Connect with us

ትብብር የመንግሥት ሥልጣን በአንድ አመት እንዲራዘም ጠየቀ

ትብብር ለህብረ-ብሔር ዲሞክራሲያዊ ፈደራሊዝም (ትብብር) የመንግሥት ሥልጣን በአንድ አመት እንዲራዘም ጠየቀ

ፓለቲካ

ትብብር የመንግሥት ሥልጣን በአንድ አመት እንዲራዘም ጠየቀ

ትብብር ለህብረ-ብሔር ዲሞክራሲያዊ ፈደራሊዝም (ትብብር) የመንግሥት ሥልጣን በአንድ አመት እንዲራዘም ጠየቀ

ትብብር መንግሥት ገጥሞታል ላለው ሕገመንግሥታዊ ቀውስ ፓለቲካዊ የመፍትሔ ሀሳብ አቀረበ።በዚሁ መሰረት ገዥው ፓርቲ ሥልጣኑ በአንድ አመት እንዲራዘም ሀሳብ አቅርቧል።

***

የመግለጫው ማጠቃለያ ሀሳብ እነሆ

1) በኮቪድ-19 ምክንያት ምርጫዉን ማራዘም ግድ ሆኖዋል።
2) በህገ-መንግሥቱን ተከትሎ ምርጫዉን ለማራዘም የሚያስችል አማራጭ ከህገ-መንግሥቱ ዉስጥ ማግኘት አይቻልም። ካሁን በፊት ኢሕአዴግ ለሕዝብ ዉይይትና ዉሳኔ ሳያቀርብ ህገ-መንግሥቱ ላይ ማሻሻያ አድርጎ ነበር የሚለዉ ተሞክሮም (precedence) ተቀባይነት የለዉም።

3) በህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 9. 2 ላይ እንደተደነገገዉ “ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፣ ሕገ መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው፡፡” ይላል። ስለዚህ፣ መፍትሔዉ ለሀገርና ለሕዝቦች ሰላምና መግባባት ሲባል አገርን በሚጠቅም መልኩ በጥንቃቄና በስምምነት ከዉሳኔ የሚደረስበት ልሆን ይገባል።

3.4 ከህገ-መንግሥቱ ዉጪ ሥልጣንን ማራዘም የሚያመጣዉ ችግር
ህገ-መንግሥቱን ባልተከተለ መንገድ በመንግሥት በራሱ ዉሳኔ የሥልጣን ጊዜዉን የሚያራዝም ከሆነ፡

አንቀጽ 9. 3 (በዚህ ሕገ መንግሥት ከተደነገገው ውጭ በማናቸውም አኳን የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የተከለከለ ነው፡፡) የሚለዉን መተላለፍ መሆኑና ይህም በሌላ በኩል የሀገሪቱን ህገ-መንግሥት ብቻም ሳይሆን በህገ-መንግሥቱ ዉስጥ በአንቀጽ 9. 4 ላይ የተካተቱትን ዓለም-አቀፋዊ ስምምነቶችንም (9.4 ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው፡፡) መጣስ ይሆናል። ይህም ለምሳሌ፡

በአፍሪካ አንድነት ቻርተር ዉስጥ፥“Chapter 8 Sanctions in Cases of Unconstitutional Changes of Government

Article 23.5 Any amendment or revision of the constitution or legal instruments, which is an infringement on the principles of democratic change of government.”

እንዲሁም፣

“Universal Declaration of Human Rights፥ The Declaration was proclaimed by the United Nations General Assembly in Paris on 10 December 1948

Article 21 .1. Everyone has the right to take part in the government of his country, directly or through freely chosen representatives.

Article 21.3 The will of the people shall be the basis of the authority of government; this will shall be expressed in periodic and genuine elections which shall be by universal and equal suffrage and shall be held by secret vote or by equivalent free voting procedures.”

4. የመፍትሔ ሀሳብ
በየአምስት ዓመቱ የሚደረግ ጠቅላላ ምርጫን በማራዘም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን ማራዘም የሚያስችል የህገ-መንግሥት ድንጋጌ ባለመኖሩ አሁን ያለዉ የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚዉ አካል የተወሰነ የጊዜ ገደብ ተሰጥቶት በሥልጣን እንዲቀጥል ተደርጎ በዚህ ግዜ ውስጥ፡ ስልጣን ላይ ያለው አስፈጻሚው አካል የእለት ተእለት የመንግስት ስራ ከማከናወንና ምርጫን ለማካሄድ ከማገዝ ውጪ ህግ ወይም አዋጅ ማውጣት፣ ማሻሻል ወይም ያሉትን ህጎች መሻር እና አዳድስ አደረጃጀትና አወቃቀሮችን መዝርጋት የለበትም፡ ብለን እናምናለን። ይህም ማለት ህገ-መንግስቱ እንዳለ ሆኖ ወይም ሳይነካ አሁን ላጋጠመን አዲስና ያልተለመደ ፈተና በሁሉም ወገኖች የጋራ ስምምነት (consensus) አዲስና ያልተለመደ ፖለቲካዊ መፍትሔ/Political settlement ሊበጅለት ያስፈልጋል ማለታችን ነዉ። በዚህም መሠረት ያለንን ፖለቲካዊ የመፍትሔ ሀሳብ/አማራጭ እንደሚከተለዉ በዝርዝር እናቀርባለን።

ይህ የመፍትሔ ሀሳብ/አማራጭ የተመሠረተባቸዉን መሠረታዊ ምክንያቶችን መጀመሪያ ግልጽ ለማድረግ፡

✓ ኮቪድ-19 የ2012 ጠቅላላ ምርጫ በታቀደለት ጊዜ ዉስጥ እንዲካሄድ የማያስችል መሆኑን ስለሚናምንበት፣

✓ በህገመንግሥቱ አንቀጽ 9.2 ላይ በማያሻማ መልኩ እንደተቀመጠዉ፡ “ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው፣ ሕገ መንግሥቱን የማስከበርና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው፡፡” ይላል። በዚህ እናምናለን። ላለፉት ዓመታት መሠረታዊ የመቀራረቢያ ሰነድ ሆኖ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ እንዲያገለግል ተስፋ የተጣለበት ይሄዉ ህገ-መንግሥት ስለሆነ እሱ ከመሠረቱ ሳይነካ ይች እንደ አገር ሆና እንዳትቀጥል ጥያቄ ዉስጥ በማይገባበት ሁኔታ ምርጫዉን ለማራዘም፣

✓ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን የጋራ ጥቅምና ሀገራዊ ህልውና የሚያስከብርና የሚያራምድ የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጥያቄ ዉስጥ እንዳይገባ፣

✓ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲዉ መስክ፡ በኢጋድ/IGAD, በአፍሪካ ህብረት/AU እና በተባበሩት መንግሥታት/ UN ዉስጥ ያላት ድርሻ እንዳይታገድና ይህ አሻጋሪዉ መንግሥት ህጋዊነቱ ላይ የጋራ ስምምነት እንድኖረን፣

✓ ሀገራዊ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲፈጠር በፍጥነት ሀገራዊ ሰላምን የሚከላከል መንግሥት እንድኖር፣

✓ አሁን ሀገር እየመራ ያለዉ ፓርቲ በለዉጡ መጀመሪያ አከባቢ የገባዉን ቃል በመሸርሸር ህግና ህገ-መንግሥት አስከባሪ አካላትን ለራሱ ፖለቲካዊ ጥቅም በመጠቀም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችን አባላትና ደጋፊዎችን (የአመራር አባላትን ጨምሮ) በእስር ቤቶች በማጎሩ የተጣለበት ተስፋና እምነት እንደተጠበቀ አለመሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት፣

✓ ባጠቃላይ አሁን ሀገሪቱን ያጋጠመዉ ፊተና መፍትሔዉ ከህገ-መንግሥቱ ዉስጥ ተፈልጎ ልገኝለት የማይችልና አድስ እንደመሆኑ በአድስ አቀራረብ በአድስና ፖለቲካዊ መፍትሔ ብቻ ልንወጣዉ የሚንችል ነዉ ብለን ስለምናምን ነዉ።
ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦችን በመመርኮዝ አሁን ያለዉ መንግሥት የሥራ አስፈጻሚዉ አካል (Executive body of the current Government) ለአንድ ዓመት ሥልጣኑ እንዲራዘም ሆኖ ጠቅላላ ምርጫው በግንቦት ወር 2013 ተጠናቆ አዲስ የሚመረጠው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ስል በተለመደው ግዜ ስራውን እንድጀምር ማድረግ። ይህ እንዳለ ሆኖ ያሉት ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በሚከተሉት ሀገራዊ ጉዳዮች ዉስጥ በቀጥታ ተሳትፎና ድርሻ ኖሮዋቸዉ ለሚፈለገዉ የዴሞክራሲ ግምባታም ሆነ ለሀገር ሰላምና ህልዉና ይረዳ ዘንድ ወጥ የሆነ መፍትሔ “Political conventions” መቅረጹ የግድ ይላል።

እነሱም፡

1. በዉጭ ግንኙነት አካል ዉስጥ (Council of Foreign Relation)
➢ To inspire domestic trust and gain international legitimacy.

2. በብሔራዊ ደህንነት (Coordinated National security council or Committee for Monitoring the Implementation of the Security Arrangements )
➢ ሀገር ደህንነትና ሰላም ጉዳዮች አካል ዉስጥ (በሀገር ደህንነት፣ መከላከያ፣ ፖሊስ፣) ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ማገልገላቸዉን ለመከታተልና ብሎም በሀገር ህልውና ላይ የሚቃጣ አደጋ ቢያጋጥም የጋራ ሀላፍነት ለመዉሰድ እንዲያግዝ
➢ To balance the need for bureaucratic, technocratic, security and judicial expertise against the aim to limit the influence of the regime. To create civil order and end violence, while ensuring that all security and intelligence forces would be subject to control by the civilian authorities.

3. የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተቋማት (Democratic Institutions building) ዉስጥ ተሳታፊነት
➢ የሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዋስትና የሆኑት ተቋማት ዉስጥ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ተሳትፎ በማሳደግ ሂደቱንና አሠራሩን የሚቆጣጠር ሥርዓት መፍጠር። (Procedural limits how the government can act, in order to prevent arbitrariness, corruption, oppression, discrimination, and the misuse of public office for personal gain)
➢ የባለሥልጣናትን ሥልጣን ኣለግባብ መጠቀም የሚከታተልና የሚቆጣጠር ነፃና ገለልተኛ የዳኝነት ሥርዓትና የሚዲያ ተቋማት መኖራቸዉን ለመከታተልና ለማረጋገጥ የሚረዳ አሠራር ማበጀት (To establish or protect the autonomy and authority of independent judiciaries and independent media that could hold national executives and others accountable)

4. ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ ኮሚሽን
➢ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ የጋራ አካል በጋራ መፍጠር

5. የተራዘመዉን የጊዜ ገደብ አግባብ ባልሆነ መልኩ በመጠቀም ለሌላ ችግር እንዳይዳርገን የሚቆጣጠር ኮሚቴ
➢ To limit an attempts for further extension
የእነዚህን አካላት ተጠሪነትና የአሠራር ሥርዓት በዝርዝር አዘጋጅተን የሚናቀርብ ይሆናል።

በመጨረሻም አሁን ስልጣን ላይ ያለው የፌዴራል መንግስት፣ የክልል መንግስታት፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የአገርጡ ህዝቦች ከላይ የደረስነበትን የፖልቲካ ውሳኔ የምርጫ ህግን በሚመለከት ህግ መንግስቱን ካጋጠመው ቀውስ ሊያሻግረን እንደሚችል ስለምገነዘቡ ውሳኔያችንን ይጋራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ትብብር ለህብረ-ብሔር ዲሞክራሲያዊ ፈደራሊዝም(ትብብር)

ሚያዚያ 2012 ዓም

አዲስ አበባ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

 • ሥልጠና እየተካሄደ ነው ሥልጠና እየተካሄደ ነው

  ዜና

  ሥልጠና እየተካሄደ ነው

  By

  ሥልጠና እየተካሄደ ነው የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫ ቅስቀሳ አስተባባሪ ግብረሀይል የምርጫ ክልል 28 የአስተባባሪዎች...

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤ ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  ነፃ ሃሳብ

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን እናመሰግናለን፤

  By

  ብዙ የሀገር ዋርካዎች እንዳቀረቀሩ አልፈዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እናመሰግናለን ብለው እውቅና ስለሰጧቸው የጥበብ አንጋፋዎች እኛም እርስዎን...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  ነፃ ሃሳብ

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡

  By

  የሰባት ቁጥር ምስጢርና የይባቤ አዳነ አዲስ ሥራ፡፡ ሰባት ቁጥርና ሕይወት፤ (አፈወርቅ ልሣኑ ~ ድሬቲዩብ) ሰባት ቁጥር...

To Top