Connect with us

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ
Photo Facebook

ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።

ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top