Connect with us

በንስሃ ማግስት ሐጢአት፤ ለመሆኑ የህዳር በሽታ በአየር ነበር እንዴ የገባው?

በንስሃ ማግስት ሐጢአት፤ ለመሆኑ የህዳር በሽታ በአየር ነበር እንዴ የገባው?
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

በንስሃ ማግስት ሐጢአት፤ ለመሆኑ የህዳር በሽታ በአየር ነበር እንዴ የገባው?

በንስሃ ማግስት ሐጢአት፤ ዛሬም ያለ ዕውቀት የጥላቻ ዘመቻ ዓይናችን በሆነው አየር መንገዳችን ላይ፤
ለመሆኑ የህዳር በሽታ በአየር ነበር እንዴ የገባው?
(ከስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ )


አሁንም አየር መንገዱ ላይ ዘለፋው ስድቡ ወቀሳው ቀጥሏል፤ ባልታደለች ሀገር ያልታደለ ትውልድ ሲጨመር አንድ መገለጫን ለማጥፋት ሁሉም አብሮ ይዘምታል፡፡ አየር መንገዱ ስምና ዝናውን ያከማቸው በአንድ ጀምበር አይደለም፤ የአየር መንገዱን ማኔጅመንትና ሰራተኛ አንድ ታክሲ በአደራ እንደሰጠነው ደርሶ ከነገ ጀምሮ አቁሜያለሁ ማለት የሚችል አስመስለነዋል፡፡

አየር መንገዱ በርካታ ዓለም አቀፋዊ ህጎች አሉት፤ መርሁና አሰራሩ የስታር አሊያንስን ደንብና ስልት ተከትሎ ነው፡፡

የአውቶቢስ ተራ ቅጥቅጥ ይመስል ጠዋት ተነስቶ በቃ አልሄድም እንዲል መጠበቅ ያስተዛዝባል፡፡ የአየር መንገዱ መሪዎች አየር መንገዱን ለማክሰር ይፈልጋሉ የሚሉ ሰዎች የጥላቻ ስካር ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ አየር መንገዱን ለማክሰር ኮሮናን አሳቡ እጅና እግርን አጣጥፎ ድራሹን ከማጥፋት የተሻለ ጊዜ አልነበረም፤ ግን ህይወት አደጋ ውስጥ ገብቶ ሰራተኛው በወረርሺኝ እየተያዘ እንኳን አየር መንገዱ ስሙን ጥቅሙንና ክብሩን አስቀጥሎ ለመጓዝ ያደረገው ጥረት ሽልማት ሲገባው ወቀሳ ተደገሰለት፡፡

አስቀድማ አሜሪካ ቻይናን አልረግጥም አለች፡፡ በቻይና ላይ የተሳለቁ ሁሉ የገጠማቸውን አይተናል፡፡ ዜጎቿን ለዕለት ጉርስ በየሀገሩ በትና ለንግድና ለስራ ቻይናና ዱባይ ያለው እንደወጣ ይቅር በር ዘግተን ደህና እንሁን የሚለው የሚያስተዛዝብም ጭምር ነው፡፡

የህዳር በሽታ መቼ በአየር ገባ፡፡ ያኔ ዓለም እንደአሁኑ ሁሉ አንድ መንደር አልነበረችም፡፡ በጥቂት ዲፕሎማቶች የገባው ወረርሺኝ ብዙ ሰው ጎዳ፡፡ ብዙ ሰው ገደለ፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ወሰኔ ዛማኔል በዚሁ ወረርሺኝ ሞቱ፡፡ አለቃ ተገኝም እንዲሁ፤ መቃብር ቆፋሪና ሬሳ ተሸካሚ እስኪጠፋ ድረስ ጭንቅ የሆነው ወረርሺኝ ንግስቲቷን ጭምር አልጋ የጣለ፤ አልጋ ወራሹን ያመመ ነበር፡፡

ዛሬ ሌላ አየር መንገድ እዚህ ሀገር መግባት ሳይከለከል ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀድሞ ይዝጋ ማለት በሽታውን ፍራቻ ብቻ ሳይሆን ስኬታማ መሪዎቻችንን ጥላቻም ነው፡፡ ሁሉም የተነተንኩት ካልተተገበረ የሚልባት ሀገር ለሁሉም የማትሆን ኋላ ቀር መሆኗ አይካድም፡፡

በሌላ በኩል የአፍሪቃ መዲናዋ፣ የዲፕሎማት መቀመጫዋ ሀገር እንዲሁ ከነገ ጀምሮ ማንም አይገባም ማንም አይወጣም ማለት ትችላለች ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ አይ የእኛው አየር መንገድ ይቁምና ይክሰር ሌላ አየር መንገድ እንዳሻው ይሁን የሚለፈው ፌዝ ነው፡፡

ስራችንን በአግባቡ ባለመስራታችን ትንሽም ቢሆን ችግር ገጥሞናል፡፡ ገና ይብሳል የሚለው ቅስቀሳ የሟርተኛ ጥቁር ምላስ ስለሆነ እግዜር እንደ ኮሮናው ሁሉ ከዚህም እንዲብስ ከሚፈልግ ምላስ ይጠብቀን፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እግዜአብሔርን አመሰግናለሁ በማለታቸው ያ ሁሉ ኡኡታ አያስፈልግም፤ ለምን አልበዛምና ገና ይበዛል የሚሉ ፉከራዎች በንስሃ ማግስት ዳግም ሃጢአት መውደቅ ነው፡፡

ከምንም በላይ ግን አንድን የሀገር ምሰሶ ተቋም እንደቀልድ ሀገር የሚገድልና የሚያነሳ ጉዳይን ፈጥኖ ብቻውን ለምን አልወሰነም ከማለት በፊት መወሰንስ ይችላልን? ብሎ መጠየቁ መልካም ይመስለኛል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top