Connect with us

ኮሮና በማህበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል የሚል ስጋት አለ

ኮሮና በማህበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል የሚል ስጋት አለ
Photo: Social media

ጤና

ኮሮና በማህበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል የሚል ስጋት አለ

በሽታው በአጭር ጊዜ ውስጥ የመዛመት ዕድል አለው ተብሏል

ሰሞኑን በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከማህበረሰቡ ውስጥ የተገኙ ናቸው

ለበሽታው ስርጭት ከፍተኛ ተጋላጭነት እንዳላቸው የሚጠረጠሩ ተቋማት ላይ አሰሳ እየተካሄደ ነው

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማህበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል የሚል ስጋት እንዳለ የገለፁት የጤና ባለሙያዎች፤ ይህም የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ፈታኝ እንደሚያደርገው አስታወቁ፡፡

ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 49 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ያወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሚኒስትሮች የፀረ ኮቪድ -19 ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደመቀ መኮንን፤ ይህም በሽታው በአጭር ጊዜ ውስጥ በፍጥነት የመዛመት ዕድል እንዳለው በግልጽ ያመላክታል ብለዋል፡፡ አያይዘውም፤ የወረርሽኙ አዝማሚያ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመረዳት በወቅታዊ ጉዳዮች ሳንዘናጋ የጥንቃቄ መመሪያዎችን አጥብቀን ተግባራዊ እንድናደርግ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Ethiopia

የማህበረሰብ ጤና ባለሙያው ዶ/ር ቴዎድሮስ ታመነ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ ሰሞኑን የበሽታውን ስርጭት አስመልክቶ ከሚቀርቡት ሪፖርቶች መረዳት እንደሚቻለው በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠባቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያልነበሩና በማህበረሰቡ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታም በሽታው ወደ ማህበረሰቡ ዘልቆ ገብቷል የሚለውን ሥጋት ያጠናክረዋል ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ፡፡ በበሽታው መያዛቸው ይፋ ከተደረገባቸው ሰዎች መካከል በድንገተኛ የናሙና ጥናት የተገኙ መኖራቸው ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በአገራችን የኮቪድ 19 ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋ እንደገለፁት፤ በቅርቡ ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረጋገጠባቸው ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ምንም አይነት የውጪ ጉዞ ያልነበራቸው፣ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነትና ንኪኪ የሌላቸው መሆኑና አብዛኛዎቹም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያልነበሩ መሆናቸው የበሽታው ስርጭት ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ ገብቶ ይሆናል የሚለውን ጥርጣሬ ማስነሳቱን ጠቁመው፤ ይህንን ሁኔታ ለማረጋገጥ ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ሊደረጉ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ከለይቶ ማቆያ ውጪ ሆነው ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ በቫይረሱ ተጠርጥረው ተጨማሪ ምርመራ ከተደረገላቸው፣ በጤና ተቋማት ውስጥ ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማንና፣ ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው ተብለው በሚታሰቡ ቦታዎች ላይ በተደረጉ ምርመራዎች፣ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መገኘታቸውን ያመለከቱት አቶ ዘውዱ፤ ይህም ሁኔታ በሽታው በማህበረሰቡ ውስጥ መግባቱን የሚያመለክት ነው ብለዋል፡፡

አያይዘውም፤ ለበሽታው ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው ተብለው በሚታሰቡ እንደ አረጋውያን መንከባከቢያ፣ ሕጻናት ማሳደጊያ፣ ማረሚያ ቤቶችና መሰል ተቋማት ላይ የአሰሳ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Ethiopia

Confirmed
0
+0 (24h)
Deaths
0
+0 (24h)
Recovered
NAN%
Active
0
NAN%

የህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች በኮቪድ 19 በሽታ መከላከል ኮሚቴ ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ በበኩላቸው፤ “በለይቶ ማቆያ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች ውጪ የሆኑና በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ የበሽታው ስርጭት ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ ለመግባቱ አመላካች ነው፤ ይህ ደግሞ ጥሩ ዜና አይደለም::

ምክንያቱም በሽታው ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ ከገባ ለመቆጣጠርና ስርጭቱን ለመከላከል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ::”

በሽታው ኖሮባቸው እንዳለባቸው የማያውቁ ወይም ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ደግሞ በሽታውን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ለማስተላለፍ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል ብለዋል – ዶ/ር ሰለሞን፡፡

የበሽታው ስርጭት ፍጥነትና የመሰራጫ መንገዱ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚሻ መሆኑን ያመለከቱት ዶ/ር ሰለሞን፤ ጤናማ መስለው በሽታውን የሚያሰራጩ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግና ራሱን ከቫይረሱ ሊከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ በተደረገው ምርመራ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በሻይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ ከትናንት በስቲያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 29 ግለሰቦች መካከል 19ኙ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እንዲሁም በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያልነበራቸው መሆናቸው ትልቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡

ትናንት አርብ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠውን 3 ሰዎች ጨምሮ፣ እስካሁን 194 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ለ30ሺ 306 ሰዎች ምርመራ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ምንጭ:-  አዲስ አድማስ

በኢትዮጵያ እስካሁን ሰዓት ድረስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ቁጥር እንደሚከተለው ነው

confirmed 0, deaths 0, recovered 0

 

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top