Connect with us

“የኮሮናቫይረስ እስከወዲያኛው ላይጠፋ ይችላል” – የዓለም ጤና ድርጅት

"የኮሮናቫይረስ እስከወዲያኛው ላይጠፋ ይችላል" - የዓለም ጤና ድርጅት
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

“የኮሮናቫይረስ እስከወዲያኛው ላይጠፋ ይችላል” – የዓለም ጤና ድርጅት

የኮሮናቫይረስ በአለማችን እስከወዲያኛው ላይጠፋ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ በበሽታው ዙሪያ በሰጠው መገለጫ ቫይረሱ መቼ ይጠፋል የሚለውን ለመተንበይ መሞከር ስህተት መሆኑን አስጠንቅቋል፡፡

የኮሮናቫይረስ በአለም ማህበረሰብ ሌላኛው ወረርሽኝ ሆኖ እስከወዲያኛው ሊቆይ ይችላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለብን ያለው ተቋሙ፥ በአለማችን ቫይረሱ እስከወዲያኛው ሳይጠፋ አብሮን ሊኖር ይችላል ብሏል፡፡

ለበሽታው ክትባት ቢገኝ እንኳን ቫይረሱን ለመቆጣጠር ሰፊ ጥረት እንደሚጠይቅ ድርጅቱ አስገንዝቧል፡፡
እንደ የአለም ጤና ድርጅት ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እስካሁን በአለማችን ያልተወገደ ቢሆንም ቫይረሱን መረዳት እና መቆጣጠር ተችሏል ብሏል፡፡

በመሆኑንም ቫይረሱ የሚጠፋበትን ጊዜ ከመገመት ይልቅ በሽታው ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ጥረት በማድረግ እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አሁን ላይ በበሽታው ዙሪያ ከ100 በላይ ክትባቶች ቀርበው ጥናት እየተደረገባቸው መሆኑንም ተመልክቷል፡፡
ቫይረሱ በማህበረሰቡ ውስጥ ጭንቀትና የአይምሮ የጤና ችግር እየፈጠረ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅት ጠቁሟል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top