Connect with us

የኮሮና ቫይረስ ተመራማሪው አሜሪካ ውስጥ ተገደለ

የኮሮና ቫይረስ ተመራማሪው አሜሪካ ውስጥ ተገደ
Bing Liu | ዶ/ር ሊኡ በሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው የተከታታሉ ሲሆን ለሳይንሱ ዘርፍ የተለየ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጎበዝ ተመራማሪ ነበሩ

ዜና

የኮሮና ቫይረስ ተመራማሪው አሜሪካ ውስጥ ተገደለ

በኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር ሲያደርጉ የነበሩት እና አዲስ ግኝቶችን ለማውጣት ጫፍ ላይ ደርሰው የነበሩት ተመራማሪ መገደላቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

በፒትስበርግ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ተመራማሪ የነበሩት ዶ/ር ቢንግ ሊኡ፤ በፔንሲልቫኒያ በሰሜን ፒትስበርግ ሮስ ታውንሽፕ ሕይወታቸው አልፎ እንደተገኙ ባለፈው ቅዳሜ የአካባቢው የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ የተማራማሪው አስክሬን ከተገኘበት ቦታ አንድ ማይል ርቀት ላይ ወዲያውኑ የሁለተኛውን ሟች ሃኦ ጉ አስክሬን መኪና ውስጥ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

መርማሪዎች ለኤንቢሲ እንዳሉት ሃኦ ጉ፣ ዶ/ር ሊውን ገድለው ከዚያም ራሳቸው ላይ በመተኮስ ሕይወታቸው ሳይልፍ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የህክምና ትምህርት ቤቱ በድረገጹ ላይ ባስነበበው መግለጫ ዶ/ር ሊኡ በሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው የተከታታሉ ሲሆን ለሳይንሱ ዘርፍ የተለየ አስተዋጽኦ ያደረጉ ጎበዝ ተመራማሪ ነበሩ ሲል ገልጿቸዋል፡፡

አክሎም ዶ/ር ሊኡ ከኮሮናቫይረስ ጀርባ ያለውን ዑደት ለመረዳት የሚያስችል ወሳኝ የሆነ የምርምር ውጤት ለማግኘት ጫፍ ላይ ደርሰው ነበር ብሏል፡፡

በመሆኑም ለሳይንስ ዘርፉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ክፍያ ተመራማሪው የጀመሩትን ምርምር ለማጠናቀቅ ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

መረጃው የቢቢሲ ነው

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top