Connect with us

ክልሎች ለብቻቸው ምርጫ ማድረግ አይችሉም

ክልሎች ያለፌዴራል መንግስት የምርጫ ቦርድ ተሳትፎ ለብቻቸው ምርጫ ማድረግ አይችሉም
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ክልሎች ለብቻቸው ምርጫ ማድረግ አይችሉም

“ክልሎች ያለፌዴራል መንግስት የምርጫ ቦርድ ተሳትፎ ለብቻቸው ምርጫ ማድረግ አይችሉም”
(ፍሬህይወት ሳሙኤል ~የሕግ ባለሙያ)

በመርህ ደረጃ ክልሎች እራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ በመረጡትም ይተዳደራሉ ማለት ምርጫም ማድረግ ይችልሉ ማለት የሚል መልእክት እንዳለው እረዳለሁ። ነገር ግን ይህ የክልሎች መብት ለብቻው የሚቆምና ተፈፃሚ የሚሆን አይደለም። ምክንያቱም የአገሪቱ ህገመንግስት አንቀፅ 102 ስር በኢትዮጵያ በሞላ ምርጫን የማካሄድ መብት የተሰጠው ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስለሆነ ነው።(የግርጌ አባሪ ይዩ)።

ይህን በምሳሌ ለመግለፅ የህል፤ በአገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት አንድ ሰው መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት አለው። ይህ ማለት ግለሰቡ እስከቻለ ድረስ ቤት የመስራትንም መብት ይጨምራል ማለት ነው። ነገር ግን አንድ ሰው አቅሙ ስለቻለና ክፍት መሬት ስላገኘ ብቻ ሄዶ መኖሪያ ቤት መስራት ይችላል ማለት አይደለም። ቤት ሲሰራ በአገሪቱ ህግ መሰረት ቦታ መመራት፤ የቦታ ካርታ ማሰራት፤ የግንባታ ፈቀድ ማውጣት መቻል አለበት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ መኖሪያ ቦታ ማግኘት ሕገመንግታዊ መብቴ ነው በሚል መነሻ ብቻ ባገኘው ክፍት ቦታ ቤት ሰርቶ ለተገኘ ሰው ቤቱም በተለምዶ ‘’የጨረቃ ቤት” ይባላል።

የባለቤትነትም ካርታ ስለሌለው ማብራት፤ ውሃ፤ የመንገድ . . . . ወዘተ የማግኘት መብት አይኖረውም። ቤቱም ፈራሽ ነው ማለት ነው። ልክ እንደዚሁ ምርጫም በመርህ ደረጃ የክልል መንግስታትም መብት ቢሆንም ምርጫውን በህግ መሰረት ብቻ ማድረግ ደግሞ ግዴታቸው ነው። ህጉ ደግሞ ምርጫን ማስፈፀም በግልፅ የፌዴራል የምርጫ ቦርድ ስልጣን ነው ስለሚል ክልሎች ከዚህ የህገመንግስት ድንጋጌ ውጭ (ለብቻቸው ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ) ምርጫ አድርገው ቢገኙ ‘ የጨረቃ ምርጫ’ ማለት ቢቻል እንጂ ህገመንግስታዊ እውቅና ያለው ምርጫ ሊሆን አይችልም። ምርጫ ደግሞ በውጤቱ መንግስትን መመስረት ነው።

ስለሆነም ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ ምርጫ ኢ-ህገመንግስታዊ መንግስት በውጤቱ ይወልዳል። ቀጥሎም የፌዴራል መንግስት ለእንደዚህ አይነት ኢ-ህገመንግስታዊ የክልል መንግስት በጀት መመደብ አይችልም ወደሚል ድምዳሜ ያመጣናል። በኢትዮጵያ ለ”ጨረቃ ምርጫ” አሸናፊ ቡድን እውቅና ሰጥቶ በጀት ከመመደብ ይልቅ “ለጨረቃ ቤት” ማብራትና ሌላም ግልጋሎት ማስገባትና ህጋዊ ማድረግ ይቀላል። ያለምርጫ ቦርድ ተሳትፎ ሰዎች፤ቡድኖች ተመራርጠው መንግስትነትን ማወጅ የሚችሉበት ህገመንግስታዊ ቀዳዳ የለም። አለ የሚሉ የህግ ባለሙያዎች ካሉ መከራከር ይቻላል።

ክልሎች የሚመቻቸውን የምርጫ ህግ ያውጡ እንኳ እንዳይባል ምርጫን የሚመለከት ህግ የማውጣትም ስልጣን በህገመንግስቱ አንቀፅ 51 (15) መሰረት የፌዴራል መንግስቱ ስልጣን ነው።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top