Connect with us

ዛሬ የዓለም ስደተኛ አእዋፍ ቀን ነው

ዛሬ የዓለም ስደተኛ አእዋፍ ቀን ነው
Egretta garzetta, Migratory Bird Sanctuaries along the Coast of Yellow Sea-Bohai Gulf of China (Phase I) © Yancheng Broadcasting Television / Yancheng Broadcasting Television

አለም አቀፍ

ዛሬ የዓለም ስደተኛ አእዋፍ ቀን ነው

ዛሬ የዓለም ስደተኛ አእዋፍ ቀን ነው፡፡
ሰዎች ዓለምን ይረብሻሉ፤ በአካል ያለያዩትን ዓለም ምናብ ሊያገናኙት ይሞክራሉ፤ ወፎች ግን ዓለምን ያገናኛሉ፤ እነሱ እንደ ሰው አይደሉምና፡፡
******
ከሄኖክ ስዮም  በድሬቲዩብ

ዛሬ የዓለም ስደተኛ ወፎች ቀን ነው፡፡ የሰው ልጅ ዓለምን በሚረብሽበት በዚህ ዘመን ዓለምን ስለሚያገናኙ ወፎች መልካም ማውራት ምርጫ ብቻ ሳይኾን ግዴታም ነው፡፡ ዓለምን አንድ መንደር አደረግናት የሚሉት የሰው ልጆች በአካል ያለያዮዋት ዓለም ፈጥረዋል፡፡ መልኳ፣ ሀብቷ፣ ጠባይዋ፣ በሰው ላይ ከፍቷል፡፡ ጦርነት ስደት በሽታ ረሃብና ሞት በሰው ልጆች መካከል የልዩነት ግድግዳ ኾነዋል፡፡ ግን ሰው በምናብ ይገናኝ ዘንድ ረቂቅ ቴክኖሎጂዎች ይባትላሉ፡፡

ወፎች ግን በደግነት ሰማያቱ የእነሱ ነው፡፡ አውሮፓ ሲቀዘቅዝ አፍሪቃ ቤታቸው ነው፡፡ እንደ ወፍ እንግዳ ተቀባይ የለም፤ የሌላ ዓለም ሰው ያለመኖሪያ ፍቃድ መጣብኝ የማይሉት ፍጥረቶች ዓለም ሀገራቸው ነው፡፡ ሊያውም ምድሩም ሰማዮም፡፡
ስሜናዊ አቅጣጫውን ትተው ወደ ደቡብ ሲበሩ የመጡት አእዋፍ ወቅት ጠብቀው ወደመጡበት ይመለሳሉ፡፡ እድሜ ለሜዲትራኒያንና ለካረቢያን ባህር እንግዳ ተቀባይ ተፈጥሮ ሩቅ ተጉዘው የመጡ አእዋፍን ያስተናግዳል፡፡

የወፍ ስደት ታሪክ የሩቅ ዘመን እውቀት ነው፡፡ የዛሬ ሦስት ሺህ ዓመት ግሪካውያን የስልጣኔዎቻቸው አንድ ጥያቄ ምን ፍለጋ አእዋፍ እንዲህ ካደር ዳር የዓለምን ጥግ ፍለጋ በረሩ የሚል ነበር፡፡ ሆመርና አርስቶትል ስለ ሩቅ ተጓዥ ወፎች በስራዎቻቸው ገልጸዋል፡፡ በረዶ ኾነብን ብለው ወቅት በመጠበቅ ጭር የሚሉ የሀገሩን ወፎች የታዘበው ጆንስ የተባለ ፊንላንዳዊ ሰው በ1749 ሳይንሳዊ ምርምሮችን መተግበር ጀመረ፡፡ ተጓዥ ወፎችን በቀለበትና በመቆጣጠሪያ መሳሪያ መከታተልና የጉዞውን ሁኔታ በጥበብ ማጥናት ከዘመናዊው እውቀት ጋር መስተጋብር ፈጠረ፡፡

14 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን በርሮ ጥሩ ምግብና ወቅት ፍለጋ ከአንዱ ስፍራ አንዱ ጋር መሄድ ለወፍ ምንም ነው፡፡ ከዓለም አርባ በመቶ አእዋፍ ወይም አራት ሺህ የሚኾን የአእዋፍ ዝርያ በመደበኛነት የስደትን ጉዞ ያከናውናል፡፡ እንደ Jhanneel Lockhart ገለጻ ከምድርን ከፍ ብለው ከባህር ወለሉ ግማሽ ያህል ማይል ከፍታ ባለው ሰማይ ብዙውን መንገድ የሚበሩት እነኚህ ተጓዦች በአመት 49700 ማይል ይበራሉ ይለናል፡፡ በተለይም የአርክቲክ ተጓዥ አእዋፍ፤ እዚህ ውስጥ የሚቆጠር እድለኛ ወፍ ፈጣሪ ከወደደው በዓመት ሁለት በጋ ይመለከታል፡፡

ከአርክቲክ ተነስቶ አፍሪቃ የሚደርሰው የአእዋፍ ቡድን ረዥሙን ቢጓዝም ትንንሽ አእዋፍን ጭምር በመያዝ ተአምረኛ የሚባል ነው፡፡

በኢትዮጵያ እንዲህ ወቅት ጠብቀው የሚመጡ ስደተኛ ወፎችን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች አሉ፡፡ አብጃታ ሻላ ዋናው ነው፡፡ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ሀይቆች አሸንጌ፣ የጣና ባህረ ገብ ውሃ አዘል ስፍራዎች ማለትም ሸሸር እኔ እንኳን ወቅት ጠብቄ ብዙ የዓመት እንግዳ ወፍ ያየሁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

ዛሬ የሚከበረው ይህ ቀን ወፎች ዓለምን ያገናኛሉ የሚል መሪ ቃል አለው፡፡ እውነት ነው የሰው ልጅ ዓለምን ያለያያል ወፎች ዓለምን ያገናኛሉ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top