Connect with us

’’ኢትዮጵያ ለሁላችን በቂ ናት” – አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

’’ኢትዮጵያ ለሁላችን በቂ ናት" - አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
Photo: Social media

መዝናኛ

’’ኢትዮጵያ ለሁላችን በቂ ናት” – አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

የንን ጊዜ መቼም አይረሳውም። ከኦሎምፒኩ ድሉ ማግስት የተዜመለትን። “ቀነኒሳ አንበሳ”። ይሄን ዜማ ሲሰማ በውስጡ ልዩ ሀሴት ይሰፍናል። ለውለታው የተዜመ ልዩ ስጦታው አድርጎ ይቆጥረዋል። አንዳች ልዩ ስሜትና ትዝታ ውስጥ የሚከተው ዜማ እንኳን ለተወዳደሪዎቹ ተመልካቹን በስሜት የናጠ ነው።

“እልል በል ያገሬ ጎበዝ ለእምዬ ውለታ

ወርቅ አመጣሁላት ልጇ ለክብሯ ስጦታ..”

በረጅም ርቀት ውድድር የመጨረሻ ዙርን እንደ አጭር ርቀት የሚደመድም፤ በታላለቅ የውድድር መድረኮች በከፍታ የነገሰ ፤ እንደ አቦ ሸማኔ በፈጠኑ ጠንካራና ቀጫጭን እግሮቹ ተዓምር የሰራ ፤ የአገሩን ሰንደቅ አላማ በዓለም አደባባይ በክብር ከፍ አድርጎ ያወለበለበ፤ ህዝብ በእርሱ ድል እንዲፈነድቅ፣ ከያኒው ስለሱ አብዝቶ እንዲቀኝ ምክንያት የሆነ ኮከብ አትሌት ነው ቀነኒሳ በቀለ። ትጋት ጥንካሬና ፍጥነቱ “አንበሳው” የሚል ቅጥያ ያንሰዋል። ሀገር የሰጠውን ታላቅ አደራ አተልቆ የከፈለ ጀግና ነውና ።

የዕረፍት ሰዓት ቆይታ

ህይወትን ቀለል አድርጎ መኖር፤ የተካበዱ ጉዳዮችን ሳሳ አድርጎ ማየት የአትሌት ቀነኒሳ የኑሮ ፍልስፍናና ልምድ ነው። አዳዲስ ሞዴል ዘመናዊ አውቶሞቢሎችን የራሱ የማድረግ አቅም አለው፤ ነገር ግን ይህን ማድረግ አይወድም። የመረጠው ቦታ ላይ ቅንጡ ኑሮን መምራት ይችላል፤ ያን መሆን ግን አይፈልግም። ቀለል ያለ ህይወት ምቾት እንደሚፈጥርለት ይናገራል።

የሚፈልገው በአኗኗሩ

በዙሪያው ካሉ ሰዎች የተለየ አለመሆንን ነው። ያሻውን ከማድረግ ውጪ ለይሉኝታ ግድ የማይሰጠው ሰው መሆኑን ይናገራል።

ለእርሱ ይህን ከማድረግ ነፍሱ በሀሴት የሚያጥለቀልቃት ከከተማ ርቀው ዓለም በቃኝ ብለው የመነኑ፤ የዓለምን ግሳንግስ ጠልተው የኮበለሉ፤ የምድርን ደስታ ንቀው ለነፍስ ያደሩ ባህታዊያንን አግኝቶ ከእርነሱ ጋር የእረፍት ጊዜውን ማሳለፍን ይመርጣል። ገዳማትና ራቅ ያሉ ተፈጥሯዊ ቦታዎች መገኘት እጅጉን ያስደስተዋል። ተፈጥሮ በራሱ የኳለውን አካባቢያዊ መልካም ምድር መመልከት ከምንም በላይ ያደንቃል። በእንዲህ ያለው ስፍራ መገኘትንም ሀሴት ያደርጋል።

የዕረፍት ጊዜን ከቤተሰብ ጋር

አብዛኛው የእረፍት ጊዜ ከቤተሰቡ ጋር ማሳለፍን የሚመርጠው አትሌት ቀነኒሳ ቤት ውስጥ ልዩ ቤተሰባዊ ድባብ በመፍጠር ከልጆቹ ጋር መጫወት፣ አዲስ የወጡ ፊልሞችን በጋራ መመልከት፣የተለያዩ የመናፈሻ ቦታዎች ላይ ቆይታን ማድረግ በእረፍት ቀኑ ያዘወትራል። ባለቤቱና ሶስቱ የአብራኩ ክፋይ ልጆቹ ‹‹ የደስታዬ ምንጭ ናቸው›› በማለት ለእነሱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ይገልፃል። ከቃላትም በላይ ገጽታው ይመሰክራል።

በማህበራዊ ህይወት በኩል ንቁ ተሳታፊ ነው አትሌት ቀነኒሳ። ለቅሶ፣ ሰርግና ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ይሳተፋል። በተጣበበ ጊዜውም ቢሆን ከጓደኞቹ ጋር የዕረፍት ሰዓት ቆይታ ያደርጋል። እዛ ደግሞ ቋንቋ ሁሉ ይቀየራል። አንድ አይነት ክንፍ ያላቸው አብረውይበራሉም አይደል አባባሉ።

የልብስ ምርጫ

ለሚለብሰው ልብስ ምርጫ ግድ የሌለው ቀነኒሳ በተለይ በእርፍት ሰዓቱ ቀለል ያለ አለባባስን ያዘወትራል። በልብስ ፋሽን የመከተል ልምዱ አይደ ለም። ብቻ ከመልበሻ ሳጥኑ ውስጥ ያገኘውን ደስ የሚለውና ሲለብስ ይቀለኛል ብሎ የሚያስበውንይመር ጣል።

የባህል ምግብ

በባለሙያ ክሽን ተደ ርጎ የተሰራ ዶሮ ወጥና ጨጨብሳ ከኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች እጅጉን የሚወዳቸው ናቸው። ከገ በታው ላይ አትክልትና ፍራፍሬዎች አዘውትሮ ቢያገኝ ይመርጣል። ለሚያ ደርገው የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ለጤናው ጠቃሚ የተባለ የአመጋገብ ልምድ ይከተላል። ከራሱ አልፎ የቤተሰቡን ጤናማ የሆነ አመጋገብ ክትትል ያደርጋል።

የአትሌቱ መልዕክት

“ተፈጥሮ ሳያጓድል ሁሉን ነገር የቸራት ኢትዮ ጵያ ለሁላችን በቂ ናት። አንድነታችን አጠንክረን ልዩነታችንን አስወግደን ለሁላችን ምቹ የሆነች ሀገር ለመፍጠር በቅን ልቦና እንትጋ።” ከአትሌቱ ጋር የነበረን አጭር መሳጭና አስተማሪ ቆይታችንን የማበ ቃው አትሌቱ ከሚወ ደው ሙዚቃ

“..ይቺ ባንዲራ አንበሳ ናት እድለኛ

ዛሬም አኮራት አንበሳ ቀነኒ ኬኛ አንበሳዬ አንበሳ”… የሚለውን ስንኝ በመው ሰድ ነው። ሰላም!

(አዲስ ዘመን ግንቦት 2/2012)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top