Connect with us

አቶ ታደሰ ካሳ በሌላ የክስ መዝገብ በ8 ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተቀጣ

አቶ ታደሰ ካሳ በሌላ የክስ መዝገብ በ8 ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተቀጣ

ህግና ስርዓት

አቶ ታደሰ ካሳ በሌላ የክስ መዝገብ በ8 ዓመት ከአምስት ወር እስራት ተቀጣ

የባህዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ በሌላ የክስ መዝገብ 8 ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቀ።

ችሎቱ ቅጣቱን ያሳለፈው ጥረት ኮርፖሬትን በዋና ስራ አስፈፃሚነት አቶ ታደሰ ካሳይመራ በነበረበት ወቅት ከሌሎች ጋር በመተባበር ስራን በማያመች መንገድ መርተዋል በሚልና በተለያዩ የሙስና ክሶች ጥፋተኛ በመሆኑ መሆኑን ።
በእነታደሰ ካሳ የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታዩ የነበሩ ተከሳሾች ዛሬ ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚሁ መዝገብ ሥር የተዘረዘሩ ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ ከሁለት ዓመት እስከ ሦስት ዓመት ከሰባት ወር የሚደርስ እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡ ከአራት ሺህ እስከ 10 ሺህ የሚደርስ የገንዘብ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል፡፡

ነገር ግን ከአቶ ታደሰ ካሳ ውጭ ያሉ ተከሳሾች 50 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው በሁለት ዓመት ገደብ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

አቶ ታደሰ ካሳ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር በተመሰረተባቸው ተመሳሳይ የሙስና ክስ 8 ዓመት ጽኑ እስራትና 15 ሺህ ብር መቀጣቱ ይታወሳል።

ከትናንት በስቲያ በነበረው ችሎት በዚሁ መዝገብ ሥር ተከስሰው የነበሩት አቶ ምትኩ በየነ እና ሀጂ ሁሴን አህመድ በነፃ መለቀቃቸውን የአብመድ ዘግቧል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top