Connect with us

በኢትዮጵያ በቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊዮን በላይ ቤቶች ተዳርሰዋል – ዶ/ር ሊያ

በኢትዮጵያ በቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊዮን በላይ ቤቶች ተዳርሰዋል - ዶ/ር ሊያ
Photo Facebook

ጤና

በኢትዮጵያ በቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊዮን በላይ ቤቶች ተዳርሰዋል – ዶ/ር ሊያ

በኢትዮጵያ በቤት ለቤት ቅኝት ከ3 ሚሊዮን በላይ ቤቶች ተዳርሰዋል – ዶ/ር ሊያ

በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ቅኝት ከሦስት ሚሊዮን በላይ ቤቶች መዳረሳቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ሚኒስትሯ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው የቅኝት ሥራ ዳሰሳው ተካሂዷል።

በዚህም የቫይረሱ ምልክት የታየባቸው 427 የሚሆኑ ሰዎች መለየታቸውን ተናግረዋል።

በጤና ኤክስቴንሽን፣ በግብርና ልማት ባለሙያዎች፣ መምህራንና በሌሎች በጎ ፈቃደኞች ቅኝቱ እየተደረገ መሆኑንም ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

ቅኝቱ የቫይረሱ ስርጭት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስችላል ብለዋል።

World History Chart

ቫይረሱን ለመከላከል እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ መጀመሪያ ትኩረት የተደረገው በኤርፖርቶችና በየብስ ወደ አገር በሚገቡ ሰዎች ላይ እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤በሂደት ዳሰሳው በአዲስ አበባና በክልሎች እንዲስፋፋ መደረጉን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አብዛኛዎቹ ከውጭ የሚመጡና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቢሆኑም፤ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ያለመሄድንና የተዳከመ አገልግሎት ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ሊያ አመልክተዋል።

የቫይረሱ ስርጭት ለመከላከል የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ኅብረተሰቡ ቫይረሱን ለመከላከል ኃላፊነቱን መወጣት ከመወጣት ባሻገር፤ በመንግሥትና በጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች እንዲተገብር አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጣቢያዎች የማደራጀቱ ሥራ መጠናከሩ ገልጸዋል።

በዚህም በአሁኑ ወቅት የጣቢያዎቹ ቁጥር 20 መድረሳቸውንና የመመርመር አቅማቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ይህም በአገር አቀፍ የምርመራ አቅምን ያሳድገዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 117 ደርሷል።25 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፣ሦስት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።

ምንጭ:- ኢዜአ

በኢትዮጵያ እስካሁን ሰዓት ድረስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ቁጥር እንደሚከተለው ነው confirmed 0, deaths 0, recovered 0

Click to comment

More in ጤና

To Top