Connect with us

የህወሓቶች ነገር!… ገዳይ ቢያረፋፍድ ሟች ይገሰግሳልን ያስታውሳል

የህወሓቶች ነገር!... ገዳይ ቢያረፋፍድ ሟች ይገሰግሳልን ያስታውሳል
Photo Facebook

ፓለቲካ

የህወሓቶች ነገር!… ገዳይ ቢያረፋፍድ ሟች ይገሰግሳልን ያስታውሳል

የህወሓቶች ነገር!… ገዳይ ቢያረፋፍድ ሟች ይገሰግሳልን ያስታውሳል
(እሱባለው ካሳ)

ያረጀው ያፈጀው የህወሓት አመራር ተሰባስቦ መቀለ ከመሸገ ሁለት ዓመታትን ደፈነ። ብዙዎቹ የእስር ማዘዣ ከፍርድ ቤት ባይወጣላቸውም አዲስአበባን ለመርገጥ በመፍራታቸው እዚያው መሽገው ለመቀመጥ ተገደዋል። ራሳቸውን የቁም እስረኛ አድርገዋል። መቀመጥ ብቻም ሳይሆን ለዚህ ዳርጎናል በሚሉት የጠ/ሚ ዐብይ መንግሥት ላይ ጥርስ ነክሰዋል። ሲጀምር በከሀዲነት ፈርጀውታልና ምንም ቢሰራ የማይዋጥላቸው ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት አለምአቀፍ የኮሮና ወረርሽኝ በርካታ አገራት ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ እንዳዛባው ሁሉ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ችግር ተከሰተ። ምርጫ ቦርድ በያዝኩት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫ ማካሄድ ተስኖኛል አለ። ህወሓቶች በተለመደው መልኩ በተቃራኒው ቆሙ። ወረርሽኝ ባለበትም ቢሆን ምርጫ መካሄድ አለበት ማለታቸው በፌደራል ደረጃ ሰሚ ሲያጣ በክልል ደረጃ እናካሂዳለን ብለው ከሰፊ የእርግማን ዲስኩር ጋር ትላንት መግለጫ አወጡ።

እሺ፤ እንደመሻታቸው ይሁን እንበል። ከማን ጋር ሊወዳደሩ አስበዋል? ግራ የገባው ነገር እኮ ነው። በክልሉ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በህወሓት አፈና ምክንያት ለወትሮም ቢሆን እንኳንስ ምርጫ ቀርቶ አባሎቻቸውን ሰብስበው ለማናገር የማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለመድረሳቸው ደጋግመው የተናገሩት ነው። በተቃዋሚነት የተጠረጠረን ሁሉ ሰዶ ማሳደድ የአብዮታዊ ዴሞክራቷ ህወሓት መለያ ሆኖ ለ27 አመታት ዘልቋል።አሁንም ያ ክፉ ልማድ በትግራይ ቀጥሏል።

የገዥው ፓርቲ ብልፅግና በክልሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት መክፈት ብቻ ሳይሆን ከህወሓት ያፈነገጡ በርካታ አባላት እያቀፈ መምጣቱ እውነት ቢሆንም በፌደራል ደረጃ ምርጫው የሚራዘም በመሆኑ በህወሓት ምርጫ ላይ ብልፅግና ተሳትፎ አጃቢ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። እናም ህወሓቶች በቅጡ አይተውት፣ አክብረውት የማያውቁትን ህገመንግስት ጠዋት ማታ እየማሉ ምርጫ እናድርግ የሚሉት ከማን ጋር ሊወዳደሩ አስበው እንደሆነ የሚያውቁት እነሱ ብቻ ናቸው።

በዚህ ላይ ምርጫ የማካሄድ ሥልጣን ያለው አካል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ ነው። ከእሱ እውቅና ውጭ በማን ምርጫ አስፈፃሚነት ሊያካሂዱ ነው? ነው ወይስ ክልላዊ ምርጫ ቦርድ ሊመሰረቱ ነው?

እሺ፤ ይኸም ይሁን ይባል። ለምርጫ ስራ የሚያስፈልግ ከፍተኛ በጀት ከየት ይመጣል? አመታዊ በጀትን አጥፎ ለዚህ ሥራ ማዋል የፌደራል መንግስት ይሁንታ አይፈልግምን?

ይኸ ሁሉ ተደርጎም ተወዳዳሪ በሌለበት ህወሓት መቶ ፐርሰንት አሸነፈን ማወጅ ትንሽ አይሸክክምን? ሼም የሚባል ነገር የለምን? ለፌደራል ፓርላማ የሚመረጡ ሰዎች አዲስአበባ መጥተው ፓርላማ መግባት ይችላሉን?

እንዲያው ግራ ግብት ያለው ነገር እኮ ነው።በጥላቻ የታወረ አእምሮ ከዚህ ሻል ያለ ሀሳብ ቢያፈልቅ ነበር የሚያስገርመው።ለመሆኑ የፌደራል መንግሥት ትግእስቱ አልቆ ህጋዊ እርምጃ ወደመውሰድ ቢገባ ጎምቱዎቹ ዘለው ወደጦርነት ሊገቡ ነው የሚያስቡት?

ሲያልቅ አያምር እንዲሉ የህወሓት ጎምቱዎች ሸምቀቆውን በራሳቸው ላይ እያጠበቁ ነው።ገዳይ ቢያረፋፍድ ሟች ይገሰግሳል ይሉሀል ይኸ ነው።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top