Connect with us

“ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ካደረግን የመከራው ጊዜ ያጥራል” – ጠ/ ሚር ዶክተር አብይ

Photo: Social media

ዜና

“ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ካደረግን የመከራው ጊዜ ያጥራል” – ጠ/ ሚር ዶክተር አብይ

“ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ካደረግን የመከራው ጊዜ ያጥራል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

ማድረግ ያለብንን ሁሉ ካደረግን በኮሮና ተህዋስ የመጣው መከራ እንደሚያጥር፤ ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን የመከራው ጊዜ እንደሚረዝም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የትንሣኤ በዓልን አስመልክቶ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ትናንት ባስተላለፉት የእንኳን አደርሳችሁ መልዕክት እንዳስታወቁት “አሁን ያለንበት ጊዜ ከሐሙስ ምሽት እስከ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ያለውን የክርስቶስን የመከራ ሰዓት ይመስላል።

ለእኛም ጊዜው የወረርሽኝ፣ የብዥታና የጥርጣሬ ጊዜ ነው። ጽናትና ጥንካሬያችን፤ መልካምነታችንና ተባባሪነታችን፤ አንድነትና ወንድማማችነታችን የሚፈተንበት ወቅት ነው።” ብለዋል።
በዚህ ወቅት ማድረግ የሚገባንን ካደረግን በተህዋሲው የመጣ መከራ የሚያጥር ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻልን ግን የመከራ ጊዜው እንደሚረዝም ገልፀዋል።

አሁን ከገጠመን በላይ እንዳይገጥምን፣ እንደ መንግሥትና እንደ ህዝብ እንደ አንድ ልብ መክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተግባራዊነቱ መጽናት ይኖርብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትንሣኤ የተማርናቸውን ትምህርቶችም በኮቪድ 19 የገጠመንን ፈተና ልንጠቀምበት ብንችል ውጤታማ እንሆናለን ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለኮሮና ተህዋስ በሚገባ ከተዘጋጀን ያለከባድ ጫና ልንወጣው እንችላለን። ፈተናውን የምናልፈው በዝግጅታችን መጠን፣ ለተግባራዊነቱ በምናሳየው ጽናት ልክ ነው። የምንታገለው እንዲያልፍ ብቻ ሳይሆን ወረርሽኙ በብዙ ሳይጎዳን የህማማቱ ጊዜ አልፎ ትንሣኤው እንዲቀርብ ነው።

“አንዳንዶች፤ የተነገራቸውን ይረሳሉ። ሌሎች ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ስህተት ይሠራሉ። የሚወራ ወሬ ከእውነታው በልጦ ይወስዳቸዋል። አንዳንዶችም የለንበትም ብለው ጥለው ይሸሻሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ “ከዚህ በተቃራኒው ያሉት ደግሞ እስከ መጨረሻው ፀንተው ይገኛሉ። በሐሰተኛ ወሬ ሳይበገሩ ከእውነት ጋር ፀንተው ይቆማሉ። አንዳንዶች ጣት በመጠቆምና በፀያፍ ቃላት በማንቋሸሸ ሲጠመዱ ሌሎች ከመከራው ቀንበር ለመሸከም ትከሻቸውን ያዘጋጃሉ። አንዳንዶች እንደ ይሁዳ ከእንግልቱ ለማትረፍ ሲሞክሩ ሌሎች የህዝቡን መከራ ለመካፈል ይመጣሉ” ብለዋል።

አቅማቸው እየፈቀደ እጃቸውን የሰበሰቡ ሰዎች ተረስተው ሲቀሩ ተገቢውን ነገር በተገቢው ጊዜ ያደረጉት ሰዎች ታሪካቸው በመልካም እንደሚነሳም ጠቅሰዋል። ዛሬ በታሪክ አጋጣሚ ለዘመናት ስማችን ከመልካም ወይም ከክፋት ጋር ተያይዞ እንዲነሳ ታላቅ የታሪክ አጋጣሚ ላይ ደርሰናልም ብለዋል።

አሁን ያለንበት ጊዜ ወቅቱ የሚፈልገውን ሥራ በተገቢ ቦታና ሰዓት አከናውነን ተጋድሎአችንን በድል ለመወጣት መወሰን ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን። ዛሬ መናገር ያለብንን እንናገር። ዛሬ ለሌሎች ማድረግ ያለብን እናድርግ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አዲስ ዘመን ሚያዚያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

Click to comment

More in ዜና

 • የአብን ዕጩ ግድያ የአብን ዕጩ ግድያ

  ነፃ ሃሳብ

  የአብን ዕጩ ግድያ

  By

  የአብን ዕጩ ግድያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት እጩ የነበረው አባላችን በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር ግድያ የተፈፀመበት መሆኑን እያሳወቅን ፓርቲያችን በአባላችን ግድያ የተሰማውን መሪር ሐዘን ይገልጻል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በቀጣይ ግንቦት 2013 ዓ.ም በሚደረገው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች በርካታ እጩ ተወዳዳሪዎችን ያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ካድሬዎች በአባላቶቻችን ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ፣ እስር እና ድብደባ እየፈተፀመ ይገኛል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በስፋት እንዲሁም አልፎ አልፎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአባላት ማጉላላት፣ እስር እና ድብደባ እየደረሰ ይገኛል ። በተደጋጋሚ ጊዜ ሰላማዊ ዜጎችን ከመጨፍጨፍ እስከ ጅምላ ማፈናቀል የዘለቀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቀደም ብሎ የክልሉ ካድሬዎች የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንዳይሳካ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም በምርጫ ቦርድ ትብብር ምዝገባው ሊከናወን ችሏል። ከዚያ በኋላም የምርጫ ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸውን በጣሰ መልኩ አስሮ በማጉላላት እና በማስፈራራት እጩዎቻችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማሳረፍ ሞክሯል።  ይህ ሁሉ አልበቃ ያለው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የፀጥታ ሰወች ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪያችን የነበረውን አቶ በሪሁን አስፈራው ከቻግኒ ወደ በለስ ጉዞ ላይ እያለ ልዩ ቦታው ካርባር ላይ ግድያ ፈፅሞበታል። አብን ግድያው ፖለቲካዊ መሰረት ያለውና ንቅናቄው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሆነ ተብሎ የተደረገ እንደሆነ ያምናል። ለዚህም የወንድማችንን ግድያ ጨምሮ በአሶሳ እና አካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ በእጩዎቻችንና አመራሮቻችን ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ ምክንያት አልባ እስሮችና ወከባዎች ከበቂ በላይ አስረጂዎች ናቸው። በመላው ኢትዮጵያ በተለይም የግጭት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ምርጫ ሲቃረብ መሰል ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ ማፈናቀሎችና ወከባወች እንደሚኖሩ ደጋግመን ለመንግስት ያሳሰብን ቢሆንም ከስሕተቱ መማር ያልፈለገው መንግስት ዛሬም ድረስ ዜጎች በጅምላ እና በተናጥል ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ እና ኃብት ንብረታቸው ሲወድም በዝምታ እየተመለከተ ይገኛል። ፓርቲያችን አብን ይህ ጉዳይ ቀስ በቀስ አገር የሚያፈርስ አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። ሰላማዊ እና ፍትኃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለውን የዜጎች ተስፋም ከወዲሁ ያጨለመ ነው የሚል ግምገማ ላይ ደርሰናል። አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድም አበክሮ የሚታገልበት ይሆናል። ስለሆነም አብን መንግስት በምርጫ እጩ አባላችን ላይ የተፈፀመውን ግድያ በአስቸኳይ እንዲመረምር እና ገዳዮችን ለፍርድ እንዲያቀርብ በአንክሮ እየጠየቀ፤ መሰል ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ለምርጫ እጩዎቻችን ተገቢው የጸጥታ ከለላ በመንግስት በኩል እንዲሰጥ እናስገነዝባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእንዝላልነት ተጨማሪ ሕይወት ቢጠፋ እና አገራችን ወዳልተፈለገ ምዕራፍ ብትገባ ተጠያቂነቱ ሙሉ ለሙሉ መንግስት የሚወስድ መሆኑን ከወዲሁ አብክረን ማሳሰብ እንወዳለን። ለሰማዕቱ ወንድማችንና ጓዳችን አቶ በሪሁን አስፈራው ቤተሰቦችና ለመላው የንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊወች መጽናናትን እንመኛለን። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)

 • #ድሬደዋ #ድሬደዋ

  ዜና

  #ድሬደዋ

  By

  #ድሬደዋ በድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ወርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማያከብሩ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ፡፡...

 • የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል ምላሽ

  ዜና

  የአፋር ክልል ምላሽ

  By

  የአፋር ክልል ምላሽ የአፋር ክልል መንግስት ንጹሀንን እየገደለና እያፈናቀለ ነው ሲል የሱማሌ ክልል ያወጣው መግለጫ ጥፋተኝነትን...

 • ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት - ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  ዜና

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

  By

  ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳንን ጾም በመተሳሰብ፣ በመተዛዘንና መልካም ተግባራት በመከወን ማሳለፍ አለበት – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር...

 • ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  ዜና

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ

  By

  ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)  የኮሮና መከላከያ ክትባት ተከተቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top