Connect with us

የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉዳይ አሳስቦታል

የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉዳይ አሳስቦታል
Photo Facebook

ማህበራዊ

የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉዳይ አሳስቦታል

የአለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ጉዳይ አሳስቦታል

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በአፍሪካ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አዝማሚያ #እንዳሳሰባቸው ገለፁ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአፍሪካ ፣ በማእከላዊ እና በደቡብ አሜሪካ እና በምስራቅ አውሮፓ እየጨመረ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አዝማሚያዎች አሳሰቢ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡


ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በጄኔቫ በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደገለጹት፣ በምዕራብ አውሮፓ ወረርሽኙ እየተረጋጋ ወይም እየቀነሰ ቢታይም፣ ለብዙ አገሮች በሽታው ገና እየጀመረ መሆኑንና በወረርሽኙ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ጥሩ ሆነው የተገኙት አንዳንድ አገራት በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ እየተስፋፋባቸው መምጣቱን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል፡፡

“ብዙ አገራት አሁንም በወረርሽኙ የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ናቸው፤ በወረርሽኙ መጀመሪያ ላይ የተጎዱት የተወሰኑ አገራት አሁን መልሶ መቋቋም ጀምረዋል” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም “ምንም ስህተት መስራት የለብንም፣ የምንጓዘው ረዥም መንገድ አለ፣ ይህ ቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከእኛ ጋር ይቆያል” ማለታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
Credit:-EBC

በኢትዮጵያ እስካሁን ሰዓት ድረስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መረጃ እንደሚከተለው ነው

confirmed 0, deaths 0, recovered 0

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top