Connect with us

የኢ/ር ታከለ ኡማ ውሳኔ፣ የቀረበላቸው ተማጽኖ…

የኢ/ር ታከለ ኡማ ውሳኔ ፣የቀረበላቸው ተማጽኖ... | በታምሩ ገዳ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የኢ/ር ታከለ ኡማ ውሳኔ፣ የቀረበላቸው ተማጽኖ…

የኢ/ር ታከለ ኡማ ውሳኔ ፣የቀረበላቸው ተማጽኖ… | በታምሩ ገዳ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋትን ለመቀነስ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹ እንቅስቃሴ እንዲወሰን ባደረገበት በዚህ ወቅት በመዲናይቱ አዲስ አበባ የሚገኙ ዜጎችን በህገ ውጥ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ስም ማፈናቀሉ ለወረርሽኙ መስፋፋት በር ሊከፍት ይችላል ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ስጋታቸውን ገለጹ፣ ተማጽኖም አቀረቡ። መስተዳድሩ በበኩሉ እርምጃውን እንደሚገፋበት ገልጿል።

ዜና አገልግሎት ሮይተርስ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጠቅሶ እንደዘገበው “የህገወጥ ቤት ሰሪዎችን የማፈናቀሉ እርምጃ፣ የወረርሽኙ ስርጭት እስከሚገታ እና የአስቸኳይ ጊዜው አዋጅ እስኪነሳ ድረስ ዜጎችን የማፈናቀሉ እርምጃ ይቁም። በዚህ ወቅት የሚደረግ ማንኛውም ማፈናቀል ቤተሰቦችን፣ ሴቶችን፣ ህጻናትን ለኮሮና ወረርሽኝ ተጋላጭነታቸውን ከፍ ያዳርገዋል” ሲሉ የኮሚሽኑ ዋና ሹም የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ” ተማጽነዋል።

አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ ” የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ማህበራዊ ቀውስ ሳቢያ ከእለታዊ ስራቸው የተፈናቀሉ ፣ በህገ ወጥ መንገድ ጎጆ ቀልሳዋል የታባሉ ከአንድ ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በመስተዳድሩ አፍራሽ ግብረ ኃይል ከሚኖሩበት አካባቢ መፈናቀላቸው የኮሮና ተጋላጭነትን ሊያባብስ እንጂ አይቀንስውም “ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዛሬ ባወጣው መግለጫው ስጋቱን ገልጿል።

የመብት ተሟጋቹ የምስራቅ እና ደ/አፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ዲፖርሴ ሙቺና በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት” በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ሰዎች በቤት ውስጥ መወሰናቸው የወረርሽኙ ስርጭትን ይቀንሳል፣ ከዚህ አኳይ በመፈናቀል ምክንያት የዜጎችን ለኮሮና ወረርሽኝ ተጋላጭነትን አናበራክተው። መሄጂያ ያጡ በርካታ ወላጆች እና ህጻናቶች ካለፈው ሚያዚያ/አፕሪል 6,2020 እኤአ ለአስከፊ ችግር ተጋልጠዋል “ሲሉ የተማጽኖ ጥሪያቸውን አግባብነት ላላቸው ለባለስልጣናቱ አሰምተዋል።

ፎቶው ለገጣፎ/ለገዳዲ የፈረሱ ቤቶችን የሚያሳይ ሲሆን በየካቲት ወር ላይ የፈረሱ ናቸው

የአዲስ አበባ መስተዳድር ም/ል ከንቲባ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ለሮይተርስ በሰጡት አስተያየት” መንግስት የወሰደው እርምጃ ሰዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይሰደዱ እና መሬት ከመንግስት እና ከአርሶ አደሮች እንዳይቀራመቱ ለማስቆም ሲባል ነው። በወረርሽኙ ምክንያት መንግስት በሰዎች መካከል መራራቅ እንዲተገበር ሲጥር አንዳንድ ወገኖች አጋጣሚውን ቤት ለመስራት እየተጠቀሙበት ነው፣ ህገ ወጥ ቤቶቹን የማፍረሱ ዘመቻ ይቀጥላል” በማለት ከመብት ተሟጋቾቹ ድርጅቶች ለቀረበው ተማጽኖ ጆሮ ዳባ ልበስ ዋል።

ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የመንግስት ነው፣ መሸጥ መለወጥ አይቻልም፣ ዜጎችም በረጅም አመት የሚቆይ ኪራይ(ሊዝ መልክ) የባለቤትነት መብታቸው እንደሚከበር በህግ የተደነገገ ቢሆንም፣ እንደ ባለቤቶች እና የመሬት ጉዳይ ባለሙያዎች እይታ በአንዳንድ የዘመኑ ግልገል ባለስልጣናት፣ ደላሎች እና መሬት አልሚዎች ቀጥተኛ እና የእጅ አዙር ተባባሪነት ከፍተኛ የህገ ወጥ የመሬት ሽያጭ እና ገንዘብ ማጋበስ ወንጀል እንደሚፈጸም ዜና አገልግሎት ሮይተርስ አውስቷል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top