Connect with us

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

ምጽ!...ምስኪን ህወሓት!
Photo: Social media

ፓለቲካ

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

ምጽ!…ምስኪን ህወሓት!

(እሱባለው ካሳ)

መቐለ የመሸገው የህወሓት አፈንጋጭ ክንፍ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እህል ውሃውን ከእነአካቴው የሚበጥስ በእብሪት የተሞላ መግለጫ አውጥቶ ተመለከትኩት፡፡ አፈንጋጩ ቡድን ራሱን ሕገመንግሥቱን ጨምሮ ሕግና ሥርዓትን አክባሪ፣ ለነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ተቆርቋሪ፣ የአገር ጥቅም አስከባሪ፣ የኮሮና ወረርሽኝን በሳይንሳዊ መንገድ መካች፤ … በተቃራኒው ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ኢ- ሕገመንግሥታዊ፣ የጦርነት አዋጅ ጎሳሚ፣ የአገር ጥቅምን አሳልፎ ሰጪ…..አድርጎ ያቀርባል፡፡

ይኸ ገራፊ፣ ደፋሪ፣ አሳዳጅ፣ ነፍስ በላ፣ የሙስናና ብልሹ አሰራር ተምሳሌት የሆነ ቡድን.. ይኸን ሁሉ ወሬውን የሚዘከዝከው አሳምሮ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በእጅጉ ይገርማል፡፡

የሾርት ሚሞሪ ነገር… ትላንት በንጹሐን ሰዎች ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ልለካ እንዳላለ፣ የስንቱን ጎጆ በኢ- ሰብዓዊ ድርጊቱ፣ በግፉ እንዳልከረቸመ፣ እንዳላበላሸ፣ ቤተሰብ እንዳልበተነ… እነሆ ዛሬ 360 ዲግሪ ተከረባብቶ “እኔ ፈጣሪህ ነኝ፣ እኔ አዳኝህ ነኝ” እያለ ከመቐለ ምሽጉ ሊታበይ ይሞክራል፡፡ በንዴት፣ በብስጭት እንደተንቦገቦገ ያቅራራል፡፡ ይገርማል!!..

ለእነዚህ ድኩማን የደበበ ሰይፉ ግጥም ጥሩ መልስ ይሰጣል፡-

በቀበሮ ጉድጓድ – ቀበሮ መስሏቸዉ፤

ዉሾቹ አጓሩ – በዛ ጩኸታቸዉ፤

አይ የዉሾች ነገር – ማን በነገራቸዉ፤

አንበሳ እንደሆነ – የሚጠብቃቸዉ።

***

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከግንቦት 15 እስከ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ባካሄደው ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አሳልፏል፡-

1. የኮረና ቫይረስ መከላከል ስራ ከዚህ በፊት ሲደረግ እንደቆየው አዲስ ለውጦች፣ ተጨባጭ የክልላችን ሁኔታ እንዲሁም ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ህዝባችንን ለማዳን እየተከላከልን ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በሚቀንስ መልኩ እየተገመገመ በጥብቅ እንዲመራ ተወስኗል፡፡

2. የ‘ብልፅግና’ ቡድን ከድሃ ጉሮሮ እና ልማት ቀምቶ ያልተቆጠበ ሃብት በማፍሰስ ሀገር ከጫፍ እስከ ጫፍ ለማበጣበጥ፤ በዶክሜንተሪ ፊልሞች የታገዘ ዘር የማጥፋት ጥሪ እንዲካሄድና ሁሉም መብቶች እንዲረጋገጡ እያደረገ ያለው ጭፍን ፀረ ህዝብና ስልጣንን በገንዘብ የመግዛት ተግባር እንዲቆም ብቻም ሳይሆን ከጥፋት መንገድ ወጥቶ በህገ መንግስት መሰረት የሚመለከተው ወገን ሁሉ ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እና ወደ ምክንያታዊ ውይይት እንዲገባ እንዲሁም ጨርሶ ሳይረፍድ ህገመንግስታዊ ስርዓት ከማፍረስ እንዲቆጠብ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያሳስባል፡፡

3. ሙሉ ዝግጅትና የህብረተሰቡን ጤና የመጠበቅ ስራ በመስራት በህገ መንግስት በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ሁሉንም እኩል ማየት የሚችል ኃይል የሚመራው ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ዳግም ያሳስባል፡፡

4. ምርጫ በሀገር አቀፍ ይሁን በክልል ደረጃ በሺዎች መስዋዕትነትና ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ያገኘ መብት እንጂ ገደብ የለሽ የስልጣን ጥማት ያለው ግልገል አምባገነን የሚሰጠው ወይም የሚከለክለው ችሮታ አይደለም፡፡ የትግራይ ህዝብ ከድሮም ቢሆን ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን በመስዋዕትነቱ ያረጋገጠ፤ በማንኛውንም ሁኔታ በራሱ ላይ ይሁን በሌሎች ህዝቦች ላይ ባርነት እንዲነግስ የማይፈቅድ ህዝብ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በመስዋዕትነቱ ያረጋገጠው መብት በማንኛውንም ጊዜ እና ሁኔታ ወደ ድርድር እንደማይቀርብና የዚህን መብት ተግባራዊነት ወደ ኋላ መመለስ የሚችል ማንኛውም ምድራዊ ፖለቲካዊ ኃይል እንደሌለ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስምሮበታል፡፡ ስለዚህም የፌደራል ስልጣን በአምባገነናዊ አኳኋን ተቆጣጥሮ ያለው ኃይል በተለመደው አካሄዱ የህዝቦችን መብት እየደፈጠጠ መቀጠሉን አጠናክሮ እየገፋበት በመሆኑ ህዝባችን በመስዋዕትነቱ ያረጋገጠው እና የማንም ፈቃድ የማይጠይቅበት፤ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በተግባር ለመተርጎም በክልላችን ምርጫ እንድደረግ እና ይህንን ለማድረግ የተጀመሩ ዝግጅቶች ለማድረግ የተጀመሩ ዝግጅቶች በህግ አግባብ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ በትግራይ ምርጫ እንዲካሄድ ሲወስን በ‘ብልጽግና’ ጥገኛ ባህሪ ምክንያት የተጀመረው ሕገ መንግስታዊ ስርዓት የማፍረስና ሃገር የመበተን ሂደት ወደ መጨረሻ ምዕራፍ እየደረሰ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ አሁንም ቢሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና እና ህዝቦች የሀገራችንን ህገ መንግስት ያጎናፀፋቸው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዳያጡ ትግላቸው ማጠናከር እንደሚገባቸው ህወሓት ያምናል፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንን ተገንዝቦ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

5. የ‘ብልፅግና’ ቡድን ምርጫ ላለማካሄድና የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም እየወሰዳቸው ካሉ ህገ ወጥ እርምጃዎችና ሴራዎች በተጨማሪ የድርጅታችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትግራይ ክልል ህግና ስርዓት እንደሚቀጥልና ‘ብልፅግና’ ምርጫ ለማስቀረት እየሰራ በመሆኑ በትግራይ ደረጃ በህግ መሰረት ምርጫ ለማካሄድ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት የብልጽግና መሪ አሁንም መሰረታዊ የህዝቦች ራስን በራስ የመወሰን መብት ክብር እንደሌለው በሚያሳይ መልኩ የጦርነት አዋጅ ይፋ አድርጓል፡፡ የትግራይ ህዝብ በፉከራና የጦርነት ነጋሪት መጎሰም እንደማይደነግጥና መብቱን አሳልፎ እንደማይሰጥ የሚታወቅ ሃቅ ነው፡፡ ኃላፊነት በጎደለው አካሄድ እንዲሁም የ‘ብልፅግና’ ቡድን እና መሪው የሚመጣ ማንኛውንም ጥፋት ብቸኛው ተጠያቂዎች ራሳቸው መሆናቸው መላው የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ መገንዘብ ይገባቸዋል፡፡

6. በልማት ስራዎች፣ የዴሞክራሲ ባህል እና አስተዳደር የተጀመሩ ለውጦች በጊዜ የለንም መንፈስ በበለጠ ፍጥነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በየደረጃው ያለው አመራር በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ እንዲሰራው ተወስኗል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መላው ህዝባችንና ሁሉም የመንግስትና የድርጅት መዋቅሮች ለርካሽ ዓላማቸው ሲሉ ከልማትና የዴሞራሲ ግንባታ ሃዲድ አውጥተው ወደ ብጥብጥና ጥፋት ሊያስገቡን የሚረባረቡ የብልጽግና ኃይሎች፣ አይዞህ ባዮችና እና ተላላኪዎቹ ለመመከት የተጀመረውን ትግል እንዲጠናከር ተወስኗል፡፡

7. የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት፣ የህዝባችን ደህንነትና ሰላምን የማረጋገጥ ጉዳዮች ላይ አብሮው ሊሰሩ ዝግጅ ከሆኑ የሀገራችንና የክልላችን የፖለቲካ ኃይሎች የተጀመረውን ዝምድና በፍጥነት ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገርና ትርጉም ያለው ለውጥ ሊያመጣ ወደሚችልበት የህዝባችን ደህንነትና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ስራዎች እንዲገባ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል።የህገ መንግስታዊ ስርአትንና መንግስትን አስፈላጊነትና ቀጣይነት በአግባቡ ተረድታችሁ ፣ይህን ለማረጋገጥ የድርሻችሁ ሀገራዊ ግዴታ እንደምትወጡ እና ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሰያችሁን አጠናክራችሁ እንደምትቀጥሉ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ያምናል።

ግንቦት 23/ 2012 ዓ/ም

መቐለ

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top