Connect with us

አንዳንድ እውነታዎች ስለ ደማ ከሴ

አንዳንድ እውነታዎች ስለ ደማ ከሴ
Photo: Social media

ጤና

አንዳንድ እውነታዎች ስለ ደማ ከሴ

የምች መድኃኒት ስሙ ዳማ ከሴ ….

የተሳሳተ በመሆኑ መዘናጋት አይገባም። ወረርሽኙ እድሜ፣ ጾታ፣ ዘርና ቀለም ሳይለይ እንደሚያጠቃና ልጆችም ተጠቂዎች እንደሚሆን ተገንዝበው ሊጠነቀቁ ይገባል ብሏል። እንዲሁም በሽታው ጥቁሮችንም አይዝም የሚባለው ውሸት ነው። በጤናው ዘርፍ ብዙ ተጉዘዋል የሚባሉ ሀገሮችን በከፍተኛ ደረጃ እንደተጎዱ አይተናል። እኛ በጤናው ዘርፍ ልምድ የሌለን ደግሞ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ካልቻልን ጉዳቱ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።

በሀገራችን ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ እጽዋት ለሕክምና አገልግሎት ይውላሉ። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ደማ ከሴ አንዱ ነው።

• ደማ ከሴ አገር በቀል ተክል ሲሆን በሳይንሳዊ ስሙ ኦሲመም ላሚፎለም(Ocimum lamiifolium) እየተባለ ይጠራል።

• ተክሉ ሁለገብ የሆነ የመድኃኒትነት ባህሪ አለው። በሀገራችን በአብዛኛው ቦታዎች የምች መድሀኒት በመባል ይታወቃል።

• በባህላዊ ሕክምና ከተክሉ የሚገኝ ጭማቂ ለተለያዩ የዐይን በሽታዎች፣ ለራስ ምታት፣ በተለይ ትኩሳት ሲያጋጥም በባሕላዊው አጠራር ‹‹ምች›› እየተባለ ለሚጠራው ሕመም ማስታገሻነት ይውላል።

• በተጨማሪም ለምለም ቅጠሉ ተጨምቆ ሲጠጣ ለተቅማጥ፣ ለአሜባ (ደም ያለው ተቅማጥ)፣ ለሳልና ለሌሎችም ሕመሞች ለማስታገሻነት ይውላል።

• በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ለቆዳ፣ ለአንጀት፣ ጨጓራና ተያያዥነት ላላቸው ሕመሞች ይወሰዳል።

• ተክሉ ለተለያዩ የጤና ችግሮች አስተማማኝ የሚባል የፈውስ ባህሪ አለው።

• የፀረ-ወባ ገቢርነት እንዳለውም ይታወቃል።

• ቅጠሉን በማጨስ የወባ ትንኞችን ከአካባቢ እንዲርቁ ማድረግ ይቻላል።

• በተጨማሪም ፀረ ፈንገስና ፀረ ነፍሳት ባህሪ አለው። እንዲሁም ትኩሳትን ያበርዳል።

• ደማ ከሴ በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን ለዕቃ ማጠኛ አገልግሎት ይውላል።

• አብዛኛውን ጊዜ ለመድኃኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሀ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።

• ለጉንፋን፣ ለራስ ምታት ጥቅም ላይ ይውላል።

• የቅጠሉ ጭማቂ በውሃ ወይም ከቡና ጋር ለትኩሳት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

• የአንጎል ጥቃት (ስትሮክ)፣ የጀርባ አጥንት መጨፍለቅ፣ የጅማት መጨማደድን ለማከም ከፍተኛ ጥቅም አለው።

• በጥቅሉ ከነርቭና ከጡንቻ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለማከም ማለትም የጡንቻ መዛል፣ ከቀዶ ሕክምና በኋላ የሚደረጉ የአካል እንክብካቤዎች፣ ከስፖርት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፣ ከእጅና እግር መቆረጥና ከአጥንት መሰንጠቅ ጋር ያሉ ችግሮችን በቀላሉ ለማከም አገልግሎት ላይ ይውላል።

• የቅጠሉ ወይም የልጡ አካል በቁስል ላይ በመለጠፍ ቁሰሎችን በቀላሉ ለማዳን አገልግሎት ይሰጣል።

አዲስ ዘመን ሚያዚያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top