Connect with us

የህዳሴ ግድብ ሠራተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

የህዳሴ ግድብ ሠራተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው
Photo Facebook

ዜና

የህዳሴ ግድብ ሠራተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

“ግድቡ ከመቼውም ጌዜ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት እየሆነ መጥቷል” የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በላቸው ካሳ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሠራተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የፕሮጀክቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በላቸው ካሳ ገለፁ ።

ምክትል ስራ አስኪያጁ ለኢዜአ እንደገለፁት የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት በሁለት ፈረቃዎች ተከፍሎ ሥራው 24 ሰዓታት መከናወኑን እንደቀጠለ ነው፡፡

“ግድቡ ከመቼውም ጌዜ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት እየሆነ መጥቷል” ያሉት ኢንጂነሩ፤ ፕሮጀክቱ በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት እንዳይደናቀፍ ሠራተኞቹን ከበሽታው ለመከላከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ከአሶሳ፣ ማንኩሽ እና ከጠረፍ ከተማዋ ባምዛ ወደ ፕሮጀክቱ አቋርጠው የሚያልፉ ሰዎችና ተሸከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ፤ የቁጥጥር ሥራው ከሃገር መከላከያ እና ከፌደራል ፖሊስ ሃይሎች ጋር በመተባበር እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልፀዋል ።

በተለይም ከአዲስ አበባና ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ፕሮጀክቱ የሚመጡ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት በማቆየት የሰውነት ሙቀትና ሌሎችም ምርመራዎች በማካሔድ ጤንነታቸው ከተረጋገጠ በኃላ ከፕሮጀክቱ ሠራተኞች ጋር እንደሚቀላቀሉም አብራርተዋል፡፡

ሲሚንቶ፣ ብረታብረት እና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን ለፕሮጀክቱ የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች ከሠራተኞች ጋር ንክኪ እንዳይኖራቸው ከመኪናቸው ሳይወርዱ ጭነቱን አራግፈው የሚመለሱ ሲሆን በፕሮጀክቱ ስፍራ ለሚያድሩ ደግሞ የተለያዩ ክፍሎች ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ወደ ሥራ ሲገቡና ሲወጡ የሚጠቀሟቸው አውቶቡሶችና ሌሎች ተሸከርካሪዎች ላይ በተገቢው ጥንቃቄ በማድረግ አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በምግብ አዳራሾች፣ ካፍቴሪያዎች እና በመሰል አገልግሎቶች ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ፕሮጀክቱን ከሚያከናውኑ ተቋራጮች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ያመለከቱት ኢንጂነሩ፤ ሠራተኞች ከሥራ ሰዓት ውጪ ያለውን ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው እንዲያሳልፉ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አመራሮች ከተለያዩ እንግዶች የሚገናኙባቸውና በፕሮጀክቱ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች ከመጀመራቸው አስቀድሞ እጅ መታጠቢያ በማዘጋጀት፣ አልኮል፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያዎችን በማቅረብ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በአጋጣሚ ቫይረሱ ቢከሰት የለይቶ ማቆያ ማእከላት በአሶሳና ፓዌ ሆስፒታሎች መዘጋጀታቸውን ኢንጂነር በላቸው ተናግዋል፡፡

በፕሮጀክቱ ክሊኒኮች የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በሽታው ቢከሰት ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ስልጠና ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል፡፡

የላቦራቶሪ ምርመራ የሚያደርግ የህክምና ግብረሃይል ቡድን ከማዕከል ወደ ፕሮጀክቱ በቅርቡ እንደሚገባም ኢንጂነሩ አስታውቀዋል፡፡

በህዳሴው ግድብ ግንባታ 7 ሺህ የሚጠጉ ሠራተኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top