Connect with us

“አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም” ሲሉ ዶክተር ቴዎድሮስ ተቹ

Photo Facebook

ማህበራዊ

“አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም” ሲሉ ዶክተር ቴዎድሮስ ተቹ

የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የተባለውን ሃሳብ “ዘረኛ” አስተሳሰብ ሲሉ ዶክተር ቴዎድሮስ ተቹ

በሁለት የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት ያሉትን ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” ዘረኛ” ሲሉ ተቹ።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው።

ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን ” መሞከሪያ አይጥ” አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ” አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም” ብለዋል።

“በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንቲስት እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት የተዋረደ፣ አሳፋሪ ነው። እንዲህ ዓይነት ነገርን በማንኛውም ሁኔታ እናወግዛለን። እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር ይህ በጭራሽ አይሆንም” ብለዋል።

ምንጭ:- ቢቢሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top