Connect with us

#ፈንቅል!!

ፈንቅል!!

ፓለቲካ

#ፈንቅል!!

ፈንቅል!!

ትላንት የተወሰኑ የ#ፈንቅል ንቅናቄ ግዜያዊና በጎ-ፈቃደኛ አመራሮች በZoom-Videoና በአካል አገኛሃቸው፤

ለግዜው አግኝቼ ለማወያየት የቻልኩት ከትግራይ፣ ከመላ-አገርና ከውጭ በሚል ሶስት ምድብ በጠቅላላ 30 ወጣቶች ሲሆኑ አባላቱ ከጠበቁኩት በላይ በሳል፣ ቁርጠኛ፣ ነፃና ሰፊ የወጣቶች እንቅስቃሴ መረብ የፈጠሩ ሆኖው አግኝቻቸዋለሁ፡፡

ጥንስሱ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ የሆነውና አሁን በተለየ ጥንካሬና አስፈላጊነት ስለመጣው የትግራይ ወጣቶች ሰላማዊና ፖለቲካዊ ንቅናቄ (ፈንቅል) ከተወሰኑ ግዜያዊና ከበጎ-ፈቃደኛ አመራሮቹ ጋር ጥልቀትና ስፋት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች አንስተን ተወያይተናል፡፡

በውይይታችንም ፈንቅል የሚመራው በራሱ በመላ የትግራይ ወጣት መሆኑና ግዜያዊና የበጎ-ፈቃድ አመራሩም በየአከባቢው ያለው ወጣት በፈቃደኝነት እርስ-በራሱ በመመራረጥ የሚዋቀር መሆኑ ለማወቅ ችያለሁ፡፡

ከዚህ በመቀጠል አገራዊ ለውጡን እንዴት በተሻለና በተደራጀ መልኩ ከዳር እስከዳር መድረስ እንዳለበትና የትግራይ ህዝብ ባርነት ብለው ከገለፁት አስከፊ ሁኔታ እንዴት መላቀቅ እንዳለበት የሰጡኝ ትንታኔ እጅግኑ አስደምሞኝ እምበር ፈንቅል አስብለውኛል፡፡

የትግራይ ህዝብ አገራዊ ለውጡን በሚመለከት በትዕግስት መጠበቁንና ለህወሓት የመጨረሻ እድል መስጠቱን በግዜው ትክክል መኖሩ አሁን ግን ሁሉም ነገር ያበቃለትና ህወሓትም የተሰጠው የመጨረሻ እድል ሊጠቀም ባለመቻሉ አገራዊ ለውጡ በተሻለ እንቅስቃሴና አፈፃፀም ከዳር ማድረስና ከመላ ኢትዮጵያን ወጣቶች ጋር ያላቸው የሃሳብ፣ የዓላማ፣ የፍላጎት፣ የትግል ስምረት እንዲሁም ኢትዮጵያዊ አንድነታቸው እንደሚያስመሰክሩ ለዚህም በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ በሳል ፖለቲካዊ ትንታኔ ላይ ተንተርሰው አስረድተውኛል፡፡

እንግዲህ ትግራይም ለሁላችን የምትበቃ የጋራ ቤታችን ነች፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ ለማውጣትና በታሪኩ ልክ የአገር ባለቤትነቱና ተጠቃሚነቱ ለማስከበር ህዝብን አስቀድመን ባመንበትና በቻልነው መንገድ ሁሉ እንታገል፡፡

ለውጥ ፈላጊ የትግራይ ወጣቶች (ፈንቅሎች) እንኳን ተጠናክራቹ መጣቹ፤ ሰላማዊና ፖለቲካዊ ትግላችሁ ህዝብና ታሪክ ይመለከተዋል፤ ያከብረዋልም!!

ነቢዩ ስሑል ሚካኤል
የትግራይ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top