Connect with us

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለዓለም የጤና ድርጅት የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ
Photo: Social media

ዜና

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለዓለም የጤና ድርጅት የ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የቢል እና ሜሊንዳጌትስ ፋውንዴሽን የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ150 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሪክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የጌትስ ፋውንዴሽን ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት በተደረገ 401 የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 7 ሰዎች መገኘታቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 92 ከፍ ብሏል።

ዛሬ በምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከአንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ በስተቀር ስድስቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ታዳጊዋ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት ስለመሆን አለመሆኑ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው በላቦራቶሪ የተረጋገጠው የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ከአሜሪካ የመጡ የ21 ዓመት እና የ51 ዓመት እድሜ ያላቻው፣ ከስዊድን የመጡ የ76 ዓመት እና የ34 ዓመት እድሜ ያላቸው፣ የጀርመን እና የቤልጂየም የጉዞ ታሪክ ያለው አንድ የ32 ዓመት እና አንድ ከጃፓን የመጣ ሲሆን ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

በአሁኑ ሰዓት 72 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሲሆኑ አንድ ሰው ደግሞ በጽኑ ሕክምና ላይ ይገኛል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 15 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ሲያገግሙ ባጠቃላይ 5 ሺህ 389 ሰዎች ደግሞ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top