Connect with us

በትክክል የዝርፊያ ኔትዎርክ የተደራጀበት ተቋም ቢኖር ሜቴክ ነው

"በትክክል የዝርፊያ ኔትዎርክ የተደራጀበት ተቋም ቢኖር ሜቴክ ነው"
Photo Facebook

ፓለቲካ

በትክክል የዝርፊያ ኔትዎርክ የተደራጀበት ተቋም ቢኖር ሜቴክ ነው

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲጀመር መልካም ሀሰብን ይዞ የነበረ፤ ያስጀመሩት አካላትንም የሚያስመሰግን ተግባር ቢሆንም፤ ለግድቡ መጓተትም ሆነ ተያያዠ ችግሮች ምክንያቱ መሃል ላይ የገቡ ነቀዞች ናቸው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ሃላፊው አቶ አወሉ አብዲ ተናገሩ፡፡

የግድቡ መጓተትና ለተፈጠረው ችግር ቀዳሚ ድርሻ ያለው ሜቴክም የተደራጀ የዝርፊያ ኔትዎርክ የተደራጀበት ተቋም እንደነበርም አቶ አወሉ ገልጸዋል፡፡

አቶ አወሉ፣ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ የዓባይ ግድብ የሉዓላዊነታችን፣ የአብሮነትና አንድነታችን እንዲሁም የማንነታችን መገለጫ ነው፡፡ በብድር ወይም እርዳታ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከእለት ጉርሱ ቀንሶ የሰራው ግድብ ነው፡፡ ግድቡ ሲጀመር ሀሳቡ ጥሩ ነው፡፡ የጀመሩ አካላትም ጥሩ አስጀምረዋል፡፡ ነገር ግን መሀል ላይ ነቀዞች ገብተውበታል፡፡ ዛሬ የዓባይ ግድብ ግብጾች በዚህ ደረጃ እኛ ላይ ቀና ማለት እንዲችሉ ያደረጉት እነዚህ መሃል ላይ የገቡ ነቀዞች ናቸው፡፡

“እነዚህ አካላት አንደኛ ሀብቱን ዘርፈዋል፤ ሁለተኛም ያለ አቅማቸው ስራውን በመያዛቸው ችግር ፈጥረዋል፡፡ ስራው የተለየ ሙያ፣ እውቀትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ እንጂ ለዝርፊያና ሌብነት ካልሆነ በስተቀር የጡረተኛ ጄኔራሎችና ኮሎኔሎች ስብስብ የሚሰራው ተግባር አይደለም፡፡ እናም እነዚህ አካላት ስርዓት በሌለው አሰራር ዘረፉት፤ በዝርፊያቸውም ወደኋላ እንዲጎተት አደረጉት፡፡ ሆኖም ችግሩ በለውጡ አመራር ትኩረት ተሰጥቶት ችግሮቹ ተቀርፈዋል፤ ግንባታውም እየተፋጠነ ይገኛል” ብለዋል አቶ አወሉ፡፡

አቶ አወሉ፣ በእነዚህና ሌሎች ወቅታዊ አገራዊ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ አመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ በነገው እትማችን ይዘን የምንወጣ ይሆናል፡፡(ኢኘድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top