 ሰዎች ሞት ጋር የተያያዘው ክስተት እንዲጣራ ጠየቀ

ጀዋር መሐመድ ከ86 ሰዎች ሞት ጋር የተያያዘው ክስተት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቀ
Photo: Al Jazeera

ፓለቲካ

ጀዋር መሐመድ ከ86 ሰዎች ሞት ጋር የተያያዘው ክስተት እንዲጣራ ጠየቀ

ጀዋር መሐመድ ከ86 ሰዎች ሞት ጋር የተያያዘው ክስተት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠየቀ
~ ጀዋር በራሱ ገፅ ላይ ያሰፈረው ሐተታ እነሆ:-

በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ላይ የሚቀርበው ትችት በሀገሪቷ የተፈጸሙ ግድያዎችን በሙሉ አላካተተም የሚል ነው። ይህ እውነት ነው። ለምሳሌ ሚያዚያ 2011 የተፈጸመውን ከ 400 በላይ ጉሙዞች የተጨፈጨፉበትን፥ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት በአማራ፣ ተጋሩና፤ ቅማንት ማህበረሰብ ላይ በተጨማሪም ሀምሌ 2011 በሲዳማ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ ግድያዎችን አላካተተም። በኔ ላይ የግዳያ ሙከራ ከተካሄደ በኋላ በኦሮሚያ ውስጥ በተከሰተው ግጭት የተፈጸሙ እና እንደመንግስት አሃዝ የ86 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ ግጭቶችንም አላካተተም።

እዚህ ጋር ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ቢኖር በኔ ላያ ተቃጥቶ በከሸፈው ጥቃት እና እሱን ተከትሎ የተፈጸሙትን አሳዛኝ ግድያዎች አስመልክቶ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች በሀሜት እኔን ሲውነጅሉ ነበር። ሰሞኑን ደግሞ የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ግንኙነት እና ጸጥታ ሀላፊዎች በይፋ ወንጅለውኛል፤ ለ86 ሰዎች ሞት ተጠያቂ እንደሆንኩ በመግለጫቸው አትተዋል። ይህ እንግዲህ በወቅቱ የክልሉ መንግስት ፕሬዚደንት እና የፖሊስ አዛዥ በግልፅ ወጥተው ስህተቱ የመንግስት እንደሆነ አጥፊ ባለስልጣናት ተጣርተው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ቃል የገቡትን የሚጻረር ነው ብቻ ሳይሆን ሁለቱ ባለስልጣናት ድርጊቱን ወደ እኔ በማላከክ አምነስቲ ያወጣውን ሪፖርት ሽፋፍኖ ለማለፍ ያደረጉት ጥረት መሆኑ መካድ የለበትም ።

ይህ ነገር ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር ያየሁትን ነገር አስታወሰኝ። “ሰሞኑን በአሜሪካ እየደረሰ ላለው ግጭትና ውድመት ተጠያቂው ጆርጅ ፍሎይድ ነው። እሱ “I can’t breathe” ባይል ኖሮ ይህ ሁሉ ጣጣ መች ይመጣ ነበር” ያሉትን። በተወሰነ መልኩ የኔ ከሳሾች ከሚያነሱት ጋር ይመሳሰላል። በውድቅት ሌሊት እሱ ሳይሰማ ሹልክ ብላች ሁ ውጡ ያለው አካል ማንነቱን እና አላማውን ለህዝብ መናገር ፈርቶ እኔ የታሰበውን ሴራ በማጋለጤ ብቻ እኔን ተጠያቂ ሊያደርግ ይፈልጋል። ህሊና ያለው ሰው ጥፋቱ የማን እንደሆነ በሚገባ ይረዳል። እኔ ግን አውቆ የተኛን ለመቀስቀስ በመሞከር ጊዜዬን አላባክንም። በዚህ ክስተት አንድም ሰው ቢሆን መሞት እንዳልነበረበት አምናለሁ። ነገር ግን በጊዜው ማንም ሰው በኔ ቦታ ቢሆን ጀርባውን ለፈሪ ጥይት ሰጥቶ አይተኛም። የመንግስት ሃላፊዎች አሁን ፀጉራቸውን የሚነጩት ለምን ሴራችን ከሸፈ በማለት ነው። እውነት ለሟቾች ቢቆረቆሩ በጊዜው ቃል እንደገቡት ጉዳዩ ተመርምሮ ጥፋተኛውን ለህግ እንዲቀርብ ባደረጉ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ነገር ግልጽ ላደርግ እወዳለሁ። በዚያን ወቅት በሰጠኋቸው ቃለምልልሶች እንደተናገርኩት የተከሰተው ሁኔታ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን እና አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ ማስተላለፌ ይታወሳል። ከመንግስት አመራሮች ጋር ባደረግናቸው ተከታታይ ውይይቶችም ይህንኑ በአጽኖት ስናገር ነበር። በወቅቱ ከተለያዩ ባልስልጣናት ጋር ባደረግናቸው ውይይቶች፤ የኦዲፒ እና አዴፓ ሰዎች በእኔ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ የሰጠው እና በከተሞች ውስጥ የተደረገውን ግጭት ማን እንዳቀነባበረ ይወነጃጀሉ ነበር። ለዚህ ማስረጃው በዚያ ሰሞን የኦዲፒ ካድሬዎች በሶሻል ሚዲያ ሲለጥፉ የነበረውን ማየት ብቻ በቂ ነው። እከሌን እናስራለን እከሌን አናባርራለን እያሉ በግልጽ ሲወነጃጀሉ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው። የኔ መልስ ግን ያዘዘውም ይሁን ያስፈጸመው አካል በሀሜት እና ሹክሹክታ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ መታወቅ፣ መጋለጥ እና ለፍርድ መቅረብ እንዳለበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያ እንደተመለሱ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ቢሮ በአካል ተገናኝተን በጉዳዩ ላይ ስንነጋገር ፤ በድርጊቱ ውስጥ ምንም ሚና እንዳልነበራቸው እና ትዕዛዙን በሰጡት ሀላፊዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተው ነበር። እኔም ጉዳዩ በእኔና በጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ያለ ግለሰባዊ ግጭት እንዳልሆነ እና በኔ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙትን ብቻ ሳይሆን ያን ተከትሎ የተከሰተውን ግጭት መርምሮ አሳማኝ በሆነ መልኩ ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ አካል ሊኖር እንደሚገባ በተደጋጋሚ ጊዜ ተናግሬያልሁ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ገለልተኛ የመርማሪ ቡድን መቋቋም እንዳለበት በአጽንኦት ገልጪ ነበር። ከዚያን በኋላ በተገናኘንባቸውም አጋጣሚዎች ይህንኑ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ወትውቻለሁ። ያንን ግን ማድረግ አልፈለጉም። እንደዚያ አይነት ምርመራ ብዙ ጉድ ሊዘከዝክ ስለሚችን እውነታው አስፈሪ ነውና።

አሁንም ቢሆን እነዚህን በተለያዩ ወቅት የዜጎች ህይወት የተቀጠፈባቸውን ክስተቶች በሃሜት እና በአሉባልታ ከማለፍ ነጻ እና ገለልተኛ የምርመራ ኮሚሽን ተቋቁሞ እውነታውን ቢያፈርጠው ፍትሃዊ እና ገንቢ የሚሆን ይመስለኛል። እንደዚህ አይነት ኮሚሽን ከተቋቋመ በበኩላችን አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን። ሀሜት እና conpiracy theory ትተን ሃገራችን ካለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር እንድትወጣ (national healing እንዲኖር) ፍላጎቱ ካለን አጠቃላይ የሽግግር ፍትህ (transitional justice) ያስፈልጋታል። ለዚህ ደግሞ መንግስት ሁሉን ያሳተፈ ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም ሁሉም ፓርቲዎች የሚስማሙበት ተቋም ለማቋቋም ቀዳሚ ሚናውን ሊወስድ ይገባል። እስካሁን ግን መንግስት ሁሉንም ክስተት ለፖለቲካ አላማ መጠቀም እንጂ ሃገሪቱን ወደተሻለ የይቅርታ፣ ሰላምና መቻቻል መንገድ የመምራት ፍላጎትም ሆነ እቅድ እያሳየ አይደለም። ለዚህ ድክመት ግን ሌላውን እንደምክንያት ከማቅረብ አልተቆጠበም ።

ስለዚህ ወደተሻለ መንገድ የሚወስደንን መንገድ በጋራ እንድንፈጥር እራሱን ሊያዘጋጅ ይገባዋል። ይህንም እንዲያደርግ እግረመንገዴን በድጋሚ ጥሬዬን አቀርባለሁ። ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ ተሞክሮ የከሸፈ ነው። ዳግም ቢሞከርም ይከሽፋል። ኢትዮጵያ የአንድ ቡድንን ወይም ግለሰብን ፈላጭ ቆራጭ አካሄድ የምትሸከምበት አቅም የላትም። ይህን አደርጋለሁ የሚል ካለ ግን እስከመጨረሻው ድረስ እንደምንታገለዉ ግልጽ ሊሆን ይገባል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top