Connect with us

ፓርላማው ምርጫን በተመለከተ የሕገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ ወሰነ

ፓርላማው ምርጫን በተመለከተ የሕገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ ወሰነ

ህግና ስርዓት

ፓርላማው ምርጫን በተመለከተ የሕገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ ወሰነ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ልዩ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማከናወን አለመቻሉን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በምክር ቤቱ መጽደቅን ተከትሎ ቀጣይ ህገመንግስታዊ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመፍትሄ አማራጮችን መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብ መመራቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ንዑስ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አበበ ጌዴቦ ቋሚ ኮሚቴው ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የህገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

(ኢኘድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top