Connect with us

ኮሮናቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩት ግለሰቦች በሽብር ተከሰሱ

ኮሮናቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩት ግለሰቦች በሽብር ተከሰሱ
A security guard patrols the City of Miami Beach

ህግና ስርዓት

ኮሮናቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩት ግለሰቦች በሽብር ተከሰሱ

ኮሮናቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩት ግለሰቦች በሽብር ተከሰሱ

አሜሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ እናሰራጫለን ብለው ያስፈራሩ ሁለት ሰዎች በሽብር ወንጀል ተከሰሱ።

አንደኛው ተከሳሽ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲሆን የቤት ውስጥ ጥቃት ፈፅሞ በቁጥጥር ሥር ሲውል ፖሊሶች ላይ ምራቁን ተፍቷል፤ ሆን ብሎም አስሏል ተብሎ ነው የተከሰሰው።

የ31 ዓመቱ ግለሰብ ፖሊስ ላይ ከተፋ በኋላ ‘ኮሮናቫይረስ አለብኝ’ ሲል አሸብሯል ተብሏል። ሰውዬው ሲመረመር ነፃ መሆኑ ታውቋል።

ሌላኛው የቴክሳስ ነዋሪ ደግሞ በፌስቡክ ገፁ ለሆነ ሰው ከፍዬ መገበያያ ሥፍራ ውስጥ ኮሮናቫይረስ እንዲስፋፋ አድርጊያለሁ ብሎ በመፃፉ ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው።

የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ኮሮናቫይረስን ‘ባዮሎጂካዊ መሣሪያ’ ሲል ሰይሞታል። ቫይረሱን ተጠቅሞ ሕገ-ወጥ ድርጊት መፈፀም እስከ አምስት ዓመት ሊያስሳስር ይችላልም ተብሏል።

አሜሪካ ውስጥ ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሞተዋል።
ምንጭ ቢቢሲ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top