Connect with us

“ታሪካዊ ቅርሶች አይፈርሱም” የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር

"ታሪካዊ ቅርሶች አይፈርሱም" የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር
Photo Facebook

ባህልና ታሪክ

“ታሪካዊ ቅርሶች አይፈርሱም” የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ እያከናወነ ባለው መልሶ መገንባትና የከተማ ማስዋብ ስራ ከግንባታው በተጨማሪ የተለያዩ የቦታ ዝግጅቶች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚያልፍባቸው መሥመሮች 7(ሰባት) የተለያዩ በቅርስነት የተመዘገቡና የሚታወሱ ህንጻዎች ያሉ ሲሆን ህንጻዎቹም በመልሶ ማልማት ውስጥ የተካተቱ ታሪካዊ ይዞታቸውን እንደጠበቁ የሚታደሱና አገልግሎት ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡

"ታሪካዊ ቅርሶች አይፈርሱም" የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር

ህንጻዎቹን ሲገለገሉበት የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማትም ወደ ሌላ ቦታ የሚዛወሩ ይሆናል፡፡
ከዚህ ባለፈ ቅርሶቹ ሊፈርሱ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰትና የፈጠራ ወሬ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ይህን በተመለከተ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ እያስተላለፉ የሚገኙ የብሮድካስትም ይሆን የኦንላይን ሚዲያዎች የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጠየቅ ትክለኛና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ እንዲያስተላልፉ እናሳስባለን፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top